Get Mystery Box with random crypto!

ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል ፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ል | መምህር ዘበነ ለማ (ዶ/ር)



ኦ ሚካኤል ኦ መተንብል ፣ ካህነ አርያም ትሰመይ ቢጸ ሱራፌል፣ ዘእምርዑሳን ርዑስ ወዘእምልዑላን ልዑል ፣ ጊዜ ጸዋዕኩከ ቅረበኒ በምሕረት ወሣህል

አማላጃችን ሚካኤል ሆይ ፈጥኖ ደራሻችን ሚካኤል ሆይ - የጌታን ዙፋን ከሚያጥኑ ሱራፌል ካህናት አንዱ ሰማያዊ ካህን አንተ ነህ እኮን።

የሰማያውያን ሊቃነ መላእክት ሁሉ አንተ አለቃቸው ነህ እኮን። ይልቁንም የልዑላንም ልዑል አንተ ነህና - በጠራሁህ ጊዜ ሁሉ በይቅርታና በቸርነት ድረስልኝ አትራቀኝ!

መልክአ ሚካኤል