Get Mystery Box with random crypto!

ዋናው ሁሉም መንቃቱ ነው…! '…እንደ እብድም፣ እንደ ወፈፌም፣ እንደ ጋጠወጥም፣ እንደ ባለጌም፣ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

ዋናው ሁሉም መንቃቱ ነው…!

"…እንደ እብድም፣ እንደ ወፈፌም፣ እንደ ጋጠወጥም፣ እንደ ባለጌም፣ እንደ ነጭ ዱርዬም፣ እንደ አደገኛ ቦዘኔም፣ እንደ ክብረቢስ፣ እንደ ጋጠወጥም፣ እንደ አሳዳጊ የበደለው፣ አግድም አደግም፣ እንደ ተናካሽ ውሻም ጩኸን፣ ሁነን፣ ብቻ በመጨረሻ አብዛኛው ሰው መንቃቱ ነው። ዋናው እሱ ነው።

"…ሁሉም ከነቃ በኋላ መፍትሄው ቀላል ነው። ገበሬው ከነቃ፣ ወታደሩ ከነቃ፣ ቤርቤረሰቡ ከነቃ፣ ተማሪው፣ አዝማሪው ከነቃ ሌላው ቀላል ነው። ችግር የነበረው ሁሉም እኩል ያለመንቃቱ ነበር። አሁን ሁሏም በአንድም ቤላው ስለተሸነቆጠች፣ ስለተዠለጠች የደፈረ በአደባባይ፣ ያፈረ፣ የፈራ ቦቅቧቃው በጓዳው ላይ ጓ ማለቱ እውነት ነው። ሃቅ ነው።

"…የቀረ ካለ በደንብ ይዠለጥ፣ ቤቱም አናቱም ይፍረስ፣ መስጊዱም ቤተ ክርስቲያኑንም ይናድ፣ ምሁር መሃይሙ፣ ይፈናቀል፣ በጀማ በጅምላ ከርቸኬ ይውረድ፣ ይለብልበው፣ ይዠልጠው፣ ዋይ ዋይ ያስብለው። ገበሬው ማዳበሪያ ይጣ፣ ይከልክለው፣ ሠራተኛ ደሞዝ ይጣ፣ የቤት ኪራይ የሚከፍለው ይጣ፣ ነዳጅ ይወደድ፣ እህል ጣሪያ ይንካ፣ ፍትሕ፣ ፍርድ በአናቱ ይተከል ያኔ የተኛው ይነቃል፣ ይነሣል።

"…አሁን እኛ እብዶቹ አርፈን አዳዲስ እብዶች አየሩን የሚሞሉበት ዘመን እየመጣ ነው። አሁን የእኛ የእረፍት ዘመን እየቀረበ ነው። ተራውንና አየሩን የሚቆጣጠሩ አዳዲስ ተናካሽ ውሾች እየመጡ ስለሆነ ቦታ ስፍራውን እንለቅላቸዋለን። የሥርዓቱ ወዳጅ፣ አሽከር፣ ባሪያ፣ አቃጣሪ፣ አቶስቷሽ፣ አለቅላቂ የነበሩ ገረዶች አሁን ተዠልጠው ጓ ብለው እየመጡ ነው። እኛ ደግሞ ገለል እንልላቸዋለን።

"…ትግሉን ማን ይምራው የሚሉ አሉ። ትግሉን ጠኔ የጠናበት፣ ራብ የጸናበት፣ ናላው የዞረ የሆነ ድንባዣም የሆነ ቀን ይመራዋል። ዋናው እንኳን ነቃችሁ። እንኳን ባነናችሁ። ይሄ ነው።

"…አይደለም እንዴ?