Get Mystery Box with random crypto!

አስደሳች ዜና ከ3 ዓመት በፊት ብር ከፍላችሁ ሳትሄዱ ለቀራችሁ ሁጃጆች !! ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፤ በ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አስደሳች ዜና ከ3 ዓመት በፊት ብር ከፍላችሁ ሳትሄዱ ለቀራችሁ ሁጃጆች !!
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፤ በተለይም ህዝበ ሙስሊሙ እንደሚያስታውሰው በ2011 ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሐጅ ለማድረግ ተመዝግበው እና 78,150 ብር ከፍለው ያልሔዱ 479 የሱማሌና የኦሮሚያ ክልል ሁጃጆች ብራቸው የት እንደገባ ሳይታወቅ የኖሩ ግለሰቦች መኖራቸው ይታወቃል ።
ምንም እንኳን ችግሩ የተፈጠረው " የመጅሊሱ የስራ አመራር ቦርድ ነኝ " ብሎ ለራሱ ስልጣን ሰጥቶ ሲኮፈስ በኖረውና በተባረረው ቡድን ቢሆንም ፤ በሁለት የቦርድ አባላት እና በወቅቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ በነበሩት ግለሰብ ጥፋት የሙስሊሞች ገንዘብ በከንቱ መቅረት እንደሌለበት የዑለማ ምክር ቤት አምኖበታል ።
በመሆኑም ብራቸውን ከፍለው ሳይሄዱ የቀሩ ሰዎች የዛሬ ሶስት ዓመት ከከፈሉት ብር ላይ በዚህ ዓመት ያሳየውን የዋጋ ልዩነት ከራሳቸው ኪስ ጨምረው ሐጅ እንዲያደርጉ ፤ መሔድ የማይፈልጉ ደግሞ ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ዑለሞቹ ወስነዋል ።
በመሆኑም ስህተቱም ጉድለቱም የተካሄደው በተደራጀ የቡድን አሠራር ስለሆነ ፤ ይህ ደግሞ በዝርዝር ተጣርቶ ጥፋተኞቹ በአላህም በህግም መጠየቃቸው የማይቀር መሆኑ ቢታወቅም ፤ ምክር ቤቱ እንደ ተቋም ገንዘባቸውን የተቀሙ ሰዎችን ኃላፊነት መውሰድ ስለሚገባው በ2011 ብር ከፍላችሁ ሐጅ ያላደረጋችሁ ግለሰቦች እየመጣችሁ እንድትመዘገቡ እና ለጉዞ እንድትዘጋጁ መጅሊሱ በታላቅ አክብሮት ይጠይቃል ።
በዚህ አጋጣሚ ራሱን " የምሁራን ቦርድ ነኝ " እያለ የሚጠራውና የተባረረው ቡድን ቢሮ ሰብሮ ለመግባት ተደጋጋሚ ሙከራ ያደረገ ፤ የተቋሙን ኮምፒውተሮች ፣ የመጅሊሱን የፌስቡክ አካውንት ፣ የቢሮ መኪና እና የመጅሊሱን ማህተም እስከዛሬ ድረስ ይዘው እንደጠፉ ህዝበ ሙስሊሙ እና መንግስት ሊያስታውስ ይገባዋል ። ይህ ቡድን የዘንድሮውን የሐጅ ስራ በሀገር ውስጥና በውጭ አገር ጥላሸት ለመቀባትም እየተንቀሳቀሰ መሆኑን መረዳት ተችሏል ።