Get Mystery Box with random crypto!

'…ትልቁ ድል የምለው በክፍት ቦታዎች ላይ በኦሮሚያ እና በደቡብ በአፋጣኝ ሰው ይሾምባቸዋል ተባለ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

"…ትልቁ ድል የምለው በክፍት ቦታዎች ላይ በኦሮሚያ እና በደቡብ በአፋጣኝ ሰው ይሾምባቸዋል ተባለ እንጂ፣ እስከአሁን ኦሮሞ፣ ጉራጌ ይሾማል አልተባለም። ኮሚቴው አብዛኛው በኦሮሙማው መንፈስ የተሳበ ቢሆንም እሱ ግን ወሳኝ አይደለም። አሁን እንደማየው ከሆነ አቡነ ዮሴፍ የሉበትም። አቡነ ማቴዎስን ግን አያለሁ። የሰሜን ሸዋው ተወላጅ አቡነ ማቴዎስ የኦሮሙማው ደጋፊ ናቸው ይባላል። በግብግቡ ወቅት ሁሉንም አጋፍጠው እርሳቸው ወደ ሲውዘርላንድ የፈረጠጡ፣ በዚያም ቆይተው ኦሮሞዎቹ መሸነፋቸውን ሲያረጋግጡ ነገር ካለፈ ከበረደ በኋላ የተመለሱ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ሌሎቹ አስመራጮች አብላጫ ድምጽ ያላቸው በሙሉ ግን ኦሮሞዎቹ ናቸው። ኦሮሞ ሆነ ጉራጌ፣ ትግሬ ሆነ ዐማራ ግን የኮሚቴው ሥራ መርጦ ማቅረብ ነው። አጽዳቂው ቋሚ ሲኖዶሱ ነው። ይሄ ቀመር ሴራ ቢኖርበትም አንድ እርምጃ ወደፊት ቀድመን ማሰብ ከቻልን ሴራውን ብትንትኑን ማውጣቱ ቀላል ነው። እኔ የራሴን መዶሻ ይዤ እየጠበቅኩ ነው። እናንተም ተዘጋጁ።

"…አሁን ባለው ቦለጢቃ ምዕራብ ሸዋ እና ጅማ የሃገረ መንግሥቱን ቁልፍ ቁልፍ ሥፍራዎች በመያዝ በአንደኝነት እየመሩ ነው። ልክ እንደ ዘመነ ወያኔ በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በሃይማኖት ዓድዋዎቹ አጥለቅልቀው እንደነበሩት ማለት ነው። አሁን ደግሞ የላይኛውን የሥልጣን፣ የኢኮኖሚና የሃይማኖት ወሳኝ ክፍል ጅማ እና ምዕራብ ሸዋ ናቸው የተቆጣጠሩት ሲሆን ፍርፋሪው ለአሩሲ፣ ለባሌና ለሃረርጌ ኦሮሞ እስላሞች ነው የተሰጠው። በተለይ መስጊድ እና ቤተ ክርስቲያን ፈረሳው። ጅማዎች በእስላሙ አቢይ አሕመድ አማካኝነት ሀገረ መምግሥቱን በሀጂ ኢብራሂም ቱፋ አማካኝነት እስልምናውን ተቆጣጥረውታል። ከሥር የጅማዎቹ እነ አህመዲን ጀበልም እስልምናውን እንዲቆጣጠሩት ተደርጓል። ፕሮቴስታንቱ ኦሮሞ ገና አልለየለትም። የባሌው፣ የኢሉአባቦር እና የወለጋው ክንፍ እየተጠዛጠዘ ነው። በፓስተር ጻድቁ በኩል ባሌ የሚያሽንፍ ይመስላል።

"…ወደ ኦርቶዶክስ ስንመጣ የኦሮሙማው ቡድን ፓትርያርክ መሆን ያለበት ከምዕራብ ሸዋ ነው ብለው ወስነዋል። ወለጋ ጴንጤ ነው። ጅማ እስላም ነው። ሸዋ ኦርቶዶክስ ነው። ስለዚህ በድልድሉ መሠረት ፕትርክናው ከሸዋ መሆን አለበት ነው የሚሉት ኦህዴድኦነግ ብልጽግናዎቹ። ዐማራ ቢሆኑም እነ አቡነ ማቴዎስ፣ አቡነ ቀለሜንጦስ ተሿሚው ከሸዋ ይሁን እንጂ ኦሮሞ ቢሆንም ግድ የለንም። ብቻ ፕትርክናው ከትግሬ ወጥቶ ዐማራ እጅ ያውም ጎንደር፣ ጎጃምና ወሎ እጅ መግባት የለበትም ባይ ናቸው። ምዕራብ ሸዋ ማለት ደግሞ የኦሮሞ ፕሬዘዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ ደመላሽ ገ/ሚካኤል፣ ባጫ ደበሌ፣ አዳነች አቤቤም አሩሲ ትወለድ እንጂ መሠረቷ ምዕራብ ሸዋ ነው፣ የእነ ታከለ ኡማ የትውልድ ሃገር ነው። እናም አሁን ምዕራብ ሸዋ የፓትርያርክነቱን ሥፍራ ይፈልጋል።

"…የምዕራብ ሸዋው ቡድን መጀመሪያ በምዕራብ ሸዋው ጠበቃ ኃይለሚካኤል ታደሰ በኩል የመረጧቸው ሦስቱ ጳጳሳት ማለትም ሳዊሮስ፣ ኤውስጣቴዎስ እና ዜናማርቆስ ጋለሞታ፣ ሸርሙጣና ነውረኛ ሆነው መገኘታቸው ከባድ ኪሳራ ላይ እንደጣላቸው ተረዱ። በተለይ ኃይለሚካኤል ሸርሙጣ ጋለሞታውን ወንድኛ አዳሪ ይታገሱ፣ ይቴ ጭሷን እኔ ጋር ፋይል እንዳለው ሳያውቅ ለጵጵስና መምረጡ እጅግ ከባድ ዋጋ አስከፍሎታል። ልብ በሉ ይታገሱም የምዕራብ ሸዋ የአድአበርጋ ሰው ነው። ይቴ ጭሱ ለጅማ ነበር የተሾመው። ከዚያ ያ ሲያከስራቸው አሁን በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የሆነ ሰው ፈልገው መቀየር እንዳለባቸው ወሰኑ። ወሰኑና በአቋማቸው ጽኑ የነበሩትን ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን አገኙ። እናም ኦሮሞ ያውም የጀልዱ የምዕራብ ሸዋ ሰው ለፓትርያርክነት የሚታጭ አገኙ ማለት ነው። ጾሯ ስላለች አቡኑም የምንኩስና የመጨረሻ ጣሪያ የሆነችው ዕድል ከመጣችማ ለምን አልፋታለሁ ብለው ተንበረከኩላት። አፈገፈጉም። ለዚህ ነው ሽመልስ በአቡነ ናትናኤል ልብ ላይ "ሳናግዝዎት" ብሎ የተጎዘጎዘው።

"…ቀጣዩ ፈተና ሲያዩት ከባድ ይመስላል። ከተባበርን፣ አንድ ከሆን፣ ከጸለይን፣ ከደፈርን፣ እንደነሱ ሼምለስ ከሆን፣ እንደ ርግብም የዋህ፣ እንደ እባብም ተናዳፊ ኮብራ ከሆን ፈተናው እጅግ ሲበዛ ቀላል ነው። አሁን ኮሚቴው ዕጩ ተሿሚዎቹን መርጦ ለቋሚ ሲኖዶሱ ነው የሚያቀርበው። ቋሚ ሲኖዶሱ ደግሞ አይቶ እና ገምግሞ፣ አጣርቶ ለዋናው ሲኖዶስ የሚያሳልፈው። የእኛ ሥራ የሚሆነው ቋሚ ሲኖዶሱ በኮሚቴዎቹ የታጩትን ግለሰቦች ስምና ፎቶ ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ ብቻ ነው የምንጠይቀው። ዕጩው መነኩሴ በፈለገው ሰው ይታጭ የልቡን መንፈስ ቅዱስ ይመርምረው በሥጋው ግን ከእኔ ከዘመዴ የባሰ ሸርሙጣ፣ እንደ ይታገሱም ጋለሞታ፣ እንደ እነ ኤውስጣቴዎስም ሰርተፍኬት ያለው አመንዝራ ነውረኛ ከሆነ አንፈልገውም እንላለን። ሕይወቱ፣ ዕውቀቱ፣ ትምሕርቱ፣ አገልግሎቱ በሰው ዘንድ የተመሰገነውን፣ ነውርና ነቀፋ የሌለበትን ደግሞ ዕጩው አልሾምም እንኳ ቢል እጅ እግሩን አስረን በግድ ተሾምብን እንለዋለን። ይህ ይደረግ ዘንድ ከወዲሁ መወትወት አለብን። አለበለዚያ ሉጢው፣ ክብሪቱ፣ እስላምና መናፍቁ ሁሉ ተሹሞ ይላገድብናል።

"…እስከ ሐምሌ የሚፈጠረውንም ዐናውቅም። የተለየ ነገር በሃገሪቱ ሊከሰትም ይችላል። ብቻ ከእኔ የሚጠበቀውን ስነግራችሁ ከበፊቱ የበለጠ ደረጃ አንድ ክፍት አፍ ባለጌ፣ አሳዳጊው የበደለው ሳይሆን ራሱን የበደለ ስድ አደግ መሆን ነው። ከእኔ የሚጠበቀው ይሄ ብቻ ነው። አንድማ እብድ በቤታችን የግድ ነው። አይደለም እንዴ? አሁን በቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት ውስጥ በግለሰብ ደረጃ ነውረኞች እንደሞሉበት እናውቃለን። በመንበረ ፓትርያሪክ ግቢ ውስጥ ጳጳስ ሆኖ መነኩሲት አስገድዶ ደፍሮ አስወልዶ የተቀመጠ እንዳለም እናውቃለን። በሴት ሠራተኛ ስም ሁለት ሚስት በቤቱ ያስቀመጠ ነውረኛም እንዳለ፣ ከአሜሪካ በሽርሙጥናው ምክንያት የተባረረ፣ የቴክስት ሚሴጁን ወፎቼ ጠልፈው የሰጡኝን ወራዳ ሰው መሳይ በሸንጎ ባሰማችሁ ጉድ ነው የምትሉት። የፎን ሴክስ አድራጊውን ድምፁን በማርያም ብዬ ለምኜ ያስቀረሁትም እኔ ነኝ። ስለዚህ እኔ በበኩሌ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም እንደሚባለው የፈለገው ይምጣ አይደለም ሲኦል የሲኦል አጎት ለምን አልገባም ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን ያልቆመውን አባት እንደ አባት ቆጥሬ አልጠራውም። በግልፅ እዋጋዋለሁ። እሱም፣ እኔም ለቤተ ክርስቲያን እኩል ነን። የሚበልጠኝ በሥልጣነ ክህነት ብቻ ነው። ለቤተ ክርስቲያኒቱ ጥብቅና በመቆም በኩልም ቢሆን ሁለታችንም እኩል መብት እና ሓላፊነት ነው ያለን። ስለዚህ ማንም ምንም አባቱ አያመጣም። በሃገሬ እና በሃይማኖቴ ቀልድ ብሎ ነገር የለም። በሁለቱ የመጣብኝን አልፋታውም። ሃላስ።

"…ጊዜው ሲደርስ የተሸፋፈነውን እገልጠዋለሁ። ሌባውንም፣ ዘራፊ ሸርሙጣ ወንድኛ አዳሪውንም አጋልጠዋለሁ። የአክስቴ ልጅ፣ የአጎቴ እያለ በቤቱ በሠራተኛ ስም ከአንድም ሁለት የጭን ገረድ ያስቀመጠውን ነውረኛ ሸርሙጣ ሁላ እዋጋዋለሁ። በባንክ ብር ያከማቸውን፣ ወልዶ ልጆቹን የሚያስተምረውን፣ ሉጢውን፣ የስልክ ወሲብ አድራጊውን፣ ሱዳን ድረስ ሄዶ የስንፈተ ወሲብ መድኃኒት አስቀማሚውን፣ ቅንዝረኛ፣ መናፍቅ፣ እስላሙን፣ ከየገዳሙ እሸት እሸት የመሰሉ እምቡጥ መነኮሳትን አዲስ አበባ አምጥቶ በቤተ ክህነቱ የኪራይ ቤት አስቀምጦ የወሲብ ባርያ ያደረገውን ሁሉ ነውሩን የሸፈነችለትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አዋርጄ እኔ ከብሬ እኖራለሁ ካለ ወንድ እናቱ ወልዳዋለች። ዘሪሁን ሙላት በማስረጃ የነገረኝን፣ የሰጠኝን አቡነ ክብሪትንም… ከታች ይቀጥላል።