Get Mystery Box with random crypto!

'…አስተማማኝ መረጃ እና ማስረጃ ይዘን በአሁን ሰዓት የኦነግ ሸኔውን መሪ ጃልመሮን እና የአማጺ ሠ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…አስተማማኝ መረጃ እና ማስረጃ ይዘን በአሁን ሰዓት የኦነግ ሸኔውን መሪ ጃልመሮን እና የአማጺ ሠራዊቱን ከፍተኛ አመራሮች ከበባ ውስጥ አስገብተናል። በሕይወት እንያዛቸው ወይስ እንደምስሳቸው? በማለት በጋምቤላ ጃልመሮን ከበባ ውስጥ ያስገቡት ጄነራል ለአለቃቸው ለፊልድ ማረሻ ብርሃኑ ጁላ መልእክት ያስተላልፋሉ።

"…ፊልድ ማረሻውም መልሰው ከጋምቤላ ከሚደውሉት ጄነራል የደረሰውን መልእክት እንደሰማ ለጄነራሉ እንዲህ በማለት ይመልሳል። " ቆየኝማ… በከበበው እርግጠኛ ከሆናችሁ ወደ እርምጃ ከመግባታችሁ በፊት እንዲህ ያለውን ከፍ ያለ ጉዳይ መወሰን ያለባቸው ጠሚው ስለሆነ ለእሱ ልንገርና ውሳኔውን ላሳውቅህ ይለዋል።

"…ቆይቶ ራሱ አቢይ አሕመድ ወደ ጀነራሉ ደወለ። ጀነራሉንም ከፊልድ ማረሻው የሰማውን የጃልመሮን በጋምቤላ ክልል በመከላከያ ሠራዊት መከበብንም ጠይቆ አረጋገጠ። እናም ለጄነራሉም አለው። …የሚገርም አጋጣሚ ነው። ሰሞኑን ለአንድ ከፍተኛ ተልእኮ አጭተንህ ቴሌግራም ልናደርግልህ እያሰብን እያለን ሳለ ነው መልእክትህ የደረሰን። አሁን ሠራዊቱ በሰዎቹ ላይ እርምጃ እንዳይወስድ። ከበባውን ትቶም ወደ ኋላ ይመለስ። አንተ ግን አሁን ቴሌግራም ይደርስሃል። ለከፍተኛም ግዳጅ ተዘጋጅ እናም በአስቸኳይ የታዘዝከውን ፈጽም ብሎ ዘጋው።

"…ጄነራሉና ሠራዊቱ ጃልመሮን ከነሙሉ ኃይሉ አይናቸው እያየ ትተዉት። ወደ ኋላም ተመለሱ። ወደ ማረፊያ ሆቴሉ የተመለሰው ጄነራሉም ታመመ። በንዴት ደም አስመለሰው፣ ደምም አስተፋው። "ለከፍተኛ ሀገራዊ ግዳጅ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ተዘዋውረሃል።" የሚል የቴሌግራም መልእክትም ከጠሚው በፍጥነት ደረሰው። ጄነራሉም በቀናት ውስጥ ተዘዋወረ።

"…የአባ ገዳይ ልጆች በቁማሩ በገገማ ማሸነፋቸውን ቀጥለዋል። በሰው ነፍስ መጫወቱም ቀጥሏል። ግን እስከመቼ የሚለው ጥያቄ መልስ ይፈልጋል።