Get Mystery Box with random crypto!

..........I saw Jesus and The False Messiah/በጉንና አየሁት !! | The words of eternal life

..........I saw Jesus and The False Messiah/በጉንና አየሁት !!

ከጥቂት ቀናት በፊት ነበር እግዚአብሔር አይኖቼን ከፍቶአቸው ከዘመናት በፊት የነበረውን ታላቁን የMarthin Luther King ዘመን Reformation በBlack and White ያሳየኝ ነበር። ስለነበረው እንቅስቃሴ ፤ እናም ስለነበረው ተቃውሞ እንድሁም ስለነበረው ስለ ክርስቶስ ጥዑም ስብከቶች ፤ እንድሁም በዚህ በክርስቶስ ፍቅር ስብከት ሰለባ የሆኑ ከልባቸው ኢየሱስን የወደዱትን ህዝቦቸሰ አየኋቸው። ምንኛ እድግ ግሩምና ድንቅ ምያስቀና ዜማ ያለው ህይወት ነው የሚኖሩት !? ሁሉምያስቀናሉ !!

ነገር ግን ከምነው ቅጽበት እንደሆነ ባላውቅም እራሴን ከበጉ ፊትና ከኢየሱስ አጠገብ እራሴን በሰማይ አየሁት። ኢየሱስ ከጎኔ ይቆማል ፤ ከፊታችንም አንድ በግ በዙፋን ልክ ነበር የቆመው። ዙፋን ሳለው ግን ቆሟል ፤ ኢየሱስም በሀሳብ ልውውጥ እንድመለከተው ያዘኝ ነበር። አየሁት ከበላዩ በጉ ልጫንለት ያለ ልጠልቅለት ያለ አክሊል አለው። አክልሉን ይጠብቀዋል። ወዲያው እያየሁት አክሊል ጠለቀለት ግና አክሊሉ ሲጠልቅለት በጉ መልኩን ይቀይራል። ከአክልሉ መጫን የተነሳ ትክክለኛው መልኩ ይገለጥና የHindiዋ ጣዖት Krishnaን መስሎ ይገለጣል። 6 እጆችም ተገለጡበት። ይህም ሁሉ የተገለጠው በአክሊሉ መጥለቅ መንሥኤ ነው።

አጠገቤ የቆመውም ኢየሱስ አንገቱን ይነቀንቅና እንደቀድሞው በሀሳብ ልውውጥ ንግግር "ይህ የእኔ መልክ ምሳሌ አይደለም" ይላል አንገቱን በመነቅነቅ በሀዘን።

ከዚያም ሌላ በግ አየን። በጉ ትንሽዬ ጠቦት እናም በደስታ የሚፍለቀለቅ ፤ የሚጠባበቀው ተስፋ ያለው አይነት ደስ የሚል ጠቦት ነው። ዙፋን አለው ግን ይቆማል። እርሱም እንደቀድሞው አክሊል ከበላዩ ሊጠልቅለት የተዘጋጀ ነው። አክሊሉ በገድሉ የተወለደ ከውስጡ ከከበሩ ድንጋዮች ብቻ የሚወጣ አይነት የብርሃን ነጸብራቅ ያለው ፤ እጅግ ያማረ ነበር። ይህ ጠቦት በግም ከበላዩ ይህን አክሊል እንደሚገባው እያሰበ ፤ ስለተገባውም በፍጹም እርጋታ ይጠብቀዋል።

በመጨረሻም ለበጉ ይህ አክሊል እያየሁት ተጫነለት። በጉ እጅግ ተደሰተ ፤ ተፍለቀለቀ ፤ ደስታው ከተስፋ ወደ ፍጹምነት ገባ። ኢየሱስም ከጎኔ ቆሞ "ትክክለኛው የእኔ መልክ ይህ ነው። " አለኝ። ፈገግም አለ !!

እኔም በውስጤ ይህ ቃል ትዝ አለኝ !!
“ሰባተኛው መልአክ ነፋ፤ በሰማይም፦ የዓለም መንግሥት ለጌታችንና ለእርሱ ለክርስቶስ ሆነች፥ ለዘላለምም እስከ ዘላለም ይነግሣል የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ሆኑ።”
— ራእይ 11፥15

ሀሌሉያ !! ከእውነተኛው መሢህና መሥዋዕታችን ጋር እንነግሳለን።

#Be_aware of The False Messiah !!
#ትልቁ የመጨረሻው ዘመን ችግር Satanism ፤ Lesbian, Gay አይምሰላችሁ ሐሰተኛው ክርስቶስ እንጅ !! በቻለው አቅም እራሱን በመሢህአችን ይመስላል። ነገር ግን ሰዓቱ ሲያልቅ ክፋቱም ይገለጣል። “ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው፥ በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።”
— ራእይ 13፥5
42ወር/12ወር(1yr)=3.5 አመት

ኢየሱስም 3.6/3.5 አመት ነበር በምድር አገልግሎት የተገለጠው እርሱም ለ3.5አመት ይገለጣል። በቻለው በመሢሀችን ራሱን ይመስላል። ነገር ግን እርሱ ድባቅ ይመታዋል።
አብረነው እንነግሣለን ከመሢሀችን ጋር።
በእግዚአብሔር ጥበብ ልቃችሁ እንድትገኙ እጸልይላቿለሁኝ።
Seer Enbakom
@Christ_Sermons