Get Mystery Box with random crypto!

@zemariann ትህትና በአባቶቻችን አባታችን አባ እንጦስ ስለ ርኩሳን መናፍስት ሲናገር | መዝሙረ ማኅሌት ቁ፪


@zemariann
ትህትና በአባቶቻችን

አባታችን አባ እንጦስ ስለ ርኩሳን መናፍስት ሲናገር በትዕቢታቸው ምክንያት የወደቁትን ርኩሳን መናፍስት በትዕቢት ልታሸንፋቸው አትችልም ራስን በማዋረድ ግን ድል ትነሳቸዋለህ። ቅዱሳን ይህን መንገድ ተጠቅመውበታል ድልም ነስተውበታል።

አባ እንጥስ ርኩሳን መናፍስት ወደ እርሱ ሲቀርቡ'' እናንተ ሃያላን ስትሆኑ እንደ እኔ ላለው ደካማ ሰው ለምን ትፈልጋላችሁ'' በማለት ከጠየቃቸው በኋላ '' እኔ ከእናንተ መካከል በጣም ታናሽ ከሚባለው ከአንዱ ጋር ለመዋጋት እጅግም በጣም ደካማ ነኝ።'' ብሏቸዋል ከዚህ በኋላ ግን ይህ ቅዱስ ሰው '' አቤቱ ጌታዬ ሆይ ! እኔን ባለ ዋጋ አድርገው ከሚቆጥሩት ከእነዚህ ከርኩሳን መናፍስት እጅ አድነኝ ''

ብሎ ጮኋል በዚህ ጊዜ ይህን ጸሎቱንና ጩኸቱን የሰሙትን እነዚያ ርኩሳን መናፍስት ከአጠገቡ እንደ ጉመ በነው ጠፉ።

በአንድ ወቅት ደግሞ ይኸው አባ እንጦስ የርኩሳን መናፍስት ወጥመድ በምድር ሁሉ ላይ ተጠምዶ ከተመለከተ በኋላ አቤቱ ጌታዬ ሆይ! ከእነዚህ ወጥመዶች ማን ሊጃመልጥ ይችላል ? በማለት ጌታን ይጠይቀዋል #ትኁት #የሆነ #ሁሉ #ያመልጣል። የሚል ከአርያም መጥቶለታል።

የአባቶቻችን በረከት በሁላችንም ላይ ይደር። አሜን።

ፀሐፊ ሱራፊ

በአያሌው ዘኢየሱስ 'ተራራው ስብከት'