Get Mystery Box with random crypto!

እናቱ የሞተችበትና እናቱ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል እንዳሉት እንዳይሆን ብዬ እንጂ አልበላም | ዝንቅ መዝናኛ

እናቱ የሞተችበትና እናቱ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል እንዳሉት እንዳይሆን ብዬ እንጂ አልበላም አልጠጣም ብዬ የገዟኋትን ዉድ ስልክ በህዝብ ፊት ተበልቻለሁ። ድሮ ድሮ ሌባ ሲገኝ አላፊ አግዳሚዉ በሞላ ነግ በኔ ነዉ እያለ አሳዶ ይዞ በእርግጫ እያለ ነበር የሚያልፈዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን የቀድሞ ባህሉን እንደተወ የገባኝ ቀምቶኝ ሲሮጥ እያየ ሌባዉን ትቶ እኔን ለማፅናናት ከንፈሩን እየመጠጠ ሲቀርበኝ ነዉ ተበላሽተናልኮ ጎበዝ! እናንተ ሰፈርስ ሌባ እንዴት እያደረጋችሁ ነዉ? ባይ ዘ ዌይ ይሄ ኑሮ ዉድነትና ህገ ወጥነት በዚህ ከቀጠለ ገና ኩላሊት እንሰረቃለን።