Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሚያ ነው…! '…የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ ኦሮሞ ነው። አውራ ፓርቲውም የኦሮሞ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

በኦሮሚያ ነው…!

"…የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ ኦሮሞ ነው። አውራ ፓርቲውም የኦሮሞ ነው። የኦሮሚያ ፕሬዘዳንትም ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ ኦሮሞ ነው። የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር ኤታማዠር ሹምም ብራኑ ጁላ ኦሮሞ ነው። የአየር ኃይሉ አዛዥ ይልማ መርዳሳም ኦሮሞ ነው። የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አዛዥም ደመላሽ ገብረ ሚካኤልም ኦሮሞ ነው። የኢትዮጵያ ደኅንነት ዋና ሓላፊው ራሱ ሬድዋን ስልጤው አሻንጉሊት ነው። ሲሳይ ቶላ ነው ፈላጭ ቆራጩ።

"…በዚህ ሁሉ መሃል የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር አቶ በቴ በተወለደበት በገዛ ቀዬው ከሌሊቱ በ6 ተኛው ሰዓት፣ 6 ፖሊሶች መጥተው ከሆቴሉ አውጥተው፣ እጆቹን የፊጥኝ አስረው፣ በ6 ጥይት ደብድበው የገደሉት።

"…አሁን ዐማራው፣ ነፍጠኛው ይሄን አደረገ ብለው እነ ጃዋር ሊሰብኩ፣ እነ ሽመልስና አብይ ሊቀሰቅሱ እግዚአብሔር እድልም አልሰጣቸው። ፋኖም፣ ኦነግ ሸኔም ነው ለማለት እንዴት ይድፈሩ? በቃ ነገሩ ተገለበጠ። የግፍ ግድያው ወደ ዐማራ የተኮሱት የሴራ ሽጉጥ ወደራሳቸው አንባረቀ።

"…የሚገርመው ሸገር ራዲዮ የኦነግን መግለጫ የሚያነበው በምን የሕግ ማዕቀፍ ነው? የፋኖን፣ የባልደራስን፣ የመኢአድን መግለጫ የማያነበው ሸገር ራዲዮ እንዴት ለኦነግ ሲሆን ደፈረ…?

• ፀረ ኦርቶዶክስ ናት የሚሏት ጋዜጠኛ መዓዛ ብሩ ወነግ ናት እንዴ?

• ለማንኛውም ከሕግ አግባብ፣ ከፍርድ ቤት ውሳኔ ውጪ እንዲህ የዜጎችን በግፍ መገደል አጥብቄ እቃወማለሁ።