Get Mystery Box with random crypto!

ማንኛችንም አሸናፊና ተራፊ ወደማንሆንበት ፥ የእልቂት ውቅያኖስ እየተዘፈቅን ነው! ከስልጣኔ ማማ | ዘሪሁን ገሠሠ

ማንኛችንም አሸናፊና ተራፊ ወደማንሆንበት ፥ የእልቂት ውቅያኖስ እየተዘፈቅን ነው!

ከስልጣኔ ማማ ላይ የተቆናጠጡት ጀርመኖች ያንን የፋሽስታዊ ስርአት የዘር ፍጅት " የምናፍርበት ታሪካችን!" ብለው በሙዚየም ለአለም መማሪያነት ያስጎበኛሉ፡፡

ዛሬ ላይ " ሁቱና ቱትሲ" ተባብለው ለመጠራራት ሁሉ የሚፈሩት ሩዋንዳውያን በቀናት ሚሊየኖችን ጭጭ ምጭጭ ያደረገውን አስከፊ ጭፍጨፋ " አይደለም እንደዚያ አይነቱ ጥቁር ታሪክ ሊደገምና ፥ የግለሰቦች ፀብ እንኳ መስማት አንሻም!" ሲሉ ከትናንት እልቂት ተምረው ፥ በጥሩ ሀገራዊ የእድገትና የሰላም መንገድ ላይ እየተጓዙ ይገኛሉ!

እኛ ግን ላለፉት 5 አመታት ፍጅትና እልቂት እየተፈፀመ "በቃ!" ማለት ተስኖን ፥ ከሩዋንዳም ሆነ ከጀርመን ከፍ ባለ ደረጃ ፥ ወደፍጅት ውቅያኖስ መንደርደራችንን ቀጥለናል!

ላለፉት 5 አመታት በአብዛኛው የተፈጀውና እየተጨፈጨፈ ብሎም እየተፈናቀለ ያለው የአማራ ህዝብ ብቻ ቢሆንም ፥ እመኑኝ! ይህ ጭካኔና "ነግ በእኔ" የማያስብል የዝምታ መንገዳችን ፥ ማንኛችንንም ወደማያስተርፍ የእልቂት አዘቅት እያንደረደረን ነው!

"ልብ ያለው ፥ ልብ ይበል!"