Get Mystery Box with random crypto!

በ2023 በአለም ላይ ለጎብኝዎች በፍጹም ከማይመከሩና እጅግ አደገኛ ከተባሉ 10 ሀገራት ውስጥ ኢት | ዘሪሁን ገሠሠ

በ2023 በአለም ላይ ለጎብኝዎች በፍጹም ከማይመከሩና እጅግ አደገኛ ከተባሉ 10 ሀገራት ውስጥ ኢትዮጵያ አንደኛዋ መሆኗን ያውቃሉን ?

በየአመቱ የሀገራትን የሰላምና ደህንነት ሁኔታ ተገምግሞ ደረጃ በሚሰጥበት The Global Peace Index እ.ኤ.አ በ2023 በተቀመጡ መመዘኛ መስፈርቶች መሠረት የ163 ሀገራትን ደረጃ ተለይቶ ይፋ ተደርጓል።

በዚህ የደረጃ ሠንጠረዥ መሠረት ከግርጌ ያሉት አስር ሀገራት << በአለም ላይ ለጉዞና ለጎብኚዎች ፍፁም የማይመከሩ አደገኛ ሀገራት >> ተብለው ተቀምጠዋል። በዚህ መሠረት ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ163 ሀገራት በ2.80 የGPI ነጥብ 151ኛ ደረጃ ላይ በመቀመጥና ከአፍሪካ 8ተኛ ተራ ቁጥር ላይ ሰፍራ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተች ሀገር ሆናለች።

ከዚህ ቀደም የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት በበኩሉ ፤ << ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ደረጃ-3/level 3 የጉዞ አማራጭ ሀገር ነች>> ሲል መመደቡ የሚታወስ ነው። ይህ ማለት << የሀገሪቱ ሁኔታ እስከሚስተካከል ድረስ ፍፁም ለጉዞና ለጉብኝት አትመከርም! >> እንደማለት ነው።

በGPI የደረጃ ሰንጠረዥ ላይ ፣ በሀገሪቱ ያሉ የሽብርና የእገታ ወንጀሎች መስፋፋት ፣ የእርስበርስ ግጭቶች ፣ ያልተረጋጋና ረፍት አልባ ህዝብ መኖሩ ፣ የወንጀል ድርጊቶች እየተበራከተ መምጣት ፣ በጎረቤት ሀገራት ድንበሮች አካባቢ ያሉ የደህንነት ስጋቶችና በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ችግሮች በቀጠና ተለይተው በዝርዝር ተቀምጠዋል።

በአለም ላይ ለጎብኚዎች መረጃ የሚሰጡ ድህረ-ገፆችና ሌሎች ሚዲያዎች ፣ አስጎብኚ ድርጅቶች ፣ የሀገራት ኤምባሲዎች ወዘተረፈ <<...According to GPI ranking, Ethiopia is considered one of the most dangerous countries in Africa. >> እያሉ ሲያስተጋቡ መመልከት ልብን ቢያሳምምም ፣ እውነታው ግን ይኸው ነው!

በሁለንተናዊ መልኩ ፣ ሁለንተናዊ በጎ ገፅታዋንና ክብሯን እያጣች ያለች ሀገር-ኢትዮጵያ!

Fact check links

https://travellersworldwide.com/most-dangerous-countries-in-africa/

https://reliefweb.int/report/world/global-peace-index-2023

https://www.gfmag.com/global-data/non-economic-data/most-peaceful-countries