Get Mystery Box with random crypto!

ዜና ቅዱሳን

የቴሌግራም ቻናል አርማ zenaakidusan — ዜና ቅዱሳን
የቴሌግራም ቻናል አርማ zenaakidusan — ዜና ቅዱሳን
የሰርጥ አድራሻ: @zenaakidusan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 944
የሰርጥ መግለጫ

በዜና ቅዱሳን መርሐ ግብር ላይ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየትና ጥቆማ @abrishte ላይ ልታደርሱን ትችላላችሁ

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-05 21:56:24
29
ዜና ቅዱሳን
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዕንቈ ብርሃን ዘገዳመ አንገብ
እንኳን ለአባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ተአምር

የተመረጠና የተወደደ ብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡ጸሎቱና በረከቱ ወዳጆቹ በሚሆኑ____ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
#ብፁዕና ቅዱስ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ጥቅምት 29 ቀን በአረፈ ጊዜ፤<<<<አባታችን ሆይ የገዳም ኮከብ የዓለም ብርሃን ነህ፤አባታችን ሆይ የሕሙማን ፈዋሽና ሙታንን የምታስነሳ ነህ፤አባታችን ሆይ ተስፋ ለቆረጡት ተስፋ የጎስቋሎች ረዳት ነህ፤አባታችን ሆይ የዕውሮች መሪ የአንካሶች ምርኩዝ ነህ>>> የሚል ብዙ ለቅሶና ዋይታ ሆነ፡፡
#ይህ ሁሉ በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር አምላክ የክቡር አባታችንን መቃብር የሚሸፍን አመድ/አፈር/ እና የወርቅ መስቀል ከሰማይ አወረደላቸው፡፡የአባታችን መቃብርም ቤተ መቅደስ በላይዋ በነበረባት በአንዲት ድንጋይ ውስጥ ሆነ ፤ይችህም በእግዚአብሔር ፈቃድ የተሰነጠቀች ነበረች፡፡ ክቡር ሥጋውንም ምድራዊ የሰው እጅ ሳይነካው አፏን ከፍታ ሥጋውን ዋጠችው/ተቀበለችው/፡፡
የብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃንና የአባ ፊልጶስ ጸሎታቸውና በረከታቸው ወዳጆቻቸው በምንሆን___ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
57 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 14:22:36
29
ዜና ቅዱሳን
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ዕንቈ ብርሃን ዘገዳመ አንገብ
እንኳን ለአባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ተአምር

የተመረጠና የተወደደ ብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን ያደረገው ተአምር ይህ ነው፡፡ጸሎቱና በረከቱ ወዳጆቹ በሚሆኑ_ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
#የብፁዕና ቅዱስ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን የሚያርፍበት ቀን በደረሰ ጊዜ፤የእግሩን ትቢያ እየላሱና እየተመገቡ ከእርሱ ጋር ይቀመጡ የነበሩትን ዝሆኖች አንበሶችንና ነብሮችን ጠራቸውና፤<<<እናንተ ወደማታውቁት ሀገር እሔዳለሁና ከእኔ ርቃችሁ ሒዱ፤ከአሁን ጀምሮም ወደ እናንተ አልመለስም ወደዚህችም ቦታ አልገባም>>> ብሎ አሰናበታቸው፡፡

#ከዚህም በኋላ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃን አባ ፊልጶስ የተባለውን መነኩሴ ጠራውና፤<< አባቴ ሆይ ከእኔ ጋር ይቀመጡ የነበሩትን ዝሆኖች አንበሶችና ነብሮችን ውሰዳቸው ከአንተ ጋርም ይቀመጡ፤በቀኝህና በግራህ ቦታ አዘጋጅተህ አስጠጋቸው>>> አለው፡፡

#ያን ጊዜም አባ ፊልጶስ <<<አባቴ ሆይ ፈቃድህ ይሁን>>> እያለ ተቀበላቸው።አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃንም ሰጠውና ወደእርሱ ወሰዳቸው ፤እስከ ሞታቸውም ቀን ድረስ ከአባ ፊልጶስ ጋር በአንድነት ተቀመጡ፡፡

የብፁዕ አባታችን አቡነ ዕንቈ ብርሃንና የአባ ፊልጶስ ጸሎታቸውና በረከታቸው ወዳጆቻቸው በምንሆን__ላይ አድሮና ጸንቶ ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን፡፡
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
104 views11:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 11:53:03 ሐምሌ 29
ዜና ቅዱሳን
አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዲላሶር ምሥራቃዊ ዘጸገሮ ወዘጕንድ
እንኳን ለአባታችን አቡነ እጨጌ ዮሐንስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
እጨጌ አባ ዮሐንስ ዘጐንድ

ጻድቁ ተወልደው ያደጉት በኢየሩሳሌም ሲሆን ነገዳቸውም እሥራኤላዊ ነው:: ነገር ግን ተጋድሏቸውን የፈጸሙት በሃገራችን ኢትዮዽያ ውስጥ ነው:: እጨጌ አባ ዮሐንስ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቀጥሎ ባለ ረዥም እድሜ ጻድቅ መሆናቸው ይነገራል::
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ያረፉት በ562 ዓመታቸው ሲሆን እጨጌ አባ ዮሐንስ ደግሞ በ500 ዓመታቸው ነው:: የሚገርመው ጻድቁ የታላላቁ ጻድቃን ገብረ መንፈስ ቅዱስ : ተክለ ሃይማኖት: ሳሙኤል: ዜና ማርቆስ እና ሌሎችም ባልንጀራ ነበሩ::
በዛ ዘመን ዘረኝነት በቅዱሳኑ ዘንድ አልነበረምና ነጭ ሆነ ጥቁር : ከየትም ይምጣ የሰው ልጅ መሆኑ ብቻ በቂ ነበር:: እጨጌ አባ ዮሐንስ በሃገራችን 5 በዓቶች የነበሯቸው ሲሆን በአንድ በዓት የሚኖሩት ለ50 ዓመት ነበር::
በዚህም በኢየሩሳሌም ለ50 ዓመት : በኢትዮዽያ ደግሞ ለ450 ዓመታት ኑረዋል:: ከበዓቶቻቸው አንዱ ደብረ ሊባኖስ ሲሆን በገዳሙ ለ50 ዓመታት አበ ምኔት(እጨጌ) ሆነው አገልግለዋል:: "እጨጌ" የሚባሉትም በዚህ ምክንያት ነው::
ጻድቁ የመጨረሻ ዘመናቸውን ያሳለፉት በጐንድ (ጉንድ) ተክለ ሃይማኖት ገዳም ነው:: ገዳሙ የሚገኘው በሰሜን ጐንደር ዞን : በለሳ ወረዳ ውስጥ ሲሆን የመሠረቱትም ራሳቸው ናቸው:: ነገር ግን በራሳቸው እንዲጠራ አልፈለጉምና ገዳሙ የሚጠራው በወዳጃቸው በአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስም ነው::
ጐንድ እኛ ኃጥአን ሳይገባን ያየነው ገዳም ነው:: ዛሬም ድረስ ድንቅ የሆኑ አበው የሚኖሩበት : ተአምራትም የማይቋረጥበት : ፈዋሽ ጠበል ያለው ደግ ገዳም ነው:: ጻድቁ እጨጌ አባ ዮሐንስ ግን አስታዋሽ አጥተው እየተዘነጉ ካሉ ቅዱሳን አንዱ ናቸው:: ምንም ዛሬ አጽማቸው ፈልሶ ወደ ደቡብ ኢትዮዽያ አካባቢ ቢሔድም እርሳቸው በ500 ዓመታቸው ያረፉት በዚህ ገዳም ውስጥ ነው::
ከጻድቁ አቡነ ዮሐንስ በረከትን ይክፈለን
:-#መ/ር ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
113 views08:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 11:52:42
86 views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:39:48 ሐምሌ 28
ዜና ቅዱሳን
ማር አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ

ገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ
የአቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ አማላጅነትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
(ሊንኩን በመጫን በድምጽ ያዳምጡ)

ገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ክፍል ፪
121 views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:39:13 ሐምሌ 28
ዜና ቅዱሳን
ማር አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ

ገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ
የአቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ አማላጅነትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
(ሊንኩን በመጫን በድምጽ ያዳምጡ)

ገድለ አቡነ ፊልጶስ ዘደብረ ሊባኖስ ክፍል ፩
115 views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 10:35:38
ሐምሌ 28
ዜና ቅዱሳን
አቡነ ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ
እንኳን ለአባታችን አቡነ ፊልዾስ ዘደብረ ሊባኖስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ
ታላቁ ኢትዮዽያዊ ጻድቅ: ሐዋርያና ሰማዕት #አቡነ_ፊልዾስ የጻድቁ #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሲሆኑ የተወለዱት በምድረ ሽዋ በ1266 ዓ/ም ነው:: ከልጅነታቸው ጀምረው ምሥጢር ተመራማሪና መጻሕፍትን መርማሪ የነበሩት ጻድቁ የመነኑት ገና በ15 ዓመታቸው ነበር::
በደብረ_ሊባኖስ በአሞክሮ ለ3 ዓመታት ቆይተው መንኩሰዋል:: ለ22 ዓመታትም የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ደቀ መዝሙር ሆነው አገልግለዋል:: አቡነ ተክለ ሃይማኖት በ1306 ዓ/ም ነሐሴ 24 ቀን ሲያርፉ የተተኩት አባ ኤልሳዕ ቢሆኑም ለ3 ወራት ቆይተው ዐርፈዋል::
በ1307 ዓ/ም አቡነ ፊልዾስ የደብረ ሊባኖስ አበ ምኔት (እጨጌ) ሁነዋል:: ገዳሙንም ለ28 ዓመታት መርተዋል:: ከዚያም በዘመነ አፄ ዓምደ ጽዮንና በአፄ ሰይፈ አርዕድ ብዙ ስደት: መከራ: እሥራትና ግርፋት ደርሶባቸዋል:: ምክንያቱ ደግሞ እውነትን መናገራቸውና ነገሥታቱን መገሰጻቸው ነበር:: በስደትም ለ6 ዓመታት ከ9 ወራት ቆይተዋል::
ሃገሪቱን በስብከተ ወንጌል ካበሩ #12ቱ_ንቡራነ_እድ አንዱ የሆኑት #እጨጌ አባ ፊልዾስ በተወለዱ በ74 ዓመት ከ9 ወራቸው በ1341 ዓ/ም ዐርፈዋል:: የተቀበሩት #በደብረ_ዕንቁ ሲሆን ካረፉ በ140 ዓመት #አቡነ_መርሐ_ክርስቶስ ዐጽማቸውን አፍልሰዋል::
ከጻድቁ አቡነ ፊልዾስ በረከትን ይክፈለን
:-#መ/ር ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
115 views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 14:00:58 27
ዜና ቅዱሳን
ገዳማዊ አባ በግዑ

ተአምረ አባ በግዑ
የአባ በግዑ አማላጅነትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
(ሊንኩን በመጫን በድምጽ ያዳምጡ)

ተአምረ አባ በግዑ
132 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 14:00:48
126 views11:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 13:58:40 27
ዜና ቅዱሳን
ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት

ተአምረ ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
የቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት አማላጅነትና ረድኤት ከሁላችን ጋር ይሁን
t.me/zenaakidusan ...በመጫን የቅዱሳኑን የህይወት ዜና ያጣጥሙ፣
(ሊንኩን በመጫን በድምጽ ያዳምጡ)

ተአምረ ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
96 views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ