Get Mystery Box with random crypto!

'አንዳንድ ትዝታ አለ' ዝምታችን ከዝምታ ገዝፎ በአረምሞ በተዘጋንበት ጊዜ ከዕዝነ ልቦናችን በኩል | ኢትዮ_ቅምሻ💚💛❤️

"አንዳንድ ትዝታ አለ"

ዝምታችን ከዝምታ ገዝፎ በአረምሞ በተዘጋንበት ጊዜ ከዕዝነ ልቦናችን በኩል <<ኡኡኡ>>ብሎ የሚጮህ በዝግታ ካሳለፍነው የእድሜ ዘመን ቅፅበቶቻችን ከሽርፍራፊ የልጅነት ምስላችን በልጦ አልባችን ጥጋጥግ ካንጠለጠልነው ተናፋቂ ትዝታዎች መሃል ምናለ በደገምነው እያልን የምንመኘው ከትላንት ትዝታዎቻችን ጋር ባንቀላፋን ቁጥር ሳንሰለች ደጋግመን የምንኖረው አንዳንድ ትዝታ አለ። እንደ ወይን እያደር ጣዕሙ የሚጨምር። በእንባ በተሞሸርንበት ጊዜ እንኳን'በሀዘን ወህኒ ተወርውረን መረሳት፣ ክፉ አጋጣሚ ፊትለፊታችን ሲጋረጥ የመኖር ጣዕም ሲጎመዝዝ በእቅፉ የሚያስጠልለን አንዳንድ ትዝታ አለ። በዘመን መጎስቆል ባረመምንበት ጊዜ እንደ አዲስ የሚወልደን የማያረጅ የእድሜያችን ሞቃት ምዕራፍ

ያብስራ(ደብተራው)

@ZHabbesha @ZHabbesha