Get Mystery Box with random crypto!

ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፦ '…ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ'ማቴ 10፥ 3' | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

ማክሰኞ ቶማስ ይባላል፦

"…ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ"ማቴ 10፥ 3" ጌታ ለሐዋርያቱ በዝግ ቤት በተገለጸላቸው ወቅት ከሐዋርያቱ ጋር አልነበረም። የስሙ ትርጓሜ በአራማይክ ዲዲሞስ ጨለማ ኋላ ቶማስ ብርሃን በግሪክም መንታ ማለት እንደሆነ ይነገራል። በዮሐ20÷24 ላይ። በሐዋርያነት ዘመኑ ክርስቶስን ሲከተል በተስፉ መቁረጥ ውስጥ የሚገጥምን ድፍረት ዮሐ11÷8-16፣ አለማስተዋልን፣ ዮሐ14፥5፣ መጠራጠርም ይታይበት የነበረ ሐዋርያ ነበር። ዮሐ 20፥ 24-25።

"…ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ሐገረ ስብከቱ በሕንድ እና በፋርስ ነበር። የቶማስ የጌታን ጎን መንካት እና መዳሰስ የክርስቶስን ምሥጢረ ቁርባን መፈተት የሚችሉት እና የተፈቀደውም ለካህናት ብቻ መሆኑን፣ ቅዱስ ዮሐንስም በእጃችን ዳሰስነው እንዳለ። ሉቃ 24፥39: 1ኛ ዮሐ 1፥1። በዕለተ ትንሣኤ ጌታን ቀድማ ያየችውን ማርያም መግደላዊትን አትንኪኝ ማለቱ ለሴቶች ሥጋውን ደሙን መፈተት እንዳልተፈቀደላቸው ሊቃውንት ያስተምራሉ። ዮሐ 20፥17፥

"…የቅዱስ ቶማስ የክርስቶስን ጎኑን መለኮቱን የዳሰሰች እጁ በሕንድ ሀገር ከመንበር የምትኖር ተቀምጣ የምትኖር ሲሆን በዓመት በእመቤታችን በዓል በአስተርእዮ ዕለት ካህናቱ ሊያጥኑ ሲገቡ የሚሾመው ሰው ተባርኮበት ከአገልግሎ ያርፉል ይባላል። ቅዱስ ቶማስ የእመቤታችንንም እርገት ከሐዋርያቱ ጋር ያላየ ነገር ግን ከሐገረ ስብከቱ ከህንድ ሲመለስ በደመና ላይ ከእመቤታችን የተገናኘ ሐዋርያ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ግንቦት 26 ሰውነቱን እንደፍየል ተገፎ በሰማዕተነት ያረፈ ሐዋርያ ሲሆን ዛሬ ስንዘክረው እንድንውል ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ሥርዓት ሠርታልናለች።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም።