Get Mystery Box with random crypto!

አስደሳች ዜና ከ3 ዓመት በፊት ብር ከፍላችሁ ሳትሄዱ ለቀራችሁ ሁጃጆች !! ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፤ በ | ﷽ዚክረ መንዙማﷺ

አስደሳች ዜና ከ3 ዓመት በፊት ብር ከፍላችሁ ሳትሄዱ ለቀራችሁ ሁጃጆች !!
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ፤ በተለይም ህዝበ ሙስሊሙ እንደሚያስታውሰው በ2011 ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሐጅ ለማድረግ ተመዝግበው እና 78,150 ብር ከፍለው ያልሔዱ 479 የሱማሌና የኦሮሚያ ክልል ሁጃጆች ብራቸው የት እንደገባ ሳይታወቅ የኖሩ ግለሰቦች መኖራቸው ይታወቃል ምንም እንኳን ችግሩ የተፈጠረው " የመጅሊሱ የስራ አመራር ቦርድ ነኝ " ብሎ ለራሱ ስልጣን ሰጥቶ ሲኮፈስ በኖረውና በተባረረው ቡድን ቢሆንም ፤ በሁለት የቦርድ አባላት እና በወቅቱ የሐጅና ዑምራ ዘርፍ ኃላፊ በነበሩት ግለሰብ ጥፋት የሙስሊሞች ገንዘብ በከንቱ መቅረት እንደሌለበት የዑለማ ምክር ቤት አምኖበታል ።
በመሆኑም ብራቸውን ከፍለው ሳይሄዱ የቀሩ ሰዎች የዛሬ ሶስት ዓመት ከከፈሉት ብር ላይ በዚህ ዓመት ያሳየውን የዋጋ ልዩነት ከራሳቸው ኪስ ጨምረው ሐጅ እንዲያደርጉ ፤ መሔድ የማይፈልጉ ደግሞ ገንዘባቸው እንዲመለስላቸው ዑለሞቹ ወስነዋል ።
በመሆኑም ስህተቱም ጉድለቱም የተካሄደው በተደራጀ የቡድን አሠራር ስለሆነ ፤ ይህ ደግሞ በዝርዝር ተጣርቶ ጥፋተኞቹ በአላህም በህግም መጠየቃቸው የማይቀር መሆኑ ቢታወቅም ፤ ምክር ቤቱ እንደ ተቋም ገንዘባቸውን የተቀሙ ሰዎችን ኃላፊነት መውሰድ ስለሚገባው በ2011 ብር ከፍላችሁ ሐጅ ያላደረጋችሁ ግለሰቦች እየመጣችሁ እንድትመዘገቡ እና ለጉዞ እንድትዘጋጁ መጅሊሱ በታላቅ አክብሮት ይጠይቃል