Get Mystery Box with random crypto!

ለሞቷ ግብጽ እንዴት ነው ጌታዬ የግድቡ ነገር ኢትዮጵያን ለማስቆም እርዱኝ ብዬ ነበር አሜ | የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል

ለሞቷ

ግብጽ
እንዴት ነው ጌታዬ
የግድቡ ነገር
ኢትዮጵያን ለማስቆም
እርዱኝ ብዬ ነበር

አሜሪካ
በቃሌ መሰረት
ልረዳህ ወስኜ
የሚሳካ መስሎኝ
በራስ ተማምኜ
ኑ ፈርሙ ብዬ
ላስገድድ ብጣራ
እምቢ ብለው ቀሩ
ሰረዙ በረራ

ግብጽ
ታድያ ምን ወሰኑ
እንዲህ ሲዳፈሩ
የእርሶ መቺው ሀይል
አልሰማም ወይ ጦሩ

አሜሪካ
ቀላል አይምሰልህ
ኢትዮጵያ ላይ መዝመት
ፈጣሪ ጭምር ነው
አብሮ የሚዋጋላት

ደደደደግሞ

አለም ይወቅሰኛል
መብታቸውን ብጥስ

ግብጽ
እኔ ግን አልተውም
እስከመጨረሻ
ጦሬን አዘምታለው
ግድቡን ማፍረሻ

አሜሪካ
አትሞክር ወዳጄ
ይከፋል መዘዙ
አይለቁም ሀበሾች
ጦር ከተማዘዙ

በእዛ ላይ!
ሀይሎችህ ግድቡን
በአየር ቢመቱ
ካይሮን ያጠፋል
የውሀ ሙላቱ

ግብጽ
ታድያ ምን ይሻላል
ምን ላድርግ አለቃ
እጄን አጣጥፌ
መቀመጥ ነው በቃ?!

አሜሪካ
ተናዳፊ ንቦች
ከሚያሳጡህ ፋታ
ሳትዋረድ አቁም
ይሻላል ዝምታ
የአድዋን ታሪክ
አስታውስና ዛሬ
'ሚበጅህን ምረጥ
ብስሉን ከጥሬ

ይቀጥላል ግጥሜ
ዘማሪ ትንሣኤ

ሼር ይደረግ
ለመቀላቀል

t.me/zemaritnsae