Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝና በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ 'የተናጥል ርምጃ ወስዳለች' በማለት የዓረብ ሊግ የመ | ዘ-ሐበሻ የዕለቱ ዜና - Zehabesha News

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝና በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ "የተናጥል ርምጃ ወስዳለች" በማለት የዓረብ ሊግ የመሪዎች ጉባኤ ሰሞኑን ያወጣው መግለጫ "ኾን ተብሎ እውነታውን የመቀየር" አካሄድ ነው ስትል ኢትዮጵያ አውግዛለች።

የሊጉ መግለጫ "የግብጽን ጠባጫሪ አቋም የሚያንጸባርቅ" መኾኑን የገለጸችው ኢትዮጵያ፣ ፍትሃዊና ምክንያታዊ የኾነ የውሃ አጠቃቀም እንዲኖር ቁርጠኛ መኾኗን አረጋግጣለች።

ኢትዮጵያ ጨምራም፣ ግብጽ በዓረብ ሊግ አማካኝነት ኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር መሞከሯ "ቀናዒነት እንደሌላት" ያሳያል ብላለች።

የሊጉ አባል የኾኑ የአፍሪካ አገራት ከሊጉ ውሳኔ ራሳቸውን እንደሚያገሉ እምነቷ መኾኑንም ኢትዮጵያ ገልጻለች።(ዋዜማ)