Get Mystery Box with random crypto!

#ግንቦት_፩ #ልደታ_ለማርያም ከሐምሌ 7ቱ @zemarian | መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል

#ግንቦት_፩ #ልደታ_ለማርያም
ከሐምሌ 7ቱ
@zemarian
#ክፍል ፩
ጴጥርቃ እና ቴክታ የሚባሉ ቅዱሳን ሰዎች በኢየሩሳሌም በአንድነት ተጋብተው ይኖሩ ነበር:፡እነዚህም በእግዚአብሔር የሚያምኑ የተወደዱ ጻድቃን ደግ ሰዎች ነበሩ:፡ እነዚህም ሰዎች በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የበቁ ባለጸጎች ነበሩ:፡ ነገር ግን የሚወርሳቸው ልጅ አልነበራቸውምና መካን ነበሩ:፡አንድ ቀን ጴጥርቃም ቴክታን እኅቴ ሆይ ይህን ሁሉ የሰበሰብነውን ገንዘባችንን ምን እናደርገዋለን ሀብታችንን ልጅ የለን የሚወርሰን:፡ አንቺም መካን ነሽ እኔም ካንቺ በቀር ሌላ ሴት አላውቅም አላት:፡እርሷም ወንድሜ ሆይ አምላከ እስራኤል ለኔ ልጅ ቢነሳኝ አንተም እንደኔው ሆነህ ትቀራለህን? ከሌላ ደርሰህ ውለድ እንጂ ብላ ብታሰናብተው እንደዚህ ያለ ነገር እኳንስ ላደርገው በልቦናዬ እንዳላስበው አምላከ እስራኤል ያውቅብኛል አላት:፡ እሷም አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን የሚያውቅ የለም ትላንትና ማታ በህልሜ ነጭ ጥጃ ከማህጸኔ ስትወጣ ያችም ነጭ ጥጃ ሌላ ነጭ ጥጃ ስትወልድ እንዲሁ እስከ 7ት ትውልድ ሲዋለድ ሰባተኛይቱ ጨረቃን ስትወልድ ጨረቃዋም ፀሃይን ስትወልድ አየሁ አለችው:: እርሱም በጠዋት ከህልም ፈቺ ዘንድ ሂ የነገረችውን ሁሉ ነገረው:፡ ያም ህልም ፈቺ እግዚአብሔር በምሕረቱ አይቷችሇል በሳህሉ መግቧችሁአል 7 አንስት ጥጆች መውለዳቹ 7 ሴቶች ልጆችና የልጅ ልጆች ትወልዳላቹ ከቤታቹ ሰባተኛይቱ ጨረቃ መውለድዋ ከሰው የበለጠች ከመላእክትም የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹ የፀሃይ ነገር ግን አልታወቀኝም አለው:፡ እርሱም የነገረውን ሁሉ ሄዶ ነገራት እርሷም እንጃ አምላከ እስራኤል የሚያደርገውን ማን ያውቃል ብላ ዝም አለች:ከዛም ፀንሳ በ9 ወሯ ሴት ልጅ ወለደች:፡ ስሟንም #ሄሜን ብለው አወጡላት:፡ ሄሜንም አድጋ ለአካለ መጠን ስደርስ አጋብተዋት ሴት ልጅ ወለደች በስምንተኛ ቀኗም #ደርዲ ብለው ስም አወጡላት: ደርዲም አድጋ እንዲሁ ሴት ወለደች እና #ቶና አለቻት:፡ ቶናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ #ሲካር አለቻት፤ ሲካርም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ #ሴትና አለቻት፤ ሴትናም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ #ሄርሜላ አለቻት፤ሄርሜላም እንዲሁ ሴት ልጅ ወልዳ ንጽሕት ቅድስት ክብርት የምትሆን እመቤታችንን የምትወልደውን #ሃናን ወለደች:: ይህቺም ሃና በስርዓት በቅጣት አደገች:፡ ለአእምሮ ስትበቃ አካለ መጠን ስደርስ ከቤተ መንግሥት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ እያቄም ጋር አጋቧት:: እነዚህ ቅዱሳን እያቄምና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት አይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች፡ እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲፀልዩ ውለው ከዘካርያስ ከሊቀ ካህናቱ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ ቤተ እግዚአብሔርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ ቀድታ መሶብ ወርቅ ሰፍታ መጋረጃ ፈትላ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ::ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማላቹ ስእለታችሁን ይቀበልላቹ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላቹ ብሎ አሳረገላቸው፡፡ ከዚያም በኃላ ቅድስት ሐናና ቅዱስ እያቄም ዕለቱን ራእይ አይተው ነገር አግኝተው አደሩ፡፡ ራእዩም እንዴት ነው ቢሉ ኢያቄም 7ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ አላት ወፍ የተባለው ጌታች መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ነጭነቱ ንጽሐ ባህሪው ነው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ ማለቱ የኢያቄምን ባህርይ ባህር እንዳደረገው እወቅ ሲል ነው 7ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባህሪው፣ ምልአቱ፣ ስፍኀቱ ፣ ርቀቱ፣ ልዕልናው መንግሥቱ ናቸው፡፡ ሐናም እኔም አየሁ አለችው ፡፡ ምን አየሽ ቢላት ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማህጸኔ ስትተኛ አየሁ አለችው::ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ነጭነቷ ፣ ንጽህናዋ፣ ቅድስናዋ ፣ ድንግልናዋ ነው፡፡ ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብስራተ ገብርኤል በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መፀነሷ ነው: ይህንኑም ራእይ ያዩት ሐምሌ 30 ዕለት ነው:: እነሱም እንዲህ ያለ ራእይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በምንጣፍ አንድ ሣይሆኑ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ የተናገረ አምላክ ለኛስ ይነግረን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ 7 ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ: ነሐሴ በባተ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ዓለሙ ሁሉ ተሰብስቦ ቢመዘን አንድ የራሷን ፀጉር የማያህል ደግ ፍጥረት ትወልዳላቹህና ዛሬ በምንጣፍ አንድ ሁኑ ብሎአችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለቅድስት ሐና ነገራት በፈቃደ እግዚአብሄር በብስራተ መልአክ #እመቤታችን_እግዝእትነ_ማርያም እሑድ ዕለት ተፀነሰች (በኦሪት ሥርዓት እሁድ ዕለት ባልና ሚስት መገናኘት ልማድ ነበርና እመቤታችን የተፀነሰች ዕለት አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው ቅናቱ እንዴት ነው ቢሉ ሳሚናስ የሚባል የጦሊቅ ልጅ ከኤዶቅ ካጎቱ ቤት ሄዶ ሞተ እነርሱም እንቀብራለን ብለው ባልጋ ይዘው ሲሄዱ ከመንገድ አሳረፉት የሐናም የአጎቷ ልጅ ነበርና ለማልቀስ ብትደርስ ዘመዶቿ ሁሉ ተሰብስበው ሲላቀሱ ቆዩአት: እርሷም አብራ እየዞረች ስታለቅስ ጥላ ቢያርፍበት መግነዝ ፍቱልኝ ሳይል ብድግ ብሎ ተነስቶ #ስብሐት_ለኪ_ማርያም_እሙ_ለፀሐየ_ጽድቅ ለአብ ሙሽራው ለወልድ ወላዲቱ ለመንፈስቅዱስ ጽርሐ ቤቱ ተፈስሒ ደስ ይበልሽ ብሎ ሰገደላት አይሁድ ከዛ ነበሩና ምነው ሳሚናስ ምን አየህ? ምን ትላለህ? ቢሉት ከዚች ከሐና ማህፀን የምትወለደው ኅፃን ሰማይ ምድርን እምቅ አየርን የፈጠረ አምላክ ትወልዳለች እያሉ መላእክት ሁሉ ሲያመሰግኗት ሰማሇቸው እኔንም ያነሳች የፈወሰችኝ ያዳነችኝ እርሷ ናት አላቸው በል ተወው ሰማንህ ብለው ቅናት ጀመሩ:: እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ9 ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ #ዕለት_ግንቦት_፩ተወለደች

#ምንጭ\ነገረ_ማርያም
......