Get Mystery Box with random crypto!

ዛሬ የአፍሪካ ቀን ሆኖ አልፏል። እአአ 1963 May 25 የአፍሪካ ህብረት መመስረቱን ተከትሎ የዛ | ዝንቅ መዝናኛ

ዛሬ የአፍሪካ ቀን ሆኖ አልፏል። እአአ 1963 May 25 የአፍሪካ ህብረት መመስረቱን ተከትሎ የዛሬዉ እለት የአፍሪካ ህብረት ቀን ወይም የአፍሪካ ቀን ተብሎ በየአመቱ ይከበራል። ከ2100 በላይ ቋንቋ ያለባት፣ ከ3000 በላይ የተለያዩ ጎሳዎች የሚኖሩባት ባለ ብዙ ቀለምና ባለ ብዙ ባህል መገኛ አፍሪካችን እጅግ ዉብ ናት። ልዩ ልዩ ምግቦች፣ እጅግ ዉብ ሙዚቃ፣ አዝናኝ ዳንስ፣ ማራኪ የቆዳ ቀለማችን፣ የተከበሩ ማዕድኖቻችን፣ የተፈጥሮ ዉበቱ ወዘተ ሁሉ አፍሪካን በአለማችን እጅግ ልዩ ያደርጋታል።

ይህንን ልዩ የሆነዉን የአፍሪካን ቀን በማስመልከት የተካሄደዉን የአፍሪካ ተወዳጅ ወጣት ዘፋኞች የተሳተፉበትን እጅግ ዉብ የዩትዩብ ኮንሰርት ያላያችሁ ከታች ባለዉ ሊንክ እያያችሁ ተፍታቱበት።

One Love! One Africa!