Get Mystery Box with random crypto!

አንበሳዎች ከብዙ ትግል በኋላ አንድ አህያ አድነው ያዙ። ከምንበላው ለምን በጉዲፈቻ አናሳድገውም ብ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አንበሳዎች ከብዙ ትግል በኋላ አንድ አህያ አድነው ያዙ። ከምንበላው ለምን በጉዲፈቻ አናሳድገውም ብለው ተስማሙም። ልጃችን ነው ብለው አወጁም።

ከዝያም የአንበሳዎች ተወካይ አድርገው ወደ አህያ መንጋ ላኩት'ና ከአህያዎች መካከል በክብር ይኖር ጀመር።

አህያው ከመንጋው ተቀላቅሎ በሚኖርበት ግዜ ‹‹ትዕዛዜን ጥሷል›› ብሎ ያሰበውን ማንኛውንም አህያ እየመለመለ ለአንበሳዎች ምሳ ይሆን ዘንድ አሳልፎ ይሰጣል። በዚህ ምክንያት አንበሳዎች ከአደን ድካም ተገላግለው ቀለባቸው ደጃቸው ድረስ መምጣት ጀመረ።

አሁን ይህ የጉዲፈቻ አህያም በአህያዎች መኃል አንበሳ ሁኖ በአንበሳዎች መኃል ደግሞ አህያ ሁኖ ሲያገለግል መኖሩን ቀጥሏል።

የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
http://youtube.com/@zikrmenzumaneshidatube

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

Join Tg
https://t.me/ZEKR_MENZUMA