Get Mystery Box with random crypto!

መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ     ሰኔ 30 የዓለም ብርሃን ለሆነው ባሕታዊ ፤ በክብረ ፈጣሪው ለ | ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿

መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ     ሰኔ 30

የዓለም ብርሃን ለሆነው ባሕታዊ ፤ በክብረ ፈጣሪው ለተከበበ ንዑድ ክቡር አባታችን ገባሬ ተአምራት ወመንክራት፤ ሴቶች ከወለዷቸው ቅዱሳን ወገን እሱን የሚበልጥ ማንም እንደሌለና እንደማይኖር አምላካችን በሕያው ቃሉ ለመሰከረለት እንቁ አገልጋይና ጽኑ የእውነት ሰማዕት ለሆነው፤ ክብሩ ማንነቱ ከኹሉ ለላቀው የክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የአዲሱ የምህረት ዘመን መሸጋገሪያ ድልድይ፡ የአሮጌው ብሉይ ዘመን ፍጻሜ ማኅተም ለሆነው መምህር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ ! እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሳችሁ ።

አባታችን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ፍጻሜው ወቅት "አቤቱ ጌታዬ ሆይ በቃል ኪዳኔ አምነው ስሜን የሚጠሩ መታሰቢያየን የሚያደርጉ ኃጥአንን ሁሉ ማርልኝ!" ብሎ በትህትና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በለመነው መሠረት...

ጌታችንም በማይታበለው የከበረ ቃሉ፦ በስሙ የተማጸነ፤ ዝክሩን ያዘከረ፤ መታሰቢያውን ያደረገ፤ ስሙን የጠራ በቃልኪዳኑ የታመነ፤ ወዘተ... ወዳጆቹንም በወር በወር የበዓሉ መታሰቢያ ዕለት በውሃ ላይ ገድሉን አንብበው ቢጠመቁ ወር እስከ ወር የሰሩትን ኃጥአት ይቅር እንደሚላቸው...

ያም ባይሆን መስከረም 2፤ ሰኔ 30 በአመታዊ ክብረ በዓሉ ገድሉ በተነበበበት ማየ ጸሎት (ውሃ) አምኖ፣ ታምኖ፣ ተማጽኖ፣ በሠራው ኃጢአት አዝኖ ተጸጽቶ የተጠመቀ ማንም ይሁን ማን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ከዓመት እስከ ዓመት የፈጸመው ኃጢአቱ ቀልጦ ጠፍቶለት ያለወቀሳ ያለ ከሰሳ ሰተት ብሎ መንግሥተ ሰማያት እንዲገባ ይህንንና የመሳሰለውን ቃልኪዳን ከአምላኩ ተቀብሏል።

ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው በእምነትና በእውነት ሲጠቀሙበት ነውና እንደቃልኪዳኑ ኖረን በቃልኪዳኑ ለመጠቀም ያብቃን! አሜን።
.ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን
╔═★══════════ ══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══ ══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ