Get Mystery Box with random crypto!

ምሷን አግኝታለች…! እነሆ በቪዲዮ (እግዚአብሔር ታላቅ ነው…!) '…የማስታውሳት በሁለት ክስ | ....

ምሷን አግኝታለች…! እነሆ በቪዲዮ
(እግዚአብሔር ታላቅ ነው…!)

"…የማስታውሳት በሁለት ክስተቶቿ ነው። አንደኛው በቅሪላ ገፊነቷ  ሲሆን ሌላው ደግሞ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ትገነጠል ዘንድ እነ መለስ ዜናዊ የተባበሩት መንግሥታት ድረስ ደብዳቤ ማመልከቻ ይዘው በሄዱ ጊዜ፣ በተባበሩት መንግሥታት ዋና ከነበረው ከግብጻዊው ቡትሮስ ቡትሮስ ጋሊ እግር በተደፉ ጊዜ ብራዚል ነበረች እንደ ደመኛችን በኤርትራ መገንጠል ከወያኔ ጋር በብዙ የደከመችው። ምን አስባ እንደነበር ግን መድኃኔዓለም ይወቅ። ጥሎብኝ የብራዚል ቅሪላም ቅሪላ ተጫዋችም ስበውኝ አያውቁም።

"…ሰሞኑን ደግሞ ብራዚሎች ጣሪያ ነክተው ቀብጠው ነበር። እንደተለመደው ዓመታዊውን ካርኒቫላቸውን ከወትሮው በተለየ መልኩ አክብረዋል። ካርኒቫሉን ልዩ ያደረገውም በዘንድሮው ካርኒቫል ሰይጣንን ዲያብሎስን በግልጽ አምላካችን ብለው ያነገሡት መሆኑና በአንጻሩ ደግሞ በአስደንጋጭ ሁኔታ ባልተለመደ መልኩ ጴንጤና ካቶሊክ በሚበዛበት ሃገር በጌታችንና በመድኃኒታችን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የሌለ መሳለቃቸው ነበር። በሰይጣን የተወከለ ሰው በኢየሱስ የተወከለን ምድር ለምድር ሲጎትተውም ታየ። ሎቱ ስብሃት ቀለዱበት፣ አፌዙበትም። 

"…ተሳቀላቸው፣ ተጨበጨበላቸው። መጀመሪያ ጴንጤ አደረጉት። ከዚያ ደፋር አደረጉት። ድፍረታቸው ከጣሪያ ዘለለ። ካርኒቫሉም አለቀ። ጭፈራው ቀጠለ። ነገር ግን ብራዚል ከሰማይ ከፀባኦት ፈጣን ምላሽ አገኘች። 24 ሰዓት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሃገረ ብራዚል ታሪክ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ አውሎ ነፋስና ጎርፍ ዋና ከተማዋን ሪዮ ዲጂኒዬሮን በአናቷ ተከላት። ምስቅልቅሏን አወጣት።“ክፋትን አርሳችኋል፥ ኃጢአትንም አጭዳችኋል፥ የሐሰትንም ፍሬ በልታችኋል፤ በኃያላንህ ብዛት፥ በመንገድህም ላይ ታምነሃልና።” ሆሴ10፥13

• ማነህ ተረኛ…?