Get Mystery Box with random crypto!

☦ ዝማሬወመዋስዕት ☦🔈🔈

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarewoch — ☦ ዝማሬወመዋስዕት ☦🔈🔈
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemarewoch — ☦ ዝማሬወመዋስዕት ☦🔈🔈
የሰርጥ አድራሻ: @zemarewoch
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 114
የሰርጥ መግለጫ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ
አሜን!!!
#ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬዎችና ትምህርቶችን እንዲሁም ምንባባተ ቅዳሴ(መፅሐፈ ግፃዌ )
ለማግኘት #Join ብለዉ ይቀላቀሉ
ለማንኛውም አስታየት ጥያቄ
@Mahetebane_albetsem

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-04-24 15:00:46
#እምደተናገረ_ተነስቷል!!

ክርስቶስ ተንስአ እሙታን_በዓቢይ ኃይል ወስልጣን

አሰሮ ለሰይጣን__ አግአዞ ለአዳም

ሰላም__እምይእዜሰ

ኮነ__ፍስሐ ወሰላም።

መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንልን !!!


#ዲ ን እሱባለው (ሥሙር)

ሚያዝያ ፩፮

¶¶¶ ልዩ ልዩ የሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ትምህርቶች ፣መዝሙሮችን ፣ ግጥሞችን የሚፈልጉትን የመፅሐፍ ቅዱስን ቃል

ያገኛሉ • • • • ለመቀላቀል ለሌላም ሰው ለማጋራት

╔═══❖••❖═══╗

@DNEsuba @DNEsuba
@DNEsuba @DNEsuba
@DNEsuba @DNEsuba

╚═══❖••❖═══ ╝
44 viewsኢትዮጵያ ◁, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-22 21:10:18
ኦ አርምሞ ዘመጠነ ዝ አርምሞ ?
ኦ ትዕግስት ዘመጠነ ዝ ትዕግስት ?
ኦ ሂሩት ዘመጠነ ዝ ሂሩት ?
ኦ ፍቅር ዘመጠነ ፍቅረ ሠብ ?
( ይህን ያህል ትዕግሥት እንደምን ያለ ትዕግሥት ነው ? ይህን ያህል ዝመታ እንደምን ያለ ዝመታ ነው ? ይህን ያህል ሰውን ማፍቀር እንደምን ያለ ፍቅር ነው ?)
መጽሐፈ ቅዳሴ
37 viewsኢትዮጵያ ◁, 18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-20 21:05:47
43 viewsኢትዮጵያ ◁, 18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 17:36:59 ​​​​​​በሰሞነ ሕማማት የሚጸለዩት እና የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

ሼር በማድረግ ለወዳጆቻችሁ አድርሱ አሳውቁ!

ከነገ ጀምሮ የጌታችንን ሕማም የምናስብበት ሰሞን ነው። እንደ ቅድስት ቤተ-ክርስትያናችን ሥርዓት በዚህ በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸውና ለጊዜው የምንታቀባቸው ጸሎቶች አሉ።

በሰሞነ ሕማማት የምንጸልያቸው ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰሞነ ሕማማት አጥብቀን የምንጸልያቸው ጸሎቶች ውዳሴ ማርያም:ዳዊት: ሰይፈ ሥላሴ:ሰይፈ መለኮት:ድርሳነ ማሕየዊ ውዳሴ አምላክ ናቸው።

እመቤታችን ድንግል ማርያም በዚህ በሰሞነ ሕማም በልጅዋ ምክንያት ብዙ እንግልት ስለደረሰባት የእሷን ምስጋና የሆነውን ውዳሴ ማርያም አናስታጉልም። ውዳሴ ማርያም ማመስገኛ መማጸኛ ስለሆነ እንጸልያለን። ምክንያቱም በዚህ በሰሞነ ሕማማት መከራ ተቀብሎ ሞቶ ሕይወቱን የሰጠንን ጌታ በሥጋ ወልዳለችን በውዳሴዋ እናስባታለን።

የቅዱስ ዳዊት ድርሰት የሆነው ታላቁ መዝሙረ ዳዊት በትንቢት ክፍሉ ስለ ጌታችን ሕማም ስቃይ እና ሞት የሚናገርና በዳዊት ምስጋና በምድር የሰው ልጆች በሰማይ ቅዱሳን መላእክት ስለሚያመሰግኑ እንጸልየዋለን።

ሰይፈ ሥላሴ ከሦስቱ አካላት እግዚአብሔር ወልድን የሚያመሰግን አምላክነቱን የሚመሰክር እና የሚመሰጥር በመሆኑ እንጸልየዋለን።

ሰይፈ መለኮት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ስለ ምስጢረ መለኮት እና ስለ ጌታችን አምላክነት ስለሚናገር እንጸልየዋለን።

ድርሳነ ማሕየዊ በቅዱስ ዮሐንስ ወልደ-ነጎድጓድ የዓይን እማኝነት እና የቃል ምስክርነት የተጻፈና የጌታችንን መከራ ስቃይ እንግልት እና ሞት በልዩ ሁኔታ የሚናገር በመሆኑ ልክ እንደ ውዳሴ ማርየም የየእለት/የየቀን ስላለው ብንጸልየው በዓይነ ሕሊና ቀራንዮ ወሰዶ በነፍሳችን የጌታችንን ሰማያዊ ውለታ የሚስልብንና በመጸለያችን ልዩ ጸጋና ክብር የሚያሰጥ የቃል-ኪዳን ጸሎት በመሆኑ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ብንጸልየው እጅጉን እንጠቀምበታለን። ውዳሴ አምላክም የጌታችን ምስጋና በመሆኑ መጸለይ እንችላለን።

በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩት ጸሎቶች የትኞቹ ናቸው?

በሰሞነ ሕማማት የማይጸለዩትን ጸሎቶች ጠቅለል አድርገን ስናያቸው ድርሳናት ገድላት እና መልካ መልኮች ናቸው። ይህም የሆነው በሰሞነ ሕማማት ጌታችን ለእኛ ለሰው ልጆች ብሎ የተቀበላቸውን ስቃይ እና መከራ ሞት የምናስብበት እና የምናለቅስበት እንጂ ሌሎቹን በድርሳናቸው በገድላቸው በመልካቸው የምናመሰግንበት ጊዜ ስላልሆነ ነው።

በተረፈ በዚህ በሰሞነ ሕማማት ለራሳችሁ ለሀገራችሁ ብቻ አትጸልዩ ለዓለም ሕዝብ ለአሕዛብ በሙሉ ጸልዩ። ምክንያቱም ለእነሱ የመጣ ሰማያዊ ቁጣ በቀጥታም በተዘዋዋሪም ለእኛም ይተርፋልና። እነሱ ሲለበለቡ እኛ መቃጠላችን እነሱ ሲሰበሩ እኛ ወለም ማለታችን እነሱ ሲሞቱ ሞት ደጃፋችን መቆምን በማሰብ ለእነሱም እንጸልይ። የእነሱ መከራ ሲርቅ ነው የኛም የሚርቀው።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
46 viewsኢትዮጵያ ◁, 14:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 17:35:23 ​​​​​​በሰሙነ ሕማማት የሚፈጸ ሥርዓቶች

1, ስግደት :-
በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል።

2, ጸሎት :-
በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው።

በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ።

3, ጾም :-
በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል።

4, አለመሳሳም :-
አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29

5. አክፍሎት :-
እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው።

6, ጉልባን :-
ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው።

7, ጥብጠባ :-
ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው።

8, ቄጠማ :-
ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን።

እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም።

@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
@ortodoxmezmur
32 viewsኢትዮጵያ ◁, 14:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-16 21:14:41 ሆሳዕና_ማለት_ምን_ማለት_ነው ??
በሆሳዕና_ለምን_ቀለበት_እናስራለን ?
በሆሳዕና_ጌታችን_ለምን_በአህያ_ላይ_ተቀመጠ .
በሆሳዕና_ለምን_ዘንባባ_አነጠፉ ?
................................................................
እና ሌሎች በደንብ ይነበብ ሼር!
=> ሆሳዕና ማለት ምን ማለት ነው??
ሆሳዕና ማለት፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ ‹‹እባክህ አሁን አድን አሁን ባርከን›› ማለት ነው፡፡በሰሙነ ሕማማት ጸሎተ ፍትሃት ጸሎተ አስተስርዮ ስለማይፈጸም ጸሎተ ፍትሃትና አስተስርዮ
የሚደረገው በዚሁ ዕለት ነው::

=> በሆሣዕና ዕለት በእጃችን እደ ቀለበት ማሰራችን የምን ምሳሌ ነው??
1.ጌታ ለአዳም የሰጠው ቃል ኪዳን ለማስታወስ፡-ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድነሃለሁ ያለውን የተስፋ ቃል ለማስታወስ፡፡
2.ጌታ ለእመቤታችን የገባላትን ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
3.ጌታ ለእስራኤላውያን የሰጣቸው ቃል ኪዳን ተምሳሌት ነው።
4.ጌታ ለአዳም ከሰይጣን ግዛት ነጻ እንዳወጣው ሁሉ እኛም ከሰይጣን ግዛት ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ከክፋት ከኃጢአት አውጣን ማረን ለንስኃ ሞት አብቃን ከቤትህ አትለየን እንደ ቸርነትህ ይቅር በለን ስንል ለጌታ ዳግም ላናጠፋ ቃል የምንገባበት ነው፡፡

=> ጌታችን በዕለተ ሆሳዕና ለምን በፈረስ ላይ አልተቀመጠም??
ትንቢቱንና ምሳሌውን ለመፈጸም ነው፡፡ "
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ
ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።(ትንቢተ ዘካርያስ 9:9)
=> በአህያ መቀመጡ፦

•ትህትናን ለማስተማር
•የሰላም ዘመን ነው ሲል
•ለፈለጉኝ ሁሉ የቅርብ አምላክ ነኝ ሲል በንጽህና በየዋህነት ለሚኖሩ ምዕመናን አድሬባቸው እኖራለሁ ሲል፡፡

•አህያዎች ትሁታን ናቸው ረጋ ብለው ነው
የሚሄዱት፤በቀላሉ ትወጣበታለህ፤በቀላሉ
ትይዘዋለህ፤እንደፈለክም ታዝዋለህ።
ጌታችን ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ዘባባ የመነጠፉ ሚስጢር የምን ምሳሌ ነው???
1.ዝንባባ፡- ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ ደስ ብሎት አብርሃምን ዘንባባ ይዞ እግዚአብሔር አመስግነዋል፡፡
2.ዝንባባ ደርቆ እንደገና ሂይወት ይዘራል፡- የደረቀ የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
3.ዝንባባ የሰላም ምልክት ነው፡- የሰላም አምላክ ነህ ሲሉ ነው።
4.ዝንባባ የደስታ መግለጫ ነው፡- አንተ ደስ የምታሰኝ ሃዘናችንም የምታርቅልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
5.ዝንባባ እሾሃማ ነው፡- አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡
6.ዝንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጂ፡፡ ጌታም አንተ ባህሪህን የማይመረመር ነው ሲሉ ነው፡፡
ህዝቡ ከልብሳቸው ሌላ ስንት አይነት ቅጠንል አነጠፉለት ምን ምን??

ልብሳቸውን ማንጠፋቸው፡-
ለክብሩ መግለጫ ነው፡፡
ሌሎችም ሦስት አይነት ቅጠል አነጠፉለት ዘንባባ፤የቴመር ዛፍ፤የወይራ ዛፍ አነጠፉለት፡፡
ትልቅዋ አህያ በምን ትመሳለለች ውርን ጭለዋስ???
ትልቅዋ አህያ የኦሪት ምሳሌ ነው።
1.ትልቅዋ አህያ ሸክም የለመደች ናት ህገ ኦሪትም የተለመደች ህግ ናትና፡፡
2.የእስራኤል ምሳሌ ነው፡-ትልቅዋ አህያ ሸክም እንደለመደች ሁሉ እስራኤልም ህግ ለመፈጸም በህግ ለመራመድ የለመዱ ናቸው፡፡
3.የአዳም ምሳሌ ነው፡- አዳም ሸክም የበዛበት ነበርና።

ውርጭላዋ
1.በህገ ወንጌል ትመሰላለች፡-ምክንያቱም ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ የመሰረታት የሰራት አዲስዋ ህግ ናትና፡፡
2.በአህዛብ ትመሰላለች፡-ትንሽዋ አህያ ሸክም የለመደች አይደለችም እንዲሁም አህዛብም ህግህን የመቀበል የመቀበል የለመደ አይደሉም፡፡ ለህግህ አዲስ ናቸውና፡፡
3.የእመቤታችን ምሳሌ ናት፡- የዓለም ሸክም አቅልላለችና በእመቤታችን ትመሰለላለች፡፡ እመቤታችን ድህነተ ምክንያታችን ጌታን የተሸከመች ንጽህት እንከን የሌላት እናት ናትና፡፡

ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል ወለመስቀሉ_ክቡር አሜን አሜን አሜን
ዘተዋህዶ
@tewhodox
@tewhodox
ለወዳጅ ለዘመድ ለጓደኛ ያጋሩ
41 viewsኢትዮጵያ ◁, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-02-23 12:16:37
80 views🅕ⓚ🅡ⓤ, 09:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 15:00:30 መልክዐ ገብርኤል
ይኸው
124 views🅕ⓚⓡⓤ... ... ...¤∞, 12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-12-22 14:59:17
ሥርዓተ ማኅሌት ዘታህሳስ ቅዱስ ገብርኤል

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለጒርኤክሙ ስቴ አንብአ ሰብእ ዘኀሠሠ፤ ብዑላነ ሞገስ ሥላሴ ኢታንድዩኒ ሞገሰ፤ እመትትሐየዩኒሰ ኢትኅድጉኒ ጽኑሰ፤ ሚካኤልኑ ለአውጽኦ ሥጋየ ጌሠ። ወእመ አኮ ገብርኤል ወሀበኒ ነፍሰ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አድኅነነ እግዚኦ አምላክነ፤ ረዳኤ ኲነነ ወኢትግድፈነ፤ ወኢትትሐየየነ በዕለተ ምንዳቤነ፤ ርድአነ በኃይለ መላእክቲከ፤ ከመ ኢንትሐፈር በቅድሜከ።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሚካኤል ዘትቀውም በየማና ለማርያም ድንግል፤ ወበጸጋማ ገብርኤል አብሣሬ ትስብእቱ ለቃል፤ ዕቀቡነ ዘልፈ ለለመዋዕል፤ እንዘ ትሰፍሑ አክናፊክሙ ዘነበልባል፤ ወረድኤትክሙ አድኅኖ ዘይክል።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አብሠራ ገብርኤል ለማርያም ወይቤላ ትወልዲ ወልደ፤ ሚካኤል መልአክ በክነፍ ፆራ፤ መንጦላዕተ ደመና ሠወራ፤ ንጽሕት በድንግልና አልባቲ ሙስና፤ ወልድ ተወልደ እምኔሃ።
@EOTCmahlet
ነግሥ
ሰላም ለከ ገብርኤል ላዕክ፤ ትስብእተ ፈጣሪ ዘትሰብክ፤ ኀበ ማርያም ልደተ አምላክ፤ ለዳንኤል ዘገሠሥኮ ጊዜ መሥዋዕተ ሠርክ፤ ምስዋዒነ ለለሳዑ ባርክ ባርክ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
እስመ ተለዓለ ዕበየ ስብሐቲከ መልዕልተ ሰማያት፤ እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሐተ፤ ባርካ እግዚኦ ለዛቲ መካን።
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢይተረጎም ምስጢር፤ ባሕቱ ይመስል ብሂለ እግዚእ ወገብር፤ ገብርኤል ኪሩብ ፀዋሬ ዓቢይ መንበር፤ ሕዝቅኤል ዘነጸረከ በአምሳለ ብእሲ ክቡር፤ ምስለ ገጸ ላህም ወአንበሳ ወቀሊል ንስር።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ፤ እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ፤ ሥጋዌ ቃል ለድንግል ይሰብክ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ገብርኤል ብሂል ብእሲ ወአምላክ/፪/
እምኀበ እግዚአብሔር ዘተፈነወ ላዕክ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለአዕዛኒከ ኆኅያተ ቃለ አብ ሕያው፤ ወለመላትሒከ ልሑያት አምሳላተ ጽጌ ዘበድው፤ ኦ ገብርኤል መልአከ አድኅኖ ፍንው፤ አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ በአክናፊከ ምንትው፤ አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ፫ቱ ዕደው።
@EOTCmahlet

ወረብ
አድኅነኒ ዘአድኃንኮሙ ሊቀ መላእክት አድኅነኒ ሊቀ መላእክት ዘአድኃንኮሙ/፪/
፫ቱ ዕደው አመ ውስተ እሳት ተወድዩ ዘአድኃንኮሙ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ዘአድኃኖሙ እምዕቶነ እሳት፤ ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል፤ ከማሆሙ ያድኅነነ፤ እምኲሉ ዘይትቃረነነ።

ወረብ
እምዕቶነ እሳት 'ዘአድኃኖሙ'/፪/ ገብርኤል ሊቀ መላእክት/፪/
ለአናንያ ወአዛርያ ወሚሳኤል ዘአድኃኖሙ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
ሰላም ለአቊያጺከ ወለአብራኪከ ገሃደ፤ እለ ያቄርባ ወትረ ለአምላከ ሰማይ ሰጊደ፤ እግዚአ አእምሮ ገብርኤል ዘኢትፈቅድ ዕበደ፤ ጥበብ ሐነጸት በወርኅከ ውስተ ልበ አብዳን ማኅፈደ፤ ወአቀመት ላቲ ፯ተ አዕማደ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
እግዚአ አእምሮ ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ፤ ዘኮነ ሥውረ ውስተ ማዕምቀ ጽልመት፤ ወሀቤ ቃለ ትፍሥሕት ለእለ ይሰብኩ ዕበየ ኃይልከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
እግዚአ አእምሮ ገብርኤል ወዜናዌ ጥበብ ዘከሠተ ለነ/፪/
ዘኮነ ዘኮነ ሥውረ/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ገብርኤል
አልቦ እምሰብእ ዘከማየ ዘይቴክዝ ነግሃ ወሠርከ፤ ወአልቦ እመላእክት ናዛዜ ኅዙናን ዘከማከ፤ ወበእንተዝ ኃሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ፤ ኦ ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዓኒ ቃለከ፤ ዕሴተ ጸሎትየ ዝንቱ ዘአቅረብኩ ለከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ወበእንተዝ ኃሠሥኩ አእሚርየ ኪያከ/፪/
ኦ ገብርኤል ናዝዘኒ ወአስምዓኒ ቃለከ/፪/
@EOTCmahlet
ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ፤ አርእየኒ ገጸከ አርእየኒ ገጸከ ወአስምዓኒ ቃለከ፤ ነፍስየ ጥቀ ኃሠሠት ኪያከ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ገጸከ አርእየኒ/፪/
ወአስምዓኒ ቃለከ ሊቀ መላእክት/፪/
@EOTCmahlet
ማኅሌተ ጽጌ
ፈትለ ወርቅ ወፈትለ ሜላት አመ በአጽባዕትኪ ተባየጹ፤ አምሳለ መለኮት ወትስብዕት እንዘ ኢየሐፁ፤ ተአምረ ብርሃን ማርያም ለፀሐየ ጽድቅ አንቀጹ፤ ጸገይኪዮ እንበለ አብ በሰሚዓ ቃሉ ወድምፁ፤ ለገብርኤል መልአክኪ ዘፍሡሕ ገጹ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
መልአከ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል፤ መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል፤ ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል፤ ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል።

አመላለስ፦
መልአከ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ኃይል፤
መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል፤

@EOTCmahlet
ወረብ
ቅዱስ ገብርኤል መልአከ ኃይል መልአከ ፍሥሐ በእሳት ሥዑል/፪/
ሰበካ ለድንግል ምጽአቶ ለቃል ወርቀ ወሜላተ እንዘ ትፈትል/፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ፤ ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤ ወትቤሎ ይኩነኒ በከመ ትቤለኒ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
ወትቤሎ ይኩነኒ/፪/
በከመ ትቤለኒ ይኩነኒ/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ
'ወእንዘ ትፈትል'/፪/ ወርቀ ወሜላተ/፪/
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ ወረብ
ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ አስተርአያ ገብርኤል ግብተ፤
ወይቤላ እስመ ረከብኪ ሞገሰ በኀበ እግዚአብሔር፤
@EOTCmahlet
ወቦ ዘይቤ፦
ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወእንዘ ትፈትል ወርቀ ወሜላተ፤
አስተርአያ ገብርኤል አስተርአያ ለማርያም ፤
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet

እስመ ለዓለም
ክብሮሙ ለመላእክት ከመ መንኮራኲር፤ ወረደ መልአከ እግዚአብሔር ኀበ ማርያም ድንግል፤ ዘተናገሮ ለሙሴ በኀበ ዕፀ ጳጦስ፤ ዕፀ ጳጦስ ይእቲ ማርያም፤ ገብርኤል ሰበከ ላ ዜና፤ ዘለአኮ ኲሎ ነገራ።

አመላለስ
ገብርኤል ሰበከ ላ ዜና ገብርኤል ሰበከ/፪/
ዘለአኮ ኲሎ ነገራ/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ
ክብሮሙ ለመላእክት ከመ መንኮራኲር ወረደ መልአከ እግዚአብሔር/፪/
ኀበ ማርያም ድንግል ዘተናገሮ ለሙሴ በኀበ ዕፀ ጳጦስ/፪/


@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet


@EOTCmahlet
#Join & share
115 views🅕ⓚⓡⓤ... ... ...¤∞, 11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ