Get Mystery Box with random crypto!

ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል

የቴሌግራም ቻናል አርማ zhohitebirhan — ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል
የቴሌግራም ቻናል አርማ zhohitebirhan — ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል
የሰርጥ አድራሻ: @zhohitebirhan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 872
የሰርጥ መግለጫ

የቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት ማርያም ሰንበት ት/ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገጽ ነው ::
በዚህም ገጽ ላይ መንፈሳዊ ጹሁፎች ፣ የቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ መረጃዎች ፣ መልእክቶች እና ሌሎችም ይቀርቡበታል።

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-30 09:14:46 እንኳን አደረሳችሁ እንዳለፈው ዓመት ሁሉ በአሁኑም ለአዲስ ዓመት ለአንድ ቤተሰብ እንኳን አደረስዎ የምንሰጠው
፩, ሽንኩርት 4ኪግ * 50 =200 ብር
፪, እንቁላል 12 * 7.50 = 90 ብር
፫, ዘይት 2ሊ * 190 = 380 ብር
፬, በእጅ የሚሰጥ = 500 ብር              
            ጠቅላላ= 1170 ብር
ይሄ ነውና የቻላችሁትን መለገስ በግልም በቡድንም ይቻላል።

ስለምታደርጉት ልገሳ እግዚአብሔር ይስጥልን።
ለበለጠ መረጃ 0922996081

Acc-5187178520011 ዳሽን ባንክ
ፋሲካ ኃይሉ ወ/ሥላሴ እና ምህረት በላይ ንጉሴ
387 viewsedited  06:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 12:15:06
678 views09:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 08:22:43 ከዘመነ ትንሣኤ እስከ በዓለ ፶ (ጰራቅሊጦስ) ድረስ የክርስቲያኖች ሁሉ ሰላምታ

"ክርስቶስ ተንሥኣ እሙታን፣
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፣
አሰሮ ለሰይጣን፣
አግዓዞ ለአዳም፣
ሰላም እምይእዜሰ፣
ኮነ ፍስሐ ወሰላም" የሚል ሲሆን ፤

ከእመቤታችን ትንሣኤ ነሐሴ ፲፮ እስከ ነሐሴ ፳፩ ድረስ ደግሞ የክርስቲያኖች ሰላምታ

"#ተንሥኣት #እሙታን #ማርያም #ድንግል፣
#ከመትንሣኤ #ወልዳ #ዘልዑል።" የሚል ይሆናልና እንልመደው።

እንኳን አደረሰን

https://t.me/zhohitebirhan
ለሌሎች ያጋሩ
376 viewsedited  05:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 14:03:05 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ነሐሴ ፲፮ ❖

✞✞✞ እንኩዋን ለእመቤታችን
#ቅድስት_ድንግል_ማርያም ዓመታዊ የትንሳኤና የዕርገት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

+"+ # ዕርገተ_ድንግል_ማርያም +"+

=>ይሕች ዕለት እጅጉን ታላቅና ክብርት ናት:: ምክንያቱም
የድንግል ማርያም ሥጋዋ ተነስቶ ዐርጐባታልና:: ድንግል
እመቤታችን ተነሳች: ዐረገች ስንል እንደ እንግዳ ደርሶ:
እንደ ውሃ ፈሶ: ወይም በአጋጣሚ የተደረገ አይደለም::
ጥንቱን በአምላክ ልቡና ታስቦ: ሁዋላም ትንቢት
ተነግሮለት ነው::

¤ታሪኩ: ነገሩ: ምሥጢሩስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቅድመ ዓለም
በአምላክ ልቡና ታስባ ትኖር ነበር:: ከነገር ሁሉ በፊት
እግዚአብሔር እናቱን ያውቃት ነበር::

+"+ የድንግል ማርያም ሐረገ ትውልድ +"+

*ከአዳም በሴት
*ከያሬድ በሔኖክ
*ከኖኅ በሴም
*ከአብርሃም በይስሐቅ
*ከያዕቆብ በይሁዳና በሌዊ
*ከይሁዳ በእሴይ: በዳዊት: በሰሎሞንና በሕዝቅያስ
ወርዳ ከኢያቄም ትደርሳለች::

¤ከሌዊ ደግሞ በአሮን በአልዓዛር: ፊንሐስ:
ቴክታና በጥሪቃ አድርጋ ከሐና ትደርሳለች::

¤አባታችን አዳም ከገነት በወጣ በ5,485 ዓመት
ወላዲተ አምላክ ንጽሕና ሳይጐድልባት: ኃጢአት
ሳያገኛት: ጥንተ አብሶ ሳይደርስባት ከደጋጉ
ኢያቄምወሐና ትወለዳለች:: (ኢሳ. 1:9, መኃ. 4:7)
"ወኢረኩሰት በምንትኒ እምዘፈጠራ" እንዳለ::
(ቅዱስ ቴዎዶጦስ ዘዕንቆራ)

¤ከዚያም ከእናት ከአባቷ ቤት ለ3 ዓመታት ቆይታ ወደ
ቤተ መቅደስ ትገባለች:: በቤተ መቅደስም ለ12
ዓመታት ፈጣሪዋን እግዚአብሔርን እያመሰገነችና
እያገለገለች: እርሷን ደግሞ መላእክተ ብርሃን
እያገለገሏት: ሕብስት ሰማያዊ: ጽዋዕ ሰማያዊ
እየመገቧት ኑራለች:: 15 ዓመት በሞላት ጊዜ ጻድቅ
አረጋዊ ዮሴፍ ያገለግላት ዘንድ ወደ ቤቱ ወሰዳት::

¤በዚያም መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ዜና
ድኅነትን ነግሯት አካላዊ ቃልን በማሕጸንዋ ጸነሰችው::
ነደ እሳትን ተሸከመችው: ቻለችው:: "ጾርኪ ዘኢይትጸወር:
ወአግመርኪ ዘኢይትገመር" እንዳለ::
(ሊቁ ቅዱስ ኤፍሬም ለብሐዊ)

¤ወልደ እግዚአብሔርን ለ9 ወራት ከ5 ቀናት ጸንሳ:
እንበለ ተፈትሆ (በድንግልና) ወለደችው:: (ኢሳ. 7:14)
"#ኢየሱስ" ብላ ስም አውጥታለት በናዝሬት ገሊላ ለ2
ዓመታት ቆዩ::

¤አርዌ ሔሮድስ "እገድላለሁ" ብሎ በተሳበት ወቅትም
ልጇን አዝላ በረሃብ እና በጥም: በላበትና በድካም:
በዕንባና በኃዘን ለ3 ዓመታት ከ6 ወራት ከገሊላ እስከ
#ኢትዮዽያ ተሰዳለች:: ልጇ ጌታችን 5 ዓመት ከ6 ወር
ሲሆነው: ለርሷ ለድንግል ደግሞ 21 ዓመት ከ3 ወር
ሲሆናት ወደ ናዝሬት ተመለሱ::

¤በናዝሬትም ለ24 ዓመታት ከ6 ወራት ልጇን ክርስቶስን
እያሳደገች: ነዳያንን እያሰበች ኑራለች::

እርሷ 45 ዓመት: ልጇ 30 ዓመት ሲሆናቸው ጌታችን
ተጠምቆ በጉባኤ ትምሕርት: ተአምራት ጀመረ:: ለ3
ዓመታት ከ3 ወራትም ከዋለበት እየዋለች: ካደረበትም
እያደረች ትምሕርቱን ሰማች::

¤የማዳን ቀኑ ደርሶ ልጇ ክርስቶስ ሲሰቀልም
የመጨረሻውን ፍጹም ሐዘን አስተናገደች:: አንጀቷ በኃዘን
ተቃጠለ:: በነፍሷም ሰይፍ አለፈ:: (ሉቃ. 2:35) ጌታ
በተነሳ ጊዜም ከፍጥረት ሁሉ ቀድማ ትንሳኤውን አየች::
ለ40 ቀናትም ሳትለይ ከልጇ ጋር ቆየች::

¤ከልጇ ዕርገት በሁዋላ በጽርሐ ጽዮን ሐዋርያትን
ሰብስባ ለጸጋ መንፈስ ቅዱስ አበቃች:: በጽርሐ ጽዮን
ከአደራ ልጇ ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ለ15 ዓመታት ኖረች::
በእነዚህ ዓመታት ሥራ ሳትፈታ ስለ ኃጥአን ስትማልድ:
ቃል ኪዳንን ከልጇ ስትቀበል: ሐዋርያትን ስታጽናና:
ምሥጢርም ስትገልጽላቸው ኑራለች::

¤ዕድሜዋ 64 በደረሰ ጊዜ ጥር 21 ቀን መድኃኒታችን
አእላፍ ቅዱሳንን አስከትሎ መጣ:: ኢየሩሳሌምን
ጨነቃት:: አካባቢውም በፈውስ ተሞላ:: በዓለም ላይም
በጐ መዓዛ ወረደ:: እመ ብርሃን ለፍጡር ከዚያ በፊት
ባልተደረገ: ለዘለዓለምም ለማንም በማይደረግ ሞገስ:
ክብርና ተአምራት ዐረፈች:: ሞቷ ብዙዎችን አስደንቁአል::
"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ:
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ" እንዲል::

¤ከዚህ በሁዋላ መላእክት እየዘመሩ: ሐዋርያቱም
እያለቀሱ ወደ ጌቴሴማኒ: በአጐበር ሥጋዋን ጋርደው
ወሰዱ:: ይሕንን ሊቃውንት:-
"ሐራ ሰማይ ብዙኃን እለ አልቦሙ ሐሳበ:
እንዘ ይዜምሩ ቅድሜኪ ወመንገለ ድኅሬኪ ካዕበ:
ማርያም ሞትኪ ይመስል ከብካበ" ሲሉ ይገልጡታል::

¤በወቅቱ ግን አይሁድ በክፋት ሥጋዋን እናቃጥል ስላሉ
ቅዱስ ገብርኤል (ጠባቂ መልአክ ነው) እነርሱን ቀጥቶ
እርሷን ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር ወስዶ በዕጸ ሕይወት ሥር
አኑሯታል::

በዚያም መላእክት እያመሰገኗት ለ205 ቀናት
ቆይታለች::

¤ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ ለሐዋርያቱ ክብረ ድንግልን
ቢነግራቸው በጐ ቅንአት ቀንተው በነሐሴ 1 ሱባኤ
ጀመሩ:: 2ኛው ሱባኤ ሲጠናቀቅም ጌታ የድንግል
ማርያምን ንጹሕ ሥጋ ሰጣቸው:: እየዘመሩም
#በጌሴማኒ ቀብረዋታል::

¤በ3ኛው ቀን (ነሐሴ 16) እንደ ልጇ ባለ ትንሳኤ
ተነስታ ዐርጋለች:: ትንሳኤዋንና ዕርገቷንም ደጉ ሐዋርያ
ቅዱስ ቶማስ አይቶ: መግነዟን ተቀብሏል:: ሐዋርያቱም
መግነዟን ለበረከት ተካፍለው: እንደ ገና በዓመቱ ነሐሴ
1 ቀን ሱባኤ ገቡ::

¤ለ2 ሳምንታት ቆይተው: በዚህች ቀንም ሁሉንም ወደ
ሰማይ አወጣቸው:: በፍጡር አንደበት ተከናውኖ
የማይነገር ተድላ: ደስታና ምሥጢርንም አዩ:: ጌታ ራሱ
ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የበዓሉን ቃል ኪዳን
ሰምተው: ከድንግል ተባርከው ወደ ደብረ ዘይት
ተመልሰዋል::

=>ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና #እመቤታችን:
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኚልን:: አእምሮውን:
ለብዎውን: ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::

ምንጭ፡ ዝክረ ቅዱሳን
584 viewsedited  11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:23:18 ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል pinned «✞✞✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞ ✞✞✞ ደብረ ታቦር ✞✞✞ =>ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- +አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች…»
06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 09:23:12 ✞✞✞ እንኩዋን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞

✞✞✞ ደብረ ታቦር ✞✞✞

=>ደብረ ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው:: ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-

+አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ: ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር:: በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው: አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም::

+ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም: በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር:: በርግጥ ያንን ነደ እሳት: ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም::

+ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል:: እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል:: ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:-
1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12)
2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና)

3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም
4.አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ
5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት
6.ተራራውን ለመቀደስ
7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው::

+ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር:: እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት::

+ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ:: የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው:: (ማቴ. 16:13)

+መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው:: ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ:: እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ::

+በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ: ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ:: "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል:: ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ::

+በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ:: አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት::

+ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም:: መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል::

+በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው:: በዚህም 3 ዳስ እንሥራ:: አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል::

+ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል:: ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው::

+እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው:: አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ::

+ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር:: (ማቴ. ማር. ሉቃ. )

+በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያት ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል::

+ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል:: ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.)
ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:-

"ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ:
ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ:
አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ:
መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ:
ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::"

=>ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን:: ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን::

=>+"+ ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል::
ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው::
እጅህ በረታች: ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች:: +"+ (መዝ. 88:12)

=>+"+ ከስድስት ቀንም በሁዋላ ጌታ ኢየሱስ ዼጥሮስን: ያዕቆብንና ወንድሙን ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው:: በፊታቸውም ተለወጠ:: ፊቱም እንደ ፀሐይ አበራ:: ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ:: እነሆም ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው:: ዼጥሮስም መልሶ ጌታ ኢየሱስን:- "ጌታ ሆይ! በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው:: ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ: አንዱን ለአንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ" አለ:: እርሱም ገና ሲናገር እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው:: እነሆም ከደመናው:- "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው: እርሱን ስሙት" የሚል ድምጽ መጣ:: ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ:: +"+ (ማቴ. 17:1)

✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞

ምንጭ፦ ዝክረ ቅዱሳን
608 views06:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 01:37:24
የእመቤታችንን ዕርገት በማስመልከት የተዘጋጀ ጉባኤ
722 viewsedited  22:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:09:33
952 views18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 17:24:11 ለኆኅተ ብርሃን ሰ/ት/ቤት አባላት
ከክፍል ወደ ክፍል መቀየር የምትፈልጉ አባላት ከዛሬ ጀምሮ እስከ ነሐሴ 30/2014 ድረስ በአባላት ክትትል እና ውጭ ጉዳይ ክፍል ቢሮ በመገኘት ፎርም መሙላት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
አባላት ክትትል እና ውጭ ጉዳይ ክፍል
628 views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-12 18:45:29 ዘኆኅተ ብርሃን ሰንበት ት/ቤት (official) ቻናል pinned «††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ††† †††በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ቁጽረታ (ጽንሰታ) ለማርያም ††† ††† ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት…»
15:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ