Get Mystery Box with random crypto!

#ታኅሣሥ_6 ዛሬ በደጇ ወድቀን የምንለምናት ሁሉ በህይወት ስጋ በመከራ ሆና አምላክነቱን የመሰከ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

#ታኅሣሥ_6

ዛሬ በደጇ ወድቀን የምንለምናት ሁሉ በህይወት ስጋ በመከራ ሆና አምላክነቱን የመሰከረችለት አምላክ ዛሬ በትውልዱ ሁሉ እምነቷን በእርሷ ስም ለተማፀኑ ላጣ በመስጠት ሲመሰክርላት ይኖራል ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ። ዛሬ የብዙዎቻችን ችግር በእምነት መኖርን አለማወቅ ነው አንዳዶቻችን ያመነው እምነት ምድራዊ ፍላጎታችንን እስካላሟላ ድረስ ሊያሟላልን የሚችል እምነት ስንቀያይር እንኖራለን ቁስ እስካልያዝን እስካልሰበሰብን ድረስ ምኑን አምንኩ እያልን ስናማርር እንኖራለን ። ትንሽ ሰርተን ብዙ እንፈልጋለን ። ክርስቲያን የዚህን ምድር ፍላጎት ከውስጡ ሲያወጣ ብቻ ነው የሰማይ ቤቱ ሙሉ ሚሆንለት ። ሰማእታት በእውነት የዚህን ምድር ሁሉን ነገር እንደናቁ እናስተውል ።

የሰማዕቷ የቅድስት አርሴማ አማላጅነቷ አይለየን !!

~ዲያቆን ፍፁም ከበደ~