Get Mystery Box with random crypto!

'…ዘወትር ሁልጊዜ ከምስጋናው መርሀ ግብራችን በኋላ ሁልጊዜ በቀጥታ ወደ ርዕሰ አንቀጽ መርሀ ግብራ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ዘወትር ሁልጊዜ ከምስጋናው መርሀ ግብራችን በኋላ ሁልጊዜ በቀጥታ ወደ ርዕሰ አንቀጽ መርሀ ግብራችን ነበር የምንሄደው። አልዋሻችሁም የቀሲስ መኮንን ደስታ ሞት ሳላስበው ጥልቅ የመደበት ስሜት ውስጥ ነው የከተተኝ። ህመሙ ወደ አምላኩ እንደሚወስደው እያወቅኩ ለምን እንዲህ እንደደነገጥኩ እና ቅር እንደተሰኘሁ ፈጣሪ ነው የሚያውቀው። ለዛሬ ርዕሰ አንቀጽ ብጽፍም በሕይወቴ እንዲህ በደነዘዘ የሞተ ስሜት ውስጥ ሁኜ ጽፌ አላውቅም። የጀመርኩትንም ተውኩት።

"…ከዚያ ይልቅ በጎንደርና በሸዋ ፋኖዎች ጉዳይ ሁለት ልብ አውልቅ ስብሰባዎችን አድርጌም ሁለቱም በታላቅ ደስታና ድል ተጠናቀዋል። እኔማ የትናንትናውን አክተር አቢይ አሕመድ የከሸፈበትን፣ ድባቅ የተመታበትንም፣ ትእቢቱ፣ ውሸቱ፣ ቀጣፊና የአጭበርባሪነት ካባው የተገፈፈበትን፣ ተደራጅተው የመጡት የኦሮሙማ አጭቤዎችም አንዱ ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቃል ለገቡላት ለተዋሕዶ ሃይማኖታቸው በመልካም እረኛነት የመቀጠል ቃል ኪዳናቸውን ያጸኑበትን፣ የቤተ መንግሥቱን ስብሰባ በተመለከተ ትዝብቴን ጽፌ ሳልጨርሰው ነበር ወደ ስብሰባው የሄድኩት።

"…ስብሰባው ላይ ሆኜ በወንጂ ስኳር ፋብሪካ 6 የድርጅቱ ሠራተኞች በኦነግ ታግተው የተጠየቁትን ገንዘብ መክፈል ባለመቻላቸው ምክንያት ትናንት መጋቢት 6/2016 ዓም ከ6ቱ 5ቱን ማለትም 1.አቶ በቀለ ጥሩነህ 2.አቶ ተሾመ ሔራሞ 3.አቶ ያለው ተመስገን 4.ወጣት ካሚል አብዱራህማን 5.አቶ ግርማ በላቸው አርደው አስከሬናቸው መገኘቱን፣ ከሟቾቹ መሐል አንዱ ኦሮሞ ነው ብለው ሳይገድሉት እንደቀሩ እየሰማሁ፣ በሌላ ዜና ደግሞ ከማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ከጸሎት መልስ ወደ ዶርማቸው በመመለስ ላይ የነበሩ 5 የዐማራ ተወላጅ ተማሪዎች በፌደራል መኪና ታፍነው ተወስደው የት እንዳደረሷቸው አለመታወቁን እያሰማሁ ነበር የዋልኩት።

•የነገ ሰው ይበለን።