Get Mystery Box with random crypto!

ይህች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም..! ... ➭ ከመላው ህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ የተሰራ ሆስፒታል | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

ይህች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም..!
...
➭ ከመላው ህዝብ በሚሰበሰብ ገንዘብ የተሰራ ሆስፒታል ያለምንም ሀፍረት የስብከት ሜዳ ሲሆን "ለምን" ብለን ካልጠየቅን ነገ ምን እንደሚያደርጉን ዋስትናው የለንም። ሀገሪቱ ሳናውቀው ክርስቲያናዊ ስርአትን ኦፊሺያሊ እየገተበረች ከሆነም ይነገረንና ቁርጣችንን እንወቅ። እኔም ሆነ የትኛውም ሙስሊም በሚከፍለው ግብር የተቋቋመ የህዝብ መግለገያ አዳራሽ የሰበካ ቦታ እንዲሆን አንፈልግም። ሁሉም ነገር ቦታ አለው..! መረን የለቀቀ ድፍረት ዛሬ ላይ እንዲህ ካየን ነገ ጭራሽ ሆስፒታሉ ውስጥ ካልተጠመቅክ አትስተናገድም መባሉ አይቀርም። ነውር ነው..!
...
➭ የገረመኝ ደግሞ የክርስቲያን ቲዩብን ፖስት እንደ ጀብድ ላይክ የሚያደርገው ማን ቢሆን ጥሩ ነው? የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምን እየተካሔደ ነው እዚያ ክልል? እንዴው ህጉን ባትፈሩ ሀፍረትና ይሉኝታ የሚባል ነገር የለምንዴ? በዚህ ደረጃ በይፋ ይህንን ከሰራችሁ በድብቅ የምትሰሩንና ያሰባችሁልማ የከፋ ነው ማለት ነው። አሏህ ﷻ ከሸራችሁ ይጠብቀን እንጅ ይህች ባቄላማ ካደረች አትቆረጠምም..!!
___________
የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎቻችንን እና በህይወት ያሉትን ዑለማዎቻችንን መንዙማዉች እና ስራዎች እንዲሁም አዳዲስ መንዙማውች ልክ እንደተለቀቁ የሚቀርብበት ቻናል በተጨማሪም በዚህ ቻናል
ስለ ወርቃማው ታሪካችን እናወራለን።
ዑለሞቻችንን እናወሳለን፤
ጀግኖቻችንን እንዘክራለን፤
ሳይንቲስቶቻችንን እናነሳለን።
ሰብስክራይብ በማረግ ቤተሰብ ይሆኑ ለወዳጆም ሼር ያርጉ
https://www.youtube.com/channel/UCW7Mi9alF-Wnl9MRyll7g5A

Facebook page
https://www.facebook.com/profile.php?id=100066797534886

TG
@ZEKR_MENZUMA