Get Mystery Box with random crypto!

አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ሹመታቸውን ከሚያፀድቃቸው ባለ ስ | Zehabesha

አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ሹመታቸውን ከሚያፀድቃቸው ባለ ስልጣናት አንዱ ናቸው። በተለምዶ የሰኔ 15ቱ የባለ ስልጣናት ግድያ ተብሎ በሚጠራው ቀውስን ተከትሎ ክልሉን በመምራት አንፃራዊ የፖለቲካ መረጋጋትን ማምጣታቸው አይዘነጋም። ጠንካራ ጎናቸው በቲም ስራ ማመናቸው ነው ይላሉ።

የምክትል ጠቅላይ ሚኒሰተርነቱን ማእረግ ሲያገኙ የህዝብን ጥያቄ በመመለስ በተለይ የአማራ ክልልን ፖለቲካና ኢኮኖሚ ያረጋጉ ይሆን? የሚል ጥያቄ ይነሳል።

ወጣት ምሁራን ወደ መድረኩ በማምጣት በአዲስ አመራር ክልሉ ከገባበት ቀውስ ማውጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህን ያደርጉ ዘንድ መልካም የስራ ዘመን እንመኛለሁ ።

መምህር ባሻ