Get Mystery Box with random crypto!

በመንግስት በኩል ብዙ እየተወራለት ያለው የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ለሙስና በር እየከ | Zehabesha

በመንግስት በኩል ብዙ እየተወራለት ያለው የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ለሙስና በር እየከፈተ መሆኑ ተገለጸ። የዘኢትዮጵያ ዘጋቢ ያናገራቸው የአዲስ አበባ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች፤ አጥራችሁና ቤታችሁ እንዳይፈርስ ብር አምጡ እየተባሉ በወረዳ አስተዳዳሪዎች ገንዘብ እየተጠየቁ ነው።

የወረዳ አስተዳዳሪዎች ቤት ለቤት በመምጣት ጊቢያችሁ እና ቤታችሁ እንዲፈርስ ተወስኗል፤ እንዳይፈርስ ለማድረግ ክፍያ ከከፈላችሁ ልናስቀርላችሁ እንችላለን በሚል ገንዘብ እንደሚጠይቁና ፈረሳው ለሙስና በር እንደከፈተ ተናግረዋል።

መንግስት በጉዳዩ ላይ ትኩረት ሊያደርግበት ይገባል የሚሉት እነዚሁ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በወረዳ ባለስልጣናት የምንጠየቀው በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ነው ብለዋል።