Get Mystery Box with random crypto!

❖የሐምሌ ሥላሴ በዓል ድንቅ ምስጢር❖ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ ❖ አብርሃም ከደግነ | 💖 ዝማሬ መላዕክት 💖

❖የሐምሌ ሥላሴ በዓል ድንቅ ምስጢር❖
በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
❖ አብርሃም ከደግነቱ ብዛት እንግዳን ከመውደዱ የተነሣ ድንኳኑን በተመሳቀለ ጎዳና ሠርቶ የወጣ የወረደውን ያለፈ ያገደመውን ሲቀበል የሚኖር በሥራው ኹሉ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ጻድቅ ነበር (ዘፍ 18:1-10)፡፡ ጽድቁም ሊታወቅ ስድስት ሰዓት ላይ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ፤ በመምሬ ዛፍ ሥር እግዚአብሔር በአንድነት በሦስትነት ተገለጸለት ዐይኑን አቅንቶ ሲመለከት፤ ሥላሴ በአምሳለ ዕደው ቆመው አይቶ፤ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ።

❖ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ሰለዚኽ ነገር በድጓው ላይ፦
"ዮም አብርሃም ሰገደ ለፈጣሪሁ
ሶበ ነጸረ ዋሕደ በሥላሴሁ"
(ዋሕደ ባሕርይ የኾነ እግዚአብሔርን በአካላዊ ሦስትነቱ ባየው ጊዜ አብርሃም ዛሬ ለፈጣሪው ሰገደ) ይላል፨

❖ የተገለጡለት ሰዓቱ ቀትር (ስድስት) ሰዓት በዕንጨት ሥር በሰው አምሳል መኾኑ ቀደምት ሊቃውንት ሲያራቅቁት በአብ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በራሱም ፈቃድ ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ ዘመኑ ሲፈጸም የአብርሃምን ባሕርይ ተዋሕዶ ፍጹም ሰው ኾኖ በስድስት ሰዓት በዕንጨት መስቀል ላይ ለቤዛ ዓለም የሚሰቀል መኾኑን ያጠይቃል ይላሉ፨

❖ ይኽነን ይዞ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሕማማት ሰላምታው፦
"ለአብርሃም አብ ቀዳሚ ዘአስተርአይኮ ክርስቶስ
ቀትረ ታሕተ ዕፀ ድርስ
ተሰቀልከ ከመ እቡስ ስብሐት ለከ"
(ምስጋና የተገባኽ ጌታ ድርስ በሚባል የዛፍ ዐይነት ሥር በስድስት ሰዓት ለአባታችን አብርሃም ቀድሞ የተገለጥኽለት ክርስቶስ ሆይ እንደ በደለኛ ተሰቀልኽ) ይላል፨

❖ ከዚኽ በኋላ "አቤቱ በፊትኽስ ሞገስ አግኝቼ እንደኾነ ባሪያኽን አትለፈኝ ብዬ እለምናለኍ፤ ጥቂት ውሃ ይምጣላችኍ፤ እግራችኹን ታጠቡ፤ ከዚኽችም ዛፍ በታች ዕረፉ…" በማለት ተናግሯል፡፡
"በፊትኽ ሞገስን አግኝቼ" ብሎ አንድነታቸውን፤
"ውሃ ይምጣላችኍ፣ ዕረፉ፣ ትኼዳላችሁ" ብሎ የሦስትነታቸውን ምስጢር ገልጾአል፡፡

❖ ይኸው ሊቅ ያሬድ ይኽነን ይዞ በድጓ ላይ፦
"ይቤሎሙ ዮም አብርሃም ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አመጽእ ማየ ወአሐጽብ እገሪክሙ ወእርከብ ሞገሰ በቅድሜክሙ" (አብርሃም ዛሬ አብ ወልድና መንፈስ ቅዱስን ባለሟልነትን በፊታችሁ አገኝ ዘንድ ውሃን አምጥቼ እግራችኹን አጥባለሁ አላቸው) ይላል

❖ ይኽቺ አንድነቱ ሦስትነቱን ሳይጠቀልለው ሦስትነቱ አንድነቱን ሳይከፍለው በአንድነት በሦስትነት የሚመሰገን እግዚአብሔር የተገለጠባት ዛፍ፤ አንድነት ሦስትነት በጐላ በተረዳ ነገር የታወቀባት ከሦስቱ አካል አንዱ አካል እግዚአብሔር ወልድን በድንግልና የወለደች የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ መኾኗን፤ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ እንዚራ ስብሐት መጽሐፉ ላይ
"አንቲ ውእቱ ዕፀ ድርስ ዘለአብርሃም በርስአኒሁ
ዘብኪ አጽለለ እግዚአብሔር በሥላሴሁ"
(ለአብርሃው በእርጅናው ወቅት፤ እግዚአብሔርን በሦስትነት ያስጠለለብሽ የወይራ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት ሲገልጥ፦

❖ ዳግመኛም በዚኹ መጽሐፉ፡-
"እንቲ ውእቱ ዕፀት ዘነበርኪ ጥቃ ኀይመት፣
ዘብኪ አጽለሉ ሠለስቱ አጋዕዝት"
(ባንቺ ሦስቱ ጌቶች (ሥላሴ) የተጠለሉብሽ በድንኳን አጠገብ የቆምሽ ዕንጨት አንቺ ነሽ) በማለት በአንድነቱ ምንታዌ (ኹለትነት)፣ በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) ለሌለበት አምላክ የሦስትነቱ የአንድነቱ ምስጢር መገለጫ የሥላሴ ማደሪያ መኾኗን መስክሯል፡፡

❖ ከዚኽም ምስጢር የተነሣ አብርሃምም ሳራን “ሦስት መስፈሪያ የተሠለቀ ዱቄት ፈጥነሽ አዘጋጂ፤ ለውሺውም እንጎቻም አድርጊ” በማለት የተገለጸለትን የሦስትነት የአንድነት ምስጢርን አጒልቶ ተናግሯል፡፡

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ይኽነን ይዞ በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
"ግናይ ለክሙ ሥሉስ ቅዱስ ነገሥተ ሰብዐቱ አብያት
እለ በላዕክሙ ውሣጤ ኀይመት
አሐደ ኅብስተ ትሥልስት"
(ከሦስት መስፈሪያ ዶቄት የተጋገረ አንድነት ያለው ኅብስትን በድንኳን ውስጥ የተመገባችሁ የሰባት ቤቶች (ሰማያት) ነገሥት ሆይ ለእናንተ መገዛት (ምስጋና) ይገባል) ይላል፨

❖ አብርሃምም በደስታ ኾኖ መዐር፣ ወተት፣ ያዘጋጀውን ጥጃ አመጣላቸው፤ እነርሱም ደስ ይበለው ብለው በግብር አምላካዊ ተመግበዋል፤ መላእክት ሎጥ ቤት፤ ቅዱስ ሩፋኤል ጦቢት ቤት ተመገበ የተባለው አንድ ነው፤ እሳት ቅቤ በላ እንደማለት ብቻ ነው፨

❖ ይኸውም ወተትና መዐር መመገባቸው ኦሪትን ወንጌልን መሥራታቸውን ሲያጠይቁ ነው፤ መዐር የኦሪት፤ ቅቤ የወንጌል ምሳሌ ነው፨ ማር ለጊዜው ሲይዝ የሚለቅ አይመስልም፤ ግን ይለቃል ኦሪትም ስትሠራ የምታልፍ አትመስልም ነበር ግን በኽዋላ ዐልፋለች፨ ወተት የወንጌል ምሳሌ ነው፤ ይኽ ወተት ለጊዜው የሚለቅቅ ይመስላል በኽዋላ ሲያጥቡት አይለቅም ወንጌልም ለጊዜው ስትሠራ የምታልፍ ትመስል ነበር፤ በኽዋላ ግን ጸንታ የምትኖር ኾናለችና በማለት መተርጉማን ያራቅቁታል፡

ከሦስቱ አንዱ እግዚአብሔር ወልድ አብርሃምን "የዛሬ ዓመት እንደዛሬው ጊዜ ወደ አንተ በእውነት እመለሳለኍ፤ ሚስትኽ ሳራም ልጅን ታገኛለች" በማለት ዘመኑ ሲፈጸም እግዚአብሔር ወልድ ከቤተ አብርሃም ከተገኘች ከእመቤታችን የመወለዱንና፤ በሳራ የተመሰለች ወንጌል ምእመናንን እንደምታስገኝ በምስጢር ገልጾለታል፤ ቅዱስ ጳውሎስም አካላዊ ቃል በሰጠው ተስፋ መሠረት ከነገደ አብርሃም የመወለዱን ነገር ለዕብራውያን ሰዎች በጻፈው መልእክቱ ላይ "በሕይወታቸው ኹሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ኹሉ ነጻ እንዲያወጣ፤ በሥጋና በደም እንዲኹም ተካፈለ፣ የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም" በማለት ገልጾታል (ዕብ ፪፥፲፭-፲፮)፡፡

❖ ይኽቺ ሥላሴ የገቡባት ኀይመተ አብርሃም (የአብርሃም ድንኳን) የቅድስት ድንግል ማርያም ምሳሌ ናት፤ ይኸውም ሥላሴ ወደ አብርሃም ድንኳን እንደገቡ ኹሉ፤ በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያምም፤ አብ ለአጽንኦ፣ መንፈስ ቅዱስ ለአንጽሖ፣ ወልድ በተለየ አካሉ ሥጋን ለመዋሐድ ዐድረዋል (ሉቃ ፩፥፴፭)፤ በመኾኑም አማናዊቷ የሥላሴ ማደሪያ የአብርሃም ድንኳን እመቤታችን ብቻ ናት፡፡

❖ ሊቁም በነገረ ማርያም ይኽነን ምስጢር ሲገልጽ "ወይእቲ ኀይመት ትትሜሰል በድንግል ወዕደው አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ እሙንቱ፤ አብ አጽንኣ፣ ወወልድ ተሰብአ እምኔሃ፣ ወመንፈስ ቅዱስ ቀደሳ ከመ ትጹር አምላከ በከርሣ" (ያቺ ድንኳንም በድንግል ትመሰላለች፤ ሰዎቹም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ናቸው፤ አብ አጸናት፣ ወልድም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኾነ፣ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ቃል አምላክን ትሸከም ዘንድ ለያት) በማለት ተርጉሞታል፨

❖ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በሰላምታ መጽሐፉ ላይ መጽሐፉ፦ "ኀይመተ አብርሃም አብ ሰላም ለኪ፤
ዘኮንኪ ከመ ተድባብ ሰላም ለኪ"
(እንደ ጥላ የኾንሽ የአባት አብርሃም ድንኳን ሰላምታ ይገባሻል) በማለት አመስግኗታል፡፡

❖ ይኽ አብርሃም የተቀበለውን የተስፋ ቃል ሊቃውንት ሲተረጒሙት "ኦ አኃውየ በይነ መኑ እንከ ዘይቤ እግዚአብሔር ለአብርሃም አመ ከመ ዮም እገብእ ኀቤከ አኮኑ እግዝእትነ ማርያም ይእቲ ዘወፅአት እምነ ሥርው ለአዳም ..." (ወንድሞቼ ሆይ እግዚአብሔር አብርሃምን እንደዛሬው ኹሉ ወደአንተ ተመልሼ እመጣለኍ ያለው ስለማን ይመስላችኋል? ከአዳም ሥር ወጥታ፤ ከኖኅ አብራክ ተገኝታ፤ ወደ አብርሃም አብራክ ልትከፈል፤ ሥላሴ በአብርሃም ቤት በእንግድነት ተገኝተው፤ ከአብርሃም ዘር ከእመቤታችን