Get Mystery Box with random crypto!

የትምህርት ሚንስትር ውሳኔን በተመለከተ፦ .. ❐ ውሳኔው የዛሬ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊትም በዒድ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

የትምህርት ሚንስትር ውሳኔን በተመለከተ፦
..
❐ ውሳኔው የዛሬ ብቻ ሳይሆን ከዚህ በፊትም በዒድ ቀን የ12ኛ ክፍል ተፈታኞችን እንደሚፈትን መግለጹ ሙስሊሙን አስቀይሞ በመጅሉሱ ጥያቄ መሠረት ማስተካሉ የሚታወስ ነው።
..
❐ ይህንን ስህተቱን መልሶ በ2019 ደግሞት ሌላ ከፍተኛ ቅሬታ ማስነሳቱ ተመሳሳይ ትውስታ ነው። ሚንስትር መስሪያ በየአመቱ ካሌንደር የሚዘጋቸው የሙስሊም በአላት ወቅት ያለምንም ሀፍረት ተደጋጋሚ ስህተት ሲሰሩ ቆይተዋል።
...
❐ ግራ የሚያጋባው ነገር ሚንስትር መስሪያ ቤቱ ውስጥ ፕሮግራም የሚያወጡ ሰዎች ካሌንደር አይመለከቱም ወይ የሚለው ነው? ይህንን እንዳንል አንድም ቀን በክርስትናው በአላት ወቅት መሠል ስህተት ሰርተው ተመልክተን አናውቅም። በመንግስት አሰራር መሠረት ካሌንደር የሚዘጋጃቸው በአላትን እንደ ተቋም ማክበር እንደሚጠበቅባቸውስ አያውቁም?
...
❐ ባለቀ ሰአት ተማሪዎች ኒቃብ እንዳይለብሱም ከልክለዋል። ምን ማለት ነው? 12 አመት ተምረው ለፈተና ተዘጋጅተውና ለፍተው በስተመጨረሻ ሊፈተኑ ጥቂት ቀን ሲቀራቸው በሀይማኖታዊ አለባበሳቸው ምክንያት የመጨረሻ ህይወታቸውን ለማበላሸት መጣደፍ ጥላቻችሁ ምን ያክል ስር ቢሰድ ነው?
...
❐ ጉዳዩ የመውሊድ መከበር አለመከበር ጉዳይ አይደለም። ጉዳዩ ሚንስትር መስሪያ ቤቱ የ"ሙስሊም" ተብለው የተገለጹ እሴቶች ላይ በደፈናውና በተከታታይ የሚሰራው መዘባበትን የመቃወም ነው። እዚህ ላይ የአመለካከት ልዩነትን እያመጡ መጨቃጨቅ ፈጽሞ የዋህነት ነው። ጉዳዩን የወሰነው የዑለሞች ም/ቤት ሳይሆን ትላንት ኢድን ሳይቀር ንቆ ተማሪዎችን እፈትናለሁ ሲል የነበረ ሚንስተር መስሪያ ቤት ነው። በዚህ ከቀጠለ የነገ ግብታዊ እርምጃው የት ሊደርስ እንደሚችል መገመት ቀላል ነው።
@ZEKR_MENZUMA