Get Mystery Box with random crypto!

የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን ሰኞ በ9 ሰአት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን | Zehabesha

የጋዜጠኛ አስፋው መሸሻ የቀብር ስነስርዓት የፊታችን ሰኞ በ9 ሰአት በቅድስት ስላሴ ቤተክርስቲያን እንደሚፈፀም ቤተሰቦቹ ለዘሐበሻ ተናግረዋል። ለቅሶ መድረስ ለምትፈልጉ የእናቱ ቤት አድራሻ
አያት ዞን 8 መንገድ 5 ውስጥ ነው።

በአሜሪካ የአስፋው መሸሻ የሽኝትና የጸሎት መርሃግብር የሚከተለው ነው።

ረቡዕ ጃንዋሪ 17፣ ከቀኑ 2PM ጀምሮ፣
ቨርጂኒያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ECDC) አዳርሽ የሽኝት መርሃግብር
901 S Highland St,
Arlington, VA 22204

ሃሙስ፣ ጃንዋሪ 18
ከጠዋቱ 10 AM ጀምሮ የጸሎት ስነስርዓት በደብረገነት መድሃኒአለም ቤተክርስትያን
4401 Old Branch Ave.,
Temple Hills, MD 20748

ከጸሎተ ፍታቱ በኋላ ከ1 PM ጀምሮ ጸበል ጸዲቅ ቨርጂኒያ በሚገኘው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ECDC) አዳርሽ
901 S Highland St,
Arlington, VA 22204
ነፍስ ይማር።