Get Mystery Box with random crypto!

አዲሱ መጅሊስ ውስጥ ምንድነው እየተካሄ ያለው ቆይ እንዴ..? ምንድነው አላማቸው? እኔ እነሱን ለመ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አዲሱ መጅሊስ ውስጥ ምንድነው እየተካሄ ያለው ቆይ እንዴ..? ምንድነው አላማቸው? እኔ እነሱን ለመረዳት ብዙ ሞከርኩ ግን ፈፅሞ ሊገቡኝ አልቻሉም..? ይሄን ቪድዮ ተመልከቱት መጅሊሱ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከመንግሥት ጋር እንዲወያዩ ያቋቋማቸው ኮሚቴዎች ከሰላም ሚኒስተር ጋር ሲወያዩ የሚያሳይ የዜና ዘገባ ነው። ሙሉ ዜናውን አዲስ ቲቪ የዩቲዩብ ቻናል ላይ ገብታችሁ መመልከት ትችላላችሁ።

እኛ ከመስጂድ ፈረሳዎች በተጨማሪ ሰሞኑን ለደረሰብንን እልቂት ድምፅ ሆነው ለበደላችን መፍትሄ ያመጡልናል ብለን ስንጠብቅ...ጭራሽ "እኛ ባለፈው ጁመዓ ተቃውሞ እንዳይደረግ በደብዳቤ ለሁሉም መስጂዶች ብናሳውቅም በኛ ስር የሚተዳደሩ መስጂዶች ላይ ተቃውሞ ሳይነሳ እነዚህ ሁለት መስጂዶች ማለትም (አንዋር እና በኒ) ላይ ተቃውሞ የተነሳው በኛ ማለት በመጅሊሱ ስር ስለማይተዳደሩ ነው" ብለው ለደረሰው በደል እና ግፍ ጀስቲፋይ አድርገው ቁጭ አሉ። ለዛውም አንዋር መስጂድ ላይ ምንም አይነት ተቃውሞ እንዳልነበር የቪድዮ ማስረጃዎች ጭምር እያለ።

ይገርማል እኛ የደረሰብንን በደል፣ ህመም እና ግፍ ተሰምቷቸው ከመንግስት ጋር ቁጭ ብለው አውርተው ለችግሮቻችን መፍትሔ ያመጣሉ ብለን ስንጠብቅ አሁንም እነሱ የሚያሳስባቸው የብዙ መስጂዶች መፍረስ እና የምዕመን መሞት ሳይሆን ሁለት መስጂዶችን በስራቸው አለማስተዳደራቸው ነው....ብቻ ከዚህ ብኋሏ በነገሮች አዝኖ እና ተስፋ ቆርጦ ዝም ከማለት ውጪ አማራጭም የለን። ይሰለቻል