Get Mystery Box with random crypto!

Mereja News Live

የቴሌግራም ቻናል አርማ zenalivee — Mereja News Live M
የቴሌግራም ቻናል አርማ zenalivee — Mereja News Live
የሰርጥ አድራሻ: @zenalivee
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 155

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-02-01 20:46:34 https://t.me/zenalivee?livestream=556f112ad6f848d258
27 viewsUmu Abdallah, 17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 20:46:24 Live stream started
17:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 20:30:03
በሚገባ ያንብቡ

#የበአል ስጦታ

በመጀመሪያ ለመላው ሙስሊም ወገኖቻችን እንኳን ለኢድ አል-አድሃ(አረፋ) በአል በሰላም እደሳችሁ ማለት እንወዳለን

ድርጅታችን ኢትዮቴሌኮም በአሉን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የካርድና የጥቅል ሽልማቶችን አዘጋጅቷል። ተሸላሚ ለመሆን ቻናላችንን በመቀላቀል ሌሎችን መጋበዝ ብቻ ነው

የኢትዮ ቴሌኮም የበዓል ስጦታ ቻናል ይቀላቀሉ


ሽልማቱ በ 3 ደረጃ ነው :

1ኛ. ከ 100 ሰው በላይ ሼር ለሚያደርጉ 5ሺ ብር ጥሬ ገንዘብ በአካውንት እናስገባለን።
2ኛ. ከ 50 ሰው በላይ ሼር ካደረጉ 2500 ብር ገቢ ይደረግሎታል።
3ኛ. ከ 25 ሰው በላይ ሼር ለሚያደርጉ የ 1663 ብር- የአንድ ወር ያልተገደበ የድምፅ እና የኢንተርኔት ጥቅል
( ብሩን ከፈለጉ በአካውንት ይላክሎታል)

ተሸላሚ ለመሆን ይሄን መልዕክት ኮፒ አድርገው ለወዳጅዎ መላክና ፌስቡክ እና ቴሌግራም ግሩፖች ላይ ሼር (#forward) ማድረግ ብቻ ነው


ማሳሰቢያ! ተሸላሚ ለመሆን የቻናሉ አባል መሆን አለብዎት join ካላረጉ ለምን ያህል ሰው share አንዳደረጋቹ መረጃ ማግኘት አንችልም

@ethio_telecom_holiday_gift


የኢትዮ ቴሌኮም የበዓል ስጦታ ቻናል ይቀላቀሉ
9 viewsHamudi Ha, 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 06:45:13 #እንድታውቁት

ኢትዮ ቴሌኮም ከሀገር ውጭ ባሉት ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ የኢንተርኔት መገናኛ መስመሮች ላይ ባገጠመው ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎቱ በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

በዚህም የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ወይም የፍጥነት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል ከይቅርታ ጋር ገልጿል።

ድርጅቱ ፤ አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ባለሙያዎቹ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ገልጾ እስከዚያ ድረስ ደንበኞቹ በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።
81 viewsUmu Abdallah, 03:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 06:44:44 #AddisAbaba | በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሆኗል።

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉን ገልጿል።

የታሪፍ ማሻሻያው የተደረገው አለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን መሰረት በማድረግ እንደሆነ ተገልጿል።

በዚህም በመዲናዋ በሚገኙ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ተደርጓል።

የነዳጅ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ የትራንስፖርት ዋጋ ላይ ከነገ ጀምሮ ከ0.50 ሳንቲም እስከ 3 ብር 50 ሳንቲም ጭማሪ ማድረጉን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮው አስታውቋል።

በዚህም በሚድ ባስ 0.50 ሳንቲም እስከ 2.00 ብር የተጨመረ ሲሆን በሚኒ ባስ 0.50 እስከ 3.50 ተጨምሯል።
75 viewsUmu Abdallah, 03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:51:13
ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ተወለደ።

በወላይታ ዞን በገሱባ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አንዲት እናት ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ትላንት ግንቦት 22 ቀን 2014 ዓ/ም ተገላገለች።

ይህ ክስተት " Natal teeth " ተብሎ እንደሚጠራ የዘርፉ ባለሙያዎች የሚገልፁ ሲሆን ከዚህ በፊት ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም አዲስ ከሚወለዱ ከ2000 - 3000 ሕጻናት ውስጥ በአንዱ ላይ ሊከሰት እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ፡፡

ትላንትና የተወለደው ሁለት ጥርስ ያለው ልጅ ምንም ሳይቸገር ጡት እየጠባ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ የወላይታ ዞን ኮሚኒኬሽን መረጃ ያሳያል።

በዚህ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ ሊሰጥ የሚችል ፅሁፍ በዚህ ድረገፅ ማግኘት ይቻላል ፦ https://www.stanfordchildrens.org/en/topic/default?id=natal-teeth-90-P01862

#ወላይታዞንኮሚኒኬሽን #Stanfordchildern
90 viewsUmu Abdallah, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:51:13 " በ5 ወር 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ ወደ የመን ተሻግረዋል " - IOM

እንደ ተመድ የስደተኞች ኤጀንሲ (IOM) ፤ ባለንበት በዚህ ዓመት 2022 (እኤአ) /በ5 ወር/ ቢያንስ 27,800 ሰዎች ከአፍሪካ ቀንድ በጦርነት ወደምትታመሰው ወደ #የመን ተሻግረዋል ፤ ይህ ደግሞ በ2021 ሙሉ ዓመት ከተደረጉት ጉዞዎች ሁሉ የሚበልጥ ነው። (በ2021 ዓመት 27,700 ነበር)

IOM በዚህ ደረጃ ቁጥሩ ከፍ እንዲል ካደረጉት ምክንያቶች መካከል የCOVID-19 እንቅስቃሴ ገደቦች መቃለላቸው ፣ የበለጠ ምቹ የአየር ሁኔታ መኖር እንዲሁም በኢትዮጵያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ እና ድርቅ ይጠቀሳሉ ብሏል። (አብዛኞቹ ስደተኞች ከኢትዮጵያ መሆናቸው ተጠቅሷል)

IOM በቅርቡ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ በፍቃደኝነት የሚመለሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ለመደገፍ የ7.5 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ጠይቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ግን ከኢትዮጵያና ከሶማሊያ በሺህ የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን በኩል ወደ መካከለኛው ምስራቅ ለመድረስ በማሰብ አደገኛውን የኤደን ባህረ ሰላጤ ያቋርጣሉ።

ስደተኞቹ በዋናነት ዓላማቸው ወደ የመን ሰሜናዊ ጎረቤት ወደሆነችው #ሳዑዲ_አረቢያ ለመድረስ ነው።
65 viewsUmu Abdallah, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:51:13 #EU #RUSSIA

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት በሩስያ የነዳጅ ግብይት ላይ ማዕቀብ ጣሉ።

27ቱ አውሮጳ ህብረት አባል ሃገራት በሩስያ የነዳጅ ግብይት ላይ ማዕቀብ መጣላቸውን ይፋ አድርገዋል።

አባልሃገራቱ በግዙፉ የሩስያ ባንክ ስቤር ባንክንም ከዓለማቀፉ የባንኮች የክፍያ ስረዓት ወይም ስዊፍት ማስወጣታቸውን አስታውቀዋል።

በስምምነቱ መሰረት ወደ አውሮፓ የሚገባው የሩስያ ነዳጅ ሁለት ሶስተኛው እንደሚታቀብ የህብረቱ ፕሬዚደንት ቻርለስ ሚሸል ተናግረዋል።

ማዕቀቡ " የሩስያ የፋይናንስ ምንጭ በከፍተኛ ደረጃ በማንኮታኮት " ሩስያ በዩክሬን ላይ የከፈተችውን ጦርነት ገትታ ከሀገሪቱ ለቃ እንድትወጣ ያስገድዳታል " ሲሉ ፕሬዚደንቱ ተናግረዋል።

የጀርመኑ መራሄ መንግስት ኦላፍ ሾልስም " ስምምነቱ የጋራችን ነው " ብለዋል። ነገር ግን ከሃያ ሰባቱ ሃገራት መካከል ፦
ሃንጋሪ ፣
ስሎቫኪያ ፣
ቼክ ሪፐብሊክ እና ቡልጋሪያ ከሩስያ ነዳጅ ማስገባት #እንደማያቋርጡ አስታውቀዋል።

ይህንኑ በተመለከተ የሃንጋሪው ጠቅላይ ሚኒስትር ቪክቶር ኦርባን የነዳጅ ማዕቀቡ የህብረቱ አጀንዳ መሆን የለበትም ሲሉም ተቃውሟቸውን አሰምተው እንደነበር የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።
61 viewsUmu Abdallah, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:51:12 #MinT

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የፈጠራ ባለቤቶችን ለመደገፍና ለማበረታታት የሚያስችል አዋጅ እየተዘጋጀ መሆኑን አሳውቋል።

በሚኒስቴሩ የምርምርና ኢኖቬሽን ዘርፍ ዳይሬክተር ጀነራል ሠላምይሁን አደፍርስ ተከታዩን ብለዋል ፦

" ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ሥራዎቻቸው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው።

አሁን ላይ ደግሞ ጀማሪ የፈጠራ ባለቤቶች ኢንተርፕራይዝ መሆን እንዲችሉ ማበረታቻዎችን የያዘ አዋጅ እየተዘጋጀ ነው።

አዋጁ ሥራ ላይ ሲውል ውጤታማ የሚያደርግ ነው።

ረቂቅ አዋጁ ተዘጋጅቶ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ሲሆን አዋጁ ለመጽደቅ የሚያስችሉ አስፈላጊ ሂደቶችን ካለፈ በኋላ ተግባራዊ ይደረጋል።

አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸውን ዜጎች ለመደገፍ ሚኒስቴሩ እያወዳደረ ይገኛል፤ ተወዳድረው ያሸነፉ ፈጣሪዎች የገንዘብ፣ የቴክኒክና የሥልጠና ድጋፎችን እያገኙ ነው።

የልማት አጋሮች አሸናፊ ለሆኑ ኃሳቦች የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉበት ሥርዓትም ተዘርግቷል።

ሚኒስቴሩ አዳዲስ የፈጠራ ኃሳብ ያላቸውን ልጆች ከመደገፍ ባሻገር ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ልጆችም የሚወጡበት ሥርዓት እየዘረጋ ነው "

#ENA
52 viewsUmu Abdallah, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 06:51:12 #Tigray, #Mekelle

የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት መቋጫ ያገኝ እና አስተማማኝ ሰላም ይሰፍን ዘንድ ጥረት እያደረጉ የሚገኙት የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የቀድሞ ናይጄሪያ ፕሬዜዳንት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ ትግራይ ክልል ይገኛሉ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝደንት መቐለ እንደሚገኙ በመግለጽ ከዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ጋር እንደመከሩ ገልጸዋል።

ኦባሳንጆ እና ዶ/ር ደብረፅዮን በቀጠናዊ ጉዳዮች ጋር መምከራቸው የተነገረ ሲሆን ምክክሩን የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልሆነም።
46 viewsUmu Abdallah, 03:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ