Get Mystery Box with random crypto!

' በ5 ወር 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን ተሻግረዋል ' - IOM እንደ ተመድ የስ | Mereja News Live

" በ5 ወር 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን ተሻግረዋል " - IOM

እንደ ተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ (IOM) ፤ ባለንበት በዚህ ዓመት 2022 (እኤአ) /በ5 ወር/ ቢያንስ 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ በጦርነት ወደምትታመሰው ወደ #የመን ተሻግረዋል ፤ ይህ ደግሞ በ2021 ሙሉ ዓመት ከተደረጉት ጉዞዎች ሁሉ የሚበልጥ ነው። (በ2021 ዓመት 27,700 ነበር)

IOM በዚህ ደረጃ ቁጥሩ ከፍ እንዲል ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የCOVID-19 እንቅስቃሴ ገደቦች መቃለላቸው ፣ የበለጠ ምቹ የአየር ሁኔታ መኖር እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና ድርቅ ይጠቀሳሉ ብሏል። (አብዛኞቹ ስደተኞች ከኢትዮጵያ መሆናቸው ተጠቅሷል)

IOM በቅርቡ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ በፍቃደኝነት የሚመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመደገፍ የ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ጠይቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ በሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመድረስ በማሰብ አደገኛውን የኤደን ባህረ ሰላጤ ያቋርጣሉ።

ስደተኞቹ በዋናነት ዓላማቸው ወደ የመን ሰሜናዊ ጎረቤት ወደሆነችው #ሳዑዲ_አረቢያ ለመድረስ ነው።