Get Mystery Box with random crypto!

ከላይኛው የቀጠለ… …የሃይማኖት አባቶችን እየረሸኑ፣ እያጠፉ፣ በጭካኔ አረመኔ ቡልጉ ሆነው፣ ፀ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ከላይኛው የቀጠለ… …የሃይማኖት አባቶችን እየረሸኑ፣ እያጠፉ፣ በጭካኔ አረመኔ ቡልጉ ሆነው፣ ፀለምት ውስጥ በደርግ ተከበው መውጫ ያጡት ወያኔዎች የሚበሉት ቢያጡ እጣ ተጣጥለው ዕጣው የወደቀበትን ጓዳቸውን አርደው እየበሉ ሰይጣንን አስንቀው ወደ ሥልጣን መጡ። አየህ የራሱን ጓድ ዕጣ ተጣጥሎ አርዶ የበላ ወያኔ ለአንተ ምኑም ላልሆነከው ምንይጨንቀዋል? ህፃን ተገደለ፣ ቄስ ተገደለ፣ እርጉዝ ተገደለ ደንታውም አይደል። አንተ እና እኔ ነን እንጂ ለደርግ፣ ለወያኔና ለኦነግ ኦህዴድ ብልጽግና የሰው ልጅ ማለት ማኅበራዊ እንስሳቸው ነው። እንደ በግ፣ እንደ ዶሮ ያለ ነው። እነሱ ሰው ሲሞት አይደነግጡም። ምክንያቱም ሰውን እንደ ዶሮ ነው የሚቆጥሩት።

"…መነሻችን ሕዝቡ ለምን ፈሪ ሆነ ነው አይደል? አዎ የኢትዮጵያ ሕዝብ ፈሪ የሆነው ከአገዛዞቹ ጭካኔ የተነሣ ነው። አረመኔነት ቦታ ሲይዝ ሕዝብ ፈሪ ይሆናል። ወያኔና ኦነግ ሸአቢያም ሲመጡ ለመፈራት፣ ለመከበር ከደርግ የባሰ ጨካኝ፣ አረመኔ መሆን ነበረባቸው። ፓስተር ታምራት ላይኔ ምሥራቅ ሄዶ ሱማሌውንና ኦሮሞውን "ይሄ ሽርጣም ሲልህ የነበረውን ነፍጠኛ ምን ትጠብቃለህ? " በማለት ዐማሮችና ኦርቶዶክሳውያን በገፍ እንዲታረዱ አደረገ። እነ ኦነግ በአሶሳ ዐማሮችን በአንድ ቤት ሰብስበው፣ በቤንዚል በእሳት አቃጠሉ፣ በአሩሲ፣ በሀረርጌ፣ በባሌ፣ እነ ኦነግ ዐማራን ከነ ነፍሱ ሀንቁፍቱ ከተቱ፣ ጥልቅ ገደል ወረወሩ። አውሬ ሆነው ሕዝቡን ፈሪ አደረጉት። የፈለገውን ሰው፣ የደበረውን መረሸን የተለመደ ሆነ። አየሕ ሕግና ፍትሕ፣ ርትዕም ከዙፋናቸው ሲነሡ ሕዝብ ምን መጠጊያ ይኖረዋል? ፈሪ ነው የሚሆነው?

"…በመጨረሻ ወያኔም 20 ምናምን ዓመታት አድራጊ ፈጣሪ ሆና ኢትዮጵያውያንን ሽባ አድርጋ እርሷም ሽባ ሆነች። ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊን ለመቃወም ለተቃውሞ የወጡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን በአደባባይ ረሽና ጭካኔዋን በአዲስ አበቤ ልብ ላይ ዘራች፣ በ1997 ዓም ባንክ በሌለበት፣ የተፈጠረውን ግርግር እንኳ የማያውቁ በሰፈር ውስጥ ብይ የሚጫወቱ ሕጻናትን ሳይቀር በአግአዚ ጦሯ ስናይፐር ጨፍጭፋ በውሸት ግግም ብላ የገደልኳቸው ባንክ ሲዘርፉ ነው ብላ ሀገር አሸማቀቀች። ወለጋ ላይ እናት በተገደ ልጇ አስከሬን ላይ ተቀምጣ እንዳታለቅስ ተደረገች። በአሰቦት፣ በጎንደር፣ በእስጢፋኖስ መነኮሳት ታረዱ፣ ምእመናን ተገደሉ፣ ባሕታውያን በታቦት ፊት ተገደሉ። ድፍረት በዛ። አዲስ አበባ ተጨፈጨፈ። ከትግራይ ክልል በቀር ሀገር ምድሩ በሙሉ ሰቆቃ ሆነ። ይሄ ሁሉ ሲሆን ትግሬ የሆነ ሁሉ ይጨፍር ነበር።

"…መለስም ሞተ፣ ኢህአዴግም አረጀ። ኃይለማርያም ደሳለኝ አሻንጉሊቱ ሰውዬ እንኳ ጭካኔን ተለማምዶ፣ የኦሮሞንና የዐማራን ወጣቶች በዐዋጅ አስጨፍጭፎ ለሌላ አዲስ ቡልጉ ሥልጣን ለቅቆ ወረደ። ወያኔም የእጅዋን አገኘች። ይቆይ ይዘገይ ይሆናል እንጂ ሁሉም ሰው እኮ የእጁን ሥራ ማግኘቱ አይቀርም። ሀገር አመንምኑ የገደለው መለስ መንምኖ በቁሙ አልቆ ነው የሞተው። መሬት መርገጥ የተጠየፉ የህወሓት አባላት መደበቂያ መሬት ነበር ያጡት። በክረመት በበረዶ አህያ ብለው ይሰድቡት በነበረው ሰው ሁሉ ፊት ነው እንደ አሕያ የተንከባለሉት። በሕይወት ቆይተን ሁሉንም አየነው። በሕግ፣ በሥርዓት ሲያሾፉ የነሸሩት የትግራይ ነፃ አውጪ አባላትና ደጋፊዎች የሕግ ያለህ፣ የመንግሥት ያለህ ቢሉ የማይሰማቸው ራሳቸው ያሳደጉት ዱዳ አቢይ አሕመድን ጣለባቸው። ባላገጡባት ፍትሕ ተላገጠባቸው። አሁን እኮ የትግሬ ነፃ አውጪዋ ሕወሓትና አባላቶቿ የሚኖሩት ኑሮ እኮ ኑሮ አይደለም። አፋቸው አልሞት ብሎ ነው እንጂ ሞተዋል፣ ደቅቀዋል፣ አብደዋል፣ ደክርይተዋል፣ ዐመድ ነፍቶባቸዋል። ኦሮሞ ስር መርመጥመጡ ምንአልባት የሆነ ዕድል ካለ ብለው ነው እንጂ እያሉ የሉም እኮ። ይሄ ሁሉ ሕግን፣ ፍትሕን፣ ርትዕን፣ ሥርዓት ማጥፋት የፈጠረው ነው። ሕግን አጥፍተህ በሕግ አምላክ ብትል ማን ይሰማሃል? አሁን ሕጉ ጠመንጃ ያለው፣ ሥልጣን ያለው ሰውዬ ነው። አለቀ።

"…ጨካኟ ሕወሓት ስትሄስ፣ ስትወገድ የተተካው ዳግማዊው ደርግ አቢይ አሕመድ ነው። የኮሎኔል መንግሥቱ ሃይ ኮፒ ኮሎኔል አቢይ አሕመድ ነው ከች ያለው። መንግሥቱ ኃይለማርያም ኢትዮጵያ ትቅደም እያለ እንደመጣው አቢይ አሕመድም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ እያለ ከች አለ። አሞሌ ጨው እያላሰ በሬውን ሁሉ ገደል አፈፋ ወስዶ አረደው፣ ከተተውም። አዎ አቢይ አሕመድ መንግሥቱ ኃይለማርያምን እያማከረ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በተለይ ዐማራና ኦርቶዶክሱን መንግሥቱ ሞክሮ ያልጨረሰውን እርሱ አስቀጠለ። መንግሥቱ ኃይለማርያም 17 ዓመት ሙሉ ተዋግቶ ያልገደለውን የትግሬ ሕዝብ አቢይ አሕመድ በጥቂት ወራት ብቻ ሚልዮን ትግሬ ርምርም አድርጎ ጨፍጭፎ እጁን በሳሙና ታጥቦ በሰላም ሳይሰደድ ይኖራል። ዘዎ አቢይ አሕመድ እንደዚያ ነው። እንዲያውም ትግሬዎቹ በስቶኮሆልም ሲንድረም ተጠቂ ሆነው አረፉት።

"…አሁንም ወደ ጀመርኩት ጥያቄ ልመለስ። ሰዉ ለምን ፈሪ ሆነ ነው የርዕሰ አንቀጼ ርዕስ። አዎ ሰዉ ፈሪ የሆነው ሕግ ሥለሌ ነው። ፍትሕ ስለሌለ ነው። ርትዕ ሥለጠፋ ነው። ሥርዓት ስለፈረሰ ነው ፈሪ፣ ቦቅቧቃ የሆነው። ቅዘናም፣ በጭባጫ የሆነው። አዎ ለዚያ ነው። ዝምታው የተፈጠረው ከጭካኔው የተነሣ ነው። አቢይ አሕመድ ቡራዩ ጀመረ፣ መሃል አዲስ አበባ ቀጠለ፣ ለገጣፎን አውድሞ፣ ወለጋን ጨፍጭፎ፣ ሻሸመኔን አቃጥሎ፣ በባሌ፣ በሀረርጌ፣ በኢሉአባቦራ ሰዎችን አርዶ፣ አስከሬን ጎትቶ እያሳየ፣ በመተከል በግሬደር ሕዝብ ቀብሮ፣ በሸዋ ዘር አጥፍቶ፣ በትግራይ ሚልዮን አርዶ፣ በግልጽ በቪድዮ እያስቀረጸ ጨፍጭፎ ሰዉን ፈሪ አደረገው። የሰው ዝምታ ጭካኔው የፈጠረው ነው። በካራ አርደው አስደነገጡት። በሜንጫ ጨፍጭፈው አስደነገጡት። ለመጮህም ሕግና ሥርዓት እኮ መኖር አለበት። አይደለም እንዴ?

"…በምኖርበት ሀገር በጀርመን ፖሊስ የማየው አልፎ አልፎ ነው። የሰከሩ ሰዎች፣ በሀሺሽ የደነዘዙ ሰዎች እንኳ ቦርኮ የሆኑ መጥተው ሳንቲም ይለምኑሃል። የለኝም ስትላቸው ዳንከ ብለው አመስግነውህ ነው የሚሄዱት። ሰዎች አይጣሉም። ተሰዳድቦ ነው የሚለየው። እብድና ሰካራም እንኳ የፈለገ ቢያብድ፣ የፈለገ ጥንብዝ ብሎ ቢሰክር አዕምሮው ድንበር አያሳልፈውም። ሕግ የሚሉት ተጠያቂነትን እንደሚያመጣበት ያውቃል። ሰው አብዶ ሕግ እንደሚፈራና እንደሚያከብር በግልፅ ያየሁት እዚህ አውሮጳ ነው። የሕግ የበላይነት ባለበት ሀገር ሁሉም ሕግን ያከብራል። ሁሉም ፖሊስ ነው። ሁሉም ፍትሕ አክባሪም ፍትሕ አስፋኝም ነው። ለተቃውሞ የሚወጡ ሰዎች ሕግ አክብረው እስከ ጥግ ድረስ ነው መብታቸውን የሚጠቀሙት። ሕገወጥ ስትሆንም የሚቀጣህ፣ የሚፈርድብሕ ሕጉ ነው።

"…እናት ትኬት አልቆረጠችም። የባቡር ትኬት። አንድ ህጻን ልጅ በጋሪ፣ አንድ ደግሙ በእጇ እየጎተተች ነው። አንድ የ9 ዓመት ቢሆነው ነው ሌላ ልጅ ደግሞ ራሱን ችሎ ቆሟል። እናት የምትጠብቀው ባቡር መጣ። ሁለቱን ልጆች እየነዳች፣ እየገፋች ወደ ባቡሩ እየቀረበች ነው። ሰዎች የባቡሩ በር እንዳይዘጋባት በሩ ላይ ቆመውላታል። እንዲህ አይነት መረዳዳት አለ በአውሮጳ፣ አንተ እየሮጥክ ባቡርና አውቶቡስ ውስጥ ቀድሞ የገባ ሰው በሩ ላይ ከቆመልህ ትደርስበትና ትገባለህ። ይሄን ልማድ አይቼአለሁ። ሹፌሩም በር ይዞ ለረጅም ደቂቃ ይዞ መቆሙ ካልበዛ በቀር አይቆጣም። ቅርም አይለው። ኋላ ላይ የሴትየዋ የ9 ዓመቱ ሕፃን አልገባም አለ። ብትለምነው፣ ብትለምነው ንቅንቅ አልል አለ። ሰዎችም ተጠግተው… ከታች ይቀጥላል…