Get Mystery Box with random crypto!

ተመለሱ(Return ye)-2 Osho comments on (Jesus of Nazareth ) ኢየሱስ | ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy

ተመለሱ(Return ye)-2
Osho comments on (Jesus of Nazareth )

ኢየሱስ እና ይሐንስ  "ተመለሱ (ተፀፀቱ)" ሲሉ እስካሁን ድረስ ከኖራችሁበት እና ከሆናችሁበት መላው መንገድ ተመለሱ ማለት ነው፡፡ ይህ ከአንድ ሰው ይቅርታ የመጠየቅ ጥያቄ አይደለም፡፡  "መፀፀት የሚለው ቃል ኦሪጅናል ትርጉሙ "መመለስ ነው፡፡ በአርመንኛ ኢየሱስ እና ዩሐንስ ቋንቋቸውን በመጠቀም "መፀፀት" ሲሉ "መመለስ" ማለታቸው ነው፡፡ እነርሱ "ወደ ምንጩ ወደ ኦሪጅናል ፍጥረታችሁ ተመለሱ" ነው የሚሏችሁ፡፡

እነርሱ እያሉዋችሁ ያሉት እንደ ዜኖች "ኦሪጅናል ፊታችሁን ፈልጉ" ነው...ይህ ነው ተፀፀቱ" የሚለው ትርጉም፡፡ ሁሉንም ጭንብሎቻቻሁን ጣሏቸው፡፡ ይህ በእናንተ እና በሌሎች መካከል ያለ ጥያቄ አይደለም ፡፡ ይህ በእናንተ እና በእግዚአብሄራችሁ መካከል ያለ ጥያቄ ነው ፡፡ "ተፀፀቱ" ማለት ሁሉንም ዓይነ - እርግቦቻችሁን በማስወገድ በኦሪጅናል ፊታችሁ እሱ እንደፈጠራችሁ ሆናችሁ በእግዚአብሄር ፊት ቁሙ ማለት ነው፡፡
ፊታችሁን ብቻ ሁኑ፡፡ እግዚአብሄር ትሆኑ ዘንዳ በሚፈልገው መንገድ ብቻ ሁኑ፡ ፡ ብቸኛ የሆነውን ፍጥረታችሁን ሁኑ፡፡ ወደ ኦሪጅናል ፊታችሁ ተመለሱ፡፡ ወደ ጥልቁ የፍጥረታችሁ ማዕከል ተመለሱ፡፡ መፀፀት መመለስ ነው፡፡ ይህ አንዱ እና ትልቁ መንፈሳዊ ምልሰት ነው፡፡

እነርሱ የሚሉት " ስታደርጉ የነበራችሁትን ለማየት ሞክሩ ፤ ለመረዳት ሞክሩ ፤ ወደ ውስጥ እና ውስጥ ተመልከቱ ፤ ወደ ዋናው ህልውናችሁ ፍጥረት ፣ ባህሪ ውስጥ ዝለቁ እናም ምን ስታደርጉ እንደነበረ ፣ ምን እንደሆናችሁ እዩ " ነው፡፡ ይህ የምትፀፀቱበትን አንድ የሆነ ነገር የመፈለግ ጥያቄ አይደለም፡፡
የምትፀፀቱት ስለ አንድ የተወሰነ ድርጊት ነው፡፡ ፀፀታችሁ ሁሌም የተወሰኑ ድርጊቶችን ያጣቅሳል፡፡ የኢየሡስ ፀፀት ስለተወሰኑ ድርጊቶች አይደለም፡፡ ይህ ኢየሱስ የሚለው መፀፀት (መመለስ) ስለ ፍጥረታችሁ ነው፡፡እናንተ የነበራችሁበት መንገድ ፍፁም የተሳሳተ ነበር፡፡ ምናልባትም አልተናደዳችሁ ይሆናል፡፡ እስካሁንም ግን የተሳሳታችሁ ሆናችኋል፡፡ ምናልባትም በጥላቻ የተሞላችሁ ላትሆኑ ትችሉ ይሆናል፡፡ እስካሁንም ግን የተሳሳታችሁ ነበራችሁ: ምናልባትም ብዙ ሃብት ላታከማቹ ትችሉ ይሆናል፡፡ እስካሁንም ግን የተሳሳታችሁ ናችሁ፡፡ "ይህ ምን አደረጋችሁ?" የሚለው ጥያቄ አይደለም፡፡ ይህ እንዴት ባለ መንገድ ሆናችሁ እንደነበር የሚለው ጥያቄ አይደለም፡፡ አንቀላፍታችሁ ነበር፡፡ ያልነቃችሁ ነበራችሁ፡፡ ከውስጣዊው ብርሃን ጋር አልኖራችሁም፡፡ የኖራችሁት በጨለማ ውስጥ ነው እንደ ማለት ነው።
አንድ ሰው ወደ መላው ፍጥረቱ መመለስ አለበት፡፡ ከዚያ በኋላ ብቻ ነው ሽግግር የሚቻለው

@Zephilosophy
@Zephilosophy