Get Mystery Box with random crypto!

'…ይህ የጦርነት ውጤት ነው። ስትዋጋ ትገድላለህ፣ ትገደላለህ። ትማርካለህ፣ ትማረካለህ። እኩል ግን | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ይህ የጦርነት ውጤት ነው። ስትዋጋ ትገድላለህ፣ ትገደላለህ። ትማርካለህ፣ ትማረካለህ። እኩል ግን ትወድማታለህ።

"…የትግራይ ወጣቶች እየተዋጉ ያሉት በዐማራ ምድር ላይ ነው። ሲሞቱም አፈር ሆነው የሚቀሩት ዐማራ ምድር ላይ ነው። አሁን እነዚህ ሟቾች የህወሓትን ሰበካ ሰምተው በፈቃደኝነት የዘመቱ ላይሆኑ ይችላሉ። ከቤተሰብ 1ሰው ካልዘመተ እርዳታ አታገኙም ተብሎ ቤተሰብ በራብ ከሚያልቅ እኔ በሰይፍ ልሙት ብሎ የዘመተም ሊሆን ይችላል። ብዙም በዘማቹ ለመፍረድ ይከብዳል። ፀረ ኢትዮጵያ አቋም ይዞ፣ ፀረ ኢትዮጵያዊነት ስብከት ተግቶ የዘመተም የለም አልልም። ነፍ ነው። የትየለሌ…

"…ይሄ በውጭ ያለውን የእነ አሉላ ሰሎሞንን ዲስኩር፣ የ "በሎም" ፉከራን እየሰማንና እያየን በትግሬ ወጣቶች ላይ ብዙም መፍረድ ያለብን አይመስለኝም። እነሱ በርገር እየበሉ፣ ሞዴል መኪና እያሽከረከሩ፣ ረሃ ሆነው ተንደላቀው እንዲኖሩ፣ ጦርነቱ፣ ግጭቱ የእንጀራ ገመዳቸው የሆነላቸው ሰዎች ናቸው። ህወሓት ከጠፋች አብረው የሚጠፉ የህወሓት አፍና ምላሶች ናቸው። መሬት ላይ ባለው ሃቅ ግን የትግራይ ወጣት እያለቀ ነው።

"…ህወሓት የምትባል የሃገር ነቀርሳና አምጣ የወለደቻቸው ብአዴንና ኦህዴድ የሚባሉት የስለት ልጆቿ ከነ ዘረኛ ፖሊሲያቸው፣ ታቅፈው ከነሚንከባከቡት ገንጣይ አስገንጣይ ሕገ መንግሥቸው እስካልጠፉ ድረስ ሞቱም፣ እልቂቱም፣ ጦርነቱም ይቀጥላል።

"…በውጊያ ላይ መግደል፣ መማረክ፣ ደንብ ነው። የወንዶችም ተግባር ነው። አለልህ እንጂ ወሴ የሆነ ቁርንድድ ህፃናትና አራስ፣ አሮጊትና ሽማግሌ አራጅ አረመኔ። እንዲህ እንደ ትግሬ ልጅ ተወዶም ሆነ ፈቅዶ ተዋግቶ መሞት ተፈጥሮአዊም ነው። ሹርባ ሲቆነደዱ ውለው እያደሩ ህፃናትን ማረድ መጨፍጨፍ ግን የወንድም የሴትም ተግባር አይደለም። ፍናፍንትን አይመለከትም።

"…ነፍስ ይማር…!!