Get Mystery Box with random crypto!

ሰኞ ጠዋት! ሰኔ 12/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች 1፤ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በደቡብ ክልል | Zemedkun Bekele (ዘመዴ)

ሰኞ ጠዋት! ሰኔ 12/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች

1፤ ምርጫ ቦርድ ዛሬ በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን በድጋሚ የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ያካሂዳል። ቦርዱ ሕዝበ ውሳኔውን ዛሬ በድጋሚ የሚያካሂደው፣ ቦርዱ ባለፈው ጥር 29 በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች የክልልነት ሕዝበ ውሳኔ ማካሄዱ ይታወሳል። ኾኖም ቦርዱ የወላይታ ዞን ሕዝበ ውሳኔ ሂደት የሕግ ጥሰት ተገኝቶበታል በማለት ውጤቱን ሙሉ በሙሉ በመሰረዙ ነው ሕዝበ ውሳኔው በድጋሚ የሚካሄደው። ቦርዱ በዞኑ ለሚካሄደው ሕዝበ ውሳኔው 1 ሺህ 812 ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ማዘጋጀቱን ገልጧል።

2፤ የኢትዮጵያ የስደተኞች ጉዳዮች ቢሮ የዓለም ምግብ ፕሮግራምና የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት የምግብ ዕርዳታ በማቋረጣቸው በአገሪቱ የተጠለሉ ስደተኞች ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን መናገሩን ሪፖርተር ዘግቧል። በተለያዩ የስደተኛ መጠለያ ካምፖች የተጠለሉ 1 ሚሊዮን ስደተኞች የምግብ እርዳታ እንደተቋረጠባቸው የቢሮው ዋና ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ መግለጣቸውን ዘገባው ጠቅሷል። ከሱማላላንዱ ግጭት የተሰደዱ ከ91 ሺህ በላይ ስደተኞች በሱማሌ ክልል የተጠለሉ ሲኾን፣ ከሱዳን ግጭት የሸሹ ከ10 ሺህ በላይ ሱዳናዊያንና ኤርትራዊያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደገቡ የተመድ መረጃዎች ያመለክታሉ።

3፤ የሱማሊያ መንግሥት በተያዘው ወር አፍሪካ ኅብረት ከአገሪቱ በከፊል የሚያስወጣቸውን ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ለመተካት 20 ሺህ ወታደሮችን ማዘጋጀቱን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። አፍሪካ ኅብረት ከተያዘው ወር ጀምሮ በጥቂት ወራት ውስጥ ኹለት ሺህ ወታደሮችን ከሱማሊያ ለማስወጣት አቅዷል። ሱማሊያ የኅብረቱ ወታደሮች ሲወጡ የጸጥታ ክፍተቱን የሚሞሉት 20 ሺህ ወታደሮች፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ እና ኡጋንዳ ያሰለጠኗቸው እንደኾኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሐምዛ ባሬ መናገራቸውን ዘገባዎች ጠቅሰዋል። ኅብረቱ በአውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2024 ዓ፣ም ኹሉንም ሰላም አስከባሪ ወታደሮቹን ከአገሪቱ የማስወጣት እቅድ አለው።

4፤ ኹለቱ የሱዳን ተፋላሚ ወገኖች ሌላ የ72 ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደርሰዋል። አዲሱ የተኩስ አቁም ስምምነት ከዛሬ ንጋት 12 ሰዓት ጀምሮ ተግባራዊ ይኾናል። እንደካኹን ቀደሙ ኹሉ ተፋላሚዎቹ ወገኖች ከአኹኑ ተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ያስቻሉት፣ የሳዑዲ ዓረቢያና አሜሪካ አደራዳሪዎች ናቸው።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ


t.me/emsmereja
t.me/emsmereja
t.me/emsmereja