Get Mystery Box with random crypto!

የፕ/ር አስራት ወልደየስ የ23ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ . ዛሬ ጠዋት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተ | Zehabesha

የፕ/ር አስራት ወልደየስ የ23ኛ ሙት ዓመት መታሰቢያ
.
ዛሬ ጠዋት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን የፕሮፌሰር አስራት ቤተሰቦች፣ አድናቂዎች፣ የተለያዩ ፓርቲ አመራሮች በተገኙበት በሃይማኖት አባቶች ፀሎት እና ጧፍ ማብራት 23ኛ ዓመታቸው ተዘክሯል።

ፕ/ር አስራት ወልደየስ ፥ "የህዝብ ግድያ እና ማፈናቀል፣ ሰውን በዘሩ እና በማንነቱ መግደል እስካላቆማችሁ ድረስ በእናተ በገዳዮች ፊት ቆሜ ልሟገታችሁ ቃል እገባለሁ " ብለው ጥር 14/1984 ዓ/ም የመላው አማራ ህዝብ ድርጅት(መኢአድ)ን መስርተው ለህዝብ እኩልነት፣ መብት ፣ ነፃነት ሲታገሉ በሕወሐት/ኢህአዴግ መንግስት ታስረውና ህክምና ተነፍገው የጤና ሁኔታቸው የመጨረሻው ደረጃ ላይ ደርሶ ግንቦት 6/1991 ህይወታቸው ሊያልፍ ችሏል።

ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ፤ ከፖለቲከኛነታቸው ባለፈው በኢትዮጵያ እውቅ ከሚባሉ ሀኪሞች አንዱ ነበሩ።