Get Mystery Box with random crypto!

'…ነገረ ጋላ '…አንዳንድ ሰዎች ጋላ የሚለውን የነገድ ስም ከስድብ ጋር ሲያያዝት ይታያል። ነገር | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

"…ነገረ ጋላ

"…አንዳንድ ሰዎች ጋላ የሚለውን የነገድ ስም ከስድብ ጋር ሲያያዝት ይታያል። ነገር ግን ጋላ ማለት ስድብ አይደለም። ጋላ የአንድ ጥንታዊ ነገድ መጠሪያ ስም ነው። የጋላ ነገድ በምሥራቅ አፍሪካ በኢትዮጵያና በኬኒያ የሚኖርም ሰፊ ሕዝብ ነው።

"…እስከ 18ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ጀርመናዊው ሚሽነሪ ኦሮሞ ብሎ አዲስ ስም እስከያወጣለት ድረስ ነገዱ ጋላ ተብሎ ነበር የሚጠራው። ልክ እንደ ጉራጌ፣ ሲዳማ፣ ትግሬ፣ አፋር ማለት ነው። ጀርመናዊው ፈረንጅ ባወጣለት አዲሱ ስም ኦሮሞ ተብሎ መጠራትን እንጂ ጋላ ተብሎ መጠራትን እንደ ስድብ የቆጠረውም ቆይቶ ነው። አሁን ፌስቡክ እንኳ ጋላ ብለህ ከጻፍክ 30 ቀን ነው የሚቀጣህ። ትግሬም ሰሞኑን ትግሬ መባል ደብሮኛል ተጋሩ በሉኝ እያለ ነው። ጉድ እኮ ነው። የምን ተጋሩ ባትጋሩኝ ነው። በቃ ትግሬነህ ትግሬነህ አከተመ።

"…ባህላችን ጠፍቷል እያሉ ዘወትር እሪሪ የሚሉት የዚህ ነገድ አባላት አዲስ አበባን ፊንፊኔ ለማለት የሚላላጡትን ያህል ጋላ የሚለውን የቀደመ የጥንት አባቶቻቸውን የክብር ስም ለማስመለስ ግን ጥረት ሲያደርጉ አይታይም። ይሄ ነውር ነው። ይታሰብበት።

"…በኬኒያ የነገድ ዝርዝር ውስጥ እስከአሁን ጋላ በክብር እንደተቀመጠ ነው። ጋላ መባልን በኬኒያ የሚያፍርበት ሰው የለም። ኢትዮጵያ ያሉቱ ናቸው ሲሸማቀቁ የሚታዩት። ብዙ ሰዎች ቤተሰብ ያወጣላቸው ስም ሲደብራቸው ይታያል። በጋዜጣ ጭምር አሳውጀው የሚያስቀይሩ አሉ። እናንተም የምታውቁት ይኖራል። ከቤተሰብ ስም ወደ ፈረንጅ ስም ቲቲ፣ ቢቲ፣ ቦቢ የቀየሩም ብዙዎች ናቸው። ይሄም መብታቸው ነው። ነገር ግን በስምህ ማፈር፣ መሽኮርመም፣ መደበቅ የለብህም። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው ጋላ የነገድ ስም እንጂ ስድብ አይደለም።

• የተከበሩ አቶ ጋሻየለህ ጋላ… ይቀጥሉ።