Get Mystery Box with random crypto!

የዝሆኖቹ የቀይ ባህር ፖለቲካዊ ትርምስና የቅጥረኛ ተዋጊዎቹ ጉዳይ! ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ፣ አ | ዘሪሁን ገሠሠ

የዝሆኖቹ የቀይ ባህር ፖለቲካዊ ትርምስና የቅጥረኛ ተዋጊዎቹ ጉዳይ!

ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ ፣ አብይና ትህነግ ተፋቅረው ፥ አብይ ''በነፍሴ ድረሺልኝ!'' ያላትን ኤርትራ ሊወጉ ይችላሉ! የውክልና ጦርነቱ ምስራቅ አፍሪካን ወደትርምስ ቀጠና ይወስዳታል ብዬ ነበር!

''አማራውን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ባንዲራ እያሳየን የአሰብ ወደብን ለማስመለስ ነው ካልነው ከጎናችን እናሰልፈዋለን!'' የሚል አደገኛ የአፍ ወለምታ በመድረክ ተነግሮ እንደነበርም ጭምር ምንጮቼን ጠቅሼ አጋርቼ ነበር።

ይኸው አሁን በሁለቱም ጎራ የውክልና ጦርነት ዝግጅቱ መጀመሩን እየተመለከትን ነው። ኤርትራ ድንበሯን ጠርቅማ ከዘጋች ወራት ተቆጥረዋል። የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካዮች ወከባና ክትትል በዝቶብናል እያሉ እዬዬውን አቅልጠውታል። ወዲህ ''ለቀይ ባህር በቀይ ባህር እንሞታለን!'' የምትል አስቂኝ ፕሮፓጋንዳ ብቅ ብቅ ማለት ጀምራለች። የሸለመጥማጡ አብይ ሁኔታ ያላማራት ኤርትራ ከህወሓት ጋር በተደረገው ጦርነት በነበራት አስተዋፅኦና በስምምነቷ መሠረት ለተኮሰችው እያንዳንዷ ጥይት ፣ ላወጣችው ሎጅስቲክና ደመወዝ ፣ ለከፈለችው ህይወት ሁሉ ሂሳብ አስልታ የጠየቀችው ገና የትህነግ ዳግም ወረራ ሊጀማምር አካባቢ ነበር። አብይ ይህን መክፈል ባለመቻሉ በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ድብቅ ድርድር ተደርጎም ሳይቋጭ በነበረበት መክረሙ አይዘነጋም። ኤርትራ ከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትኬት ሽያጭ የሰበሰበውን 2 ሚሊየን ዶላር ሳይቀር እንዳይንቀሳቀስ ያገደችው ''ይህ ሁሉ እዳ ሳይከፈለኝ!'' በማለት ይመስላል።

እጅ ጠምዛዦቹ ምዕራባውያን ከሳምንታት በፊት የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፣ የምዕራባውያኑ ቁጥር አንድ ባላንጣ በሆኑት ሩሲያና ቻይና ያደረጉትን ይፋዊ ጉብኝት ተከትሎ ፣ የምስራቅ አፍሪካ ቅጥረኛ ተዋጊዎቻቸው (አብይና ትህነግን ጨምሮ ሌሎቹም) ይቺን ቀንድ ላይ ያለች ስትራቴጂክ ሀገር በቶሎ እንዳልነበረች አድርገው እንዲያጠፏት የተጣደፉም ይመስላል።

የቀይ ባህር ፖለቲካ ምዕራባውያኑንና ተቃራኒዎቻቸውን ለዘመናት የሚያራኩት ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ ግልፅ ነው። ሩሳያና ቻይናን ጨምሮ የምዕራባውያኑ ባላንጣ ሀገራት በቀይ ባህር ፖለቲካው ውስጥ ድርሻቸውና የበላይነታቸው እየጎላ የመጣው በዚች በኢሳያስ ሀገር ሳቢያ እንደሆነ ያምናሉ። ስለዚህ ይቺን ሀገር ድራሿን ካላጠፉ የሚተኙ አይመስልም።

አብይ ጀነራሎቹን በሙሉ ሰብስቦ እየዶለተ ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ወታደራዊ ዝግጅትም ገዘፍ ያለና በሎጂስቲክ የተጠናከረ መሆኑን ምንጮች እየገለፁ ይገኛሉ።

በዚህ መሀል የምዕራባውያኑ ቅጥረኛ ተዋጊ ኢትዮጵያውያንን በተለይም አዲስአበባ ላይ መኖር የተሳነውን አማራ ለመቀስቀስ '' ለቀይ ባህር በቀይ ባህር እንሙት!'' የሚል ጭዌ መሆኑ ያስቃል።

ለሁሉም ጊዜ መልስ አለው! ኢመቻችሁ!