Get Mystery Box with random crypto!

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በቤት ማህበር ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታትእየሰራሁ ነ | Zehabesha

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር በቤት ማህበር ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታትእየሰራሁ ነው በመጀመሪያው ዙር ለ665 ማህበራት ቦታ ሊስረክብ ነው
******
ባህርዳር ከተማ አስተዳደር ባለፉት ዓመታት በቤት ማህበር ተደራጅተው እውቅና ያገኙ የመኖሪያ ቤት ስራ ማህበራትን ጥያቄዎችን ለመፍታት በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት ዕውቅና ያገኙትን ማህበራትን ለማስተናገድ እየተሰራ ነው ። በመሆኑም ፦

1. በባህርዳር ከተማ አስተዳደር ቦታ ለመውሰድ የተደራጁ 465 ማህበር 9,916 አባላት

2. በሳተላይት ከተሞች ቦታ ለመውሰድ የተደራጁ

2.1 መሸንቲ 185 ማህበር 3,806 አባላት እና በ11 ማህበር የተደራጁ 260 የአርሶ አደር ልጆች

2.2 ዘንዘልማ 174 ማህበራት 3,659 አባላት የሳተላይት ድምር 359 ማህበራት 7,465 አባላት

ጠቅላላ የተደራጁና እውቅና ያገኙ የቤት ስራ ማህበራት ቁጥር 835=ከ 17,641 አባላት በላይ ሲሆን እስከ ሰኔ 30/2014 በ2ዙር ለማስተናገድ ታስቦ እየተሠራ ነው።

በፕሮግራሙ መሰረት በመጀመሪያ ዙር 665 ማህበራት ከ13,979 አባላት በላይ ለሚሆን የሚሰጥ ሲሆን በሁለተኛ ዙር ደግሞ ለ170 ማህበርተኞች ለ3,662 አባላት የሚስተናገዱ መሆኑን ከከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።