Get Mystery Box with random crypto!

ስማማ ልንገርህ…! '…የኢትዮጵያ ወታደር ማለት ይሄ ነው። አምቡላንስ፣ ሃኪም፣ መኪና በሌለበት የ | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ስማማ ልንገርህ…!

"…የኢትዮጵያ ወታደር ማለት ይሄ ነው። አምቡላንስ፣ ሃኪም፣ መኪና በሌለበት የተጎዳ ወንድሙን ተሸክሞ ነፍስ ለማዳን ዋጋ የሚከፍል። የማይሮጥ፣ በፈንጅ ላይ የሚንጎማለል፣ ሻማ ሆኖ ቀልጦ ለሌሎች የሚያበራ ፀሐይ ማለት ነው። ዓድዋ ትመስክር።

"…ኢትዮጵያን ሲኦል ድረስም ቢሆን ሄጄ አፈርሳታለሁ ለሚል ኃይል እንዴት ይሮጣል? እንዴት ይሸሻል? የኢትዮጵያ ወታደር ሆኖ፣ የአሸናፊዋ ሃገርን ማሊያ ለብሶ እንዴት ጦሩን ሙሉ ለጠላት እጃችንን እንስጥ ብሎ ይቀሰቅሳል? ምን አይነት አሰልጣኝ ቢያሠለጥነው ነው። ከየት ያገኘው ባህል ነው?

"…የምትሮጥለት ጠላት እኮ አለ። የምትሸሽለት፣ ትንሽም እንኳ አፈግፍጌ ጮቤ ላስረግጠው የምትለው ጠላት አለ። እንዴት ሰው ለወያኔ ይሮጣል? እንዴት ለህወሓት ይሮጣል? ይሄ በእውነት ነውር ነው።

"…በውጊያ መሃል መሞት፣ መማረክ፣ መግደል፣ መማረክም አለ። እሱ ተፈጥሮአዊ ነው። ጥይት ስትጨርስ፣ ግኑኝነት ሲቋረጥ፣ መሪህ ሲመታ፣ ሲሰዋ፣ በቆረጣም፣ በፈለጣም፣ አቅጣጫም ጠፍቶብህ ልትማረክ ትችላለህ። ነገር ግን ለመማረክ መሰለጠን እሱ ገገማነት፣ መቶ ኪሎ ሰገጤነት ነው።

"…ሴራም ይኑር ስሪያ… ኢትዮጵያ ግን ታሸንፋለች…!! አከተመ።