Get Mystery Box with random crypto!

የልዑሉ መልእክት…! '…በዚህም መሠረት፣ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ሠራዊት የዓለም አቀፍ ድጋፍ ግብረ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

የልዑሉ መልእክት…!

"…በዚህም መሠረት፣ የዐማራ ፋኖ ሕዝባዊ ሠራዊት የዓለም አቀፍ ድጋፍ ግብረ ኃይል የተመሠረተ ሲሆን፣ ግብረ ኃይሉ ከዚህ በፊት በመላው ዓለም የተቋቋሙትን የዐማራ ሕዝባዊ ግንባር የድጋፍ ቻፕተሮች ከእነ አመራራቸውና ሙሉ ቁመናቸው ጠቅልሎ የሕዝባዊ ሠራዊቱን የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ እና የፋይናንስ ሥራዎች በላቀ ብቃትና አቅም እንዲሠራ ተልዕኮ ተሰጥቶታል።

በዚህም መሠረት:-

1. ዶ/ር አምሳሉ አስናቀ ----ሰብሳቢ
2. አቶ ሙሉጌታ አያሌው----ም/ሰብሳቢ
3. ልዑል ዶ/ር አሰፋወሰን አስራተ ካሳ …የዲፕሎማሲ ሓላፊ ተደርገው የተሰየሙ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሙሉ ትብብራቸውን እንድታደርጉላቸው አደራ እንላለን የሚለውን የአርበኛ ፋኖ እስክንድር ነጋን የዛሬ መልእክት ተከትሎ ብዙ መልእክቶች በውስጥ መስመር ደርሰውኛል።

"…ስለ ዶር አምሳሉ እና አቶ ሙሉጌታ አይመለከተኝም። አያገባኝምም። የወዳጄ፣ የቅርብ ጠያቂዬን የክቡር ልዑል አስፋወሰን አሥራተ ካሣን (ዶር) ሹመት በተመለከተ ግን ራሳቸው ልዑሉን እንደ ሁል ጊዜው የስልክ ግኑኝነታችን ዛሬም ተደዋውለን ጥያቄውን አንስቼላቸዋለሁ ነበር። 

• ክቡር ሆይ እንደተባለው ኮሚቴው ውስጥ አሉበት…?

~እውነት ነው አለሁበት። ነገር ግን መታወቅ ያለበት እኔ ገንዘብ ነክ ጉዳዩ ውስጥ በፍጹም የለሁበትም። የዲፕሎማሲውን ጉዳይ በተመለከተ ግን ዐማራ ሆነው በዐማራ ጉዳይ ቀርበህ አግዘን ለሚሉኝ ሁሉ እምቢ አልልም። ከ30 በላይ የዐማራ ማኅበራት እንዳሉ ተመልክቻለሁ። ሁላቸውም በዲፕሎማሲው መስክ የዐማራን ድምጽ በማሰማቱ በኩል አግዘን ካሉኝ አቅሜ እስከቻለ ድረስ እምቢኝ አልልም። እዚህም የሆነው ይሄው ነው። ገንዘብ ነክ ሥፍራ ላይ ግን የለሁበትም የእኔ ወንድም።

• ልዑል ሆይ ደኅና ይደሩልኝ !
~ አሜን ደኅና እደር የእኔ ወንድም።