Get Mystery Box with random crypto!

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ታገቱ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኾኑት ብፁዕ አቡነ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ) ነጭ ነጯን

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ታገቱ

የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ዛሬ ኅዳር 13 ቀን 2016 ዓ.ም በመንበረ ጵጵስናቸው እንዳሉ መታገታቸው ተገለጸ።

ከሀገረ ስብከቱ ለማረጋገጥ እንደ ተቻለው ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተመልሰው ዛሬ የኹሉንም የወረዳ ቤተክህነት ሥራ አስኪያጆች  በሀገረ ስብከታቸው ሰብስበው ውይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር።

ይኹን እንጂ ከጠዋቱ አንድ ሰዓት ገደማ በመንግሥት የተደራጁ በርካታ ወጣቶች ወደ ብፁዕነታቸው መኖሪያ ጡሩንባ በመንፋት በመምጣት  መኖሪያ ቤታቸውን በድንጋይ በመደብደብ “ና ውጣ” እያሉ ይጮኻሉ።

የተፈጠረውን ገዳይ ለዞኑና ለከተማው የጸጥታ አካል አሳውቀው ከጠዋቱ ሦስት ሰዓት ላይ የዞኑና የከተማው ጸጥታ ፓሊስ ኃላፊዎች በመንበረ ጵጵስናው ደርሰው ወጣቶቹን አስወጥተው ለብቻ ወስደው ካናገሩ በኋላ ቀን አምስት ሰዓት ላይ ምንም መልስ ሳይሰጡ ተመልሰው ወደ ቢሮ ሄደዋል።

በአኹኑ ሰዓት በርካታ ወጣቶች ዙሪያውን ከበው የመኖሪያ ቤቱን ዋና የመብራት ቆጣሪ በማጥፋት መስኮቱን በድንጋይ በመደብደብ ላይ ይገኛሉ።

በተጨማሪም ከየወረዳው ለስብሰባ በጠዋት የመጡት የወረዳ ቤተክህነት ኃላፊዎች እየተደበደቡ የተባረሩ ሲኾን ወጣቶቹ የብፁዕነታቸውን መኪና እንዳይንቀሳቀስ ጎማውን አስተንፍሰዋል።

የዞኑም አስተዳደር ስልክ ቢደወልም ስልክ በማጥፋት መልስ ማግኘት አልተቻለም።

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ከዚኽ በፊት ጥር 14 ቀን 2015 ዓ. ም በተፈጸመው ሕገ ወጥ የብሔር ብሔረሰብ ሹመትን በመቃወም ቤተክርስቲያን ብሔርን ማዕከል አድርጋ መሾም የለባትም በሚል መቃወማቸውና በሐምሌ 9 በተደረገውም የአንድ ብሔር ሲመት ላይ አለመገኘታቸው ይታወሳል።