Get Mystery Box with random crypto!

መልካም… በመጀመሪያው ትግሬዎቹን እና ኦሮሞዎቹን በጠየቅኩበት ቪድዮ የተሰደቡት ትግሬዎችም ሆኑ በስ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

መልካም… በመጀመሪያው ትግሬዎቹን እና ኦሮሞዎቹን በጠየቅኩበት ቪድዮ የተሰደቡት ትግሬዎችም ሆኑ በስማቸው የተሳደበላቸው ኦሮሞዎች አፍረው ፀጥ ብለዋል። ዐማሮችም ከጥቂቶች በቀር ትእዛዝ መመሪያ አክብራችሁ እጃችሁን እየበላችሁ በትእግስት ጠብቃችኋል አሳልፋችኋልም። ተመስግናችኋልም።

"…ይሄ ነውረኛ ባለጌ ስድአደግ ሰው በቅድሙ ቪድዮ ትግሬን አሁን ደግሞ ቀጥሎ በማሳያችሁ ቪድዮ ዐማራን ይሳደባል። የእኔ ጥያቄ…?

• ልጁ ማንን ቢተማመን ነው እንዲህ LIVE እየገባ በዚህ መጠን በነፃነት አላፊ አግዳሚውን የሚሳደበው?

"…ብልፅግናስ እሺ ነውር የሆነ ፓርቲ ነው ኮተታም ወሴ ሰብሳቢ ቆሮቆምቦሾ የሆነ ፓርቲ ነው። ኦሮሞዎቹ እንዴት የዚህ ልጅ ደጋፊ ሆነው አጅበውት ይዞራሉ…? በዚህ ልጅ ስድብስ የሚያሳኩት ምን ዓይነት ድልና ስኬት ነው?

• ኦሮሞ በዚህ ልጅ መወከሉስ፣ አግባብ ነው ወይ…? ኦሮሞዎችስ ዐማራና ትግሬ በዚህ በምትሳሱለት ልጃችሁ በመሰደባቸው የምታገኙት እርካታ አለ ወይ…?

"…ፖሊስ፣ የፍትሕ አካላት ሕዝብን በዚህ መጠን የሚሳደብ ነውረኛ ሰው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት አጃቢ መድቦለት በነፃነት ማንቀሳቀሱ ምንን ለማሳካት ፈልጎ ነው?

• ልጅ ያሬድ የሚባለው አሁን ከርቸሌ የወረደው ግለሰብ ከዚህ በላይ ምን በደል አድርሶ ነው የታሰረው?

• ሁላችሁም በመልሱ መሳተፍ ትችላላችሁ።