Get Mystery Box with random crypto!

'የዛሬዋ ለሊት ለይለተል  ቀድር ነበረች!! “እንዲህ ብለው ለሚያወሩ ሰዎች ጆሮ አትስጥ።ምክንያቱ | 🌙 ዝክረ ረመዳን مجالس شهر رمضان

"የዛሬዋ ለሊት ለይለተል  ቀድር ነበረች!!

“እንዲህ ብለው ለሚያወሩ ሰዎች ጆሮ አትስጥ።ምክንያቱም በኢባዳህ ላይ እንዳትቀጥልና እንድትቋረጥ የሚያደርግ ንግግር ነውና።ለይለተል ቀድር በዚህ ለሊት ነበር ብሎ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ የቂን(እርግጠኛ እንድትሆን የሚያደርግ ነገር )  የለም፣ባይሆን በነዚህ አስርቱ የመጨረሻ ቀናት ውስጥ ሳያቋርጥ ሁሉንም ለሊት በኢባዳ ጥረት ያደረገ በእርግጠኝነት ለይለተል ቀድርን ያገኛል።
ሸይኽ ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦
"የመጨረሻዎቹ የረመዳን አስርቱ ቀናትን በሰላት ያሳለፈ ለይለተል ቀድርን አግኝቷል ብለን ድምዳሜ ላይ መድረስ እንችላለን ።"

【ፈታዋ ኑሩን አላ ደርብ  (161)】


https://t.me/sultan_54