Get Mystery Box with random crypto!

ዘጸውአ ስመከ መድኃኔ ዓለም ሆይ፤ ስምህን የጠራ መታሰቢያህንም ያደረገ እሱ በዚያ በቁርጥ የፍርድ | ዝክረ ቅዱሳን ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

ዘጸውአ ስመከ

መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ስምህን የጠራ መታሰቢያህንም ያደረገ እሱ በዚያ በቁርጥ የፍርድ ቀን ከንቱ ሁኖ አይቀርም።

ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ቅድመ ዓለም የነበርክ ዛሬም ያለህ ለዘለዓለሙም ጸንተህ የምትኖር አምላክ ስትሆን የታሠሩ አገልጋዮችህን አንተ ታስረህ ፈታሃቸው በሞትህም ሞተህም የሞቱትን ወገኖችህን አስነሳሃቸው።

ለኀጡአ ምግባር

መድኃኔ ዓለም ሆይ፤
ሃይማኖት ስንዃ ቢኖረኝ በጎ ምግባር የሌለኝ አነስተኛው አገልጋይ ማደሪያ ቤት መኖሪያ ቦታየ ከቅዱሳኖችህ ጋር ይሆን ዘንድ ፈቃድህ ይሁን አቤቱ።
ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ፤
ከከንቱ ሞት አድነኝ።ሁሉ ከንቱ ነው። የዚህ ዓለም ንብረት የከንቱ ከንቱ ነው። ሁሉም ኃላፊ ጠፊ ነውና።

ስብሐት ለከ

አቤቱ በፍጥረቱ ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ምስጋና ይገባል። አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ የምትሆናቸው ለአንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።

አቤቱ ነፍስና ስጋን አዋህደህ በምግባር ሃይማኖት አጽንተህ የምታከብራቸው ለአንተ ለመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል።

አቤቱ በመንግስትህ ሽረት በህልውናህ ሞት ኀልፈት የሌለብህ ለአንተ ለንጉሥ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል አቤቱ የቅዱስ አብ አካላዊ ቃል ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ሆይ ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባል ለዘላለሙ አሜን።