Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ማለት ምን ማለት ነው ?? በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታችን ቤተክርስቲያ | ዘማሪ ዲ/ን ፍፁም ከበደ

ወደ ምስራቅ ተመልከቱ ማለት ምን ማለት ነው ??

በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታችን ቤተክርስቲያን የምትታነፀው ምስራቁን አቅጣጫ ጠብቃ ነው እዲሁም ከቤተክርስቲያኑ ጋር አብሮ የሚሰራው ቤተልሄም በስተምስራቅ በኩል ይደረጋል በፀሎት ሰዓትም ወደምስራቅ ዞረን ነው የምንፀልየው በስረአተ ቀብር ላይም የሞተ ሰው ሲቀበር ራሱ ወደ ምዕራብ እግሩ ወደ ምስራቅ ሆኖ ይቀበራል ሌላው ዲይቆኑ በስረአተ ቅዳሴው ላይ ወደምስራቅ ተመልከቱ ይላል ለምን ይሆን ?



፦ የአዳም አባታችን ጥንተ ርስት ገነት በምስራቅ ናት። ዘፍ 2፥8 ይች እርስታችን በአዳም በደል ምክኒያት በኪሩቤል ሰይፍ ተዘግታ ስትኖር ሞትን ድል አድርጎ በበደልን ክሶ ጌታችን መዳህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ከፈተልን ሉቃ 23፥43 ወደምስራቅ በዞርን ቁጥር ወደገነት ለመግባት የተሰጠን ተስፍ ትዝ ይለናል የተከፈተችውም ቤታችን ገነት በእምነት ወለል ብላ ትታየናለች በክርስቶስ ያገኘነውን ፀጋ እናስባለን ምድራውያን አለመሆናችንም ይታወሰነል።



፦ጌታ የተወለደው በምስራቅ ነው። ሰብዓሰገል ኮከቡን ያዩት በምስራቅ ሲሆን ያኮከብ የምህረተ እግዚአብሄር ምሳሌ ነው እነርሱን ወደ እግዚአብሄር እዳደረሳቸው ሁሉ እኛንም ወደ ለመለመው መስክ ይመራናል ማቴ 2፥2 መዝ 22፥14 ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር የጌታ መወለድ እና ያደረገልን ውለታ ይታወሰናል የምህረቱ ኮከብ እየመራን መሆኑ ትዝ ይለናል ።



፦ ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው። ከምስራቅ ጨለማውን የሚገፈው ፀሀይ እደሚወጣ ሁሉ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያምም የአለምን የሀጥያት ጨለማ የሚገፍ ፀሀዬ ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ወጥቶል (ተገኝቱል) ለእናንተ ስሜን ለምትፈሩ የፅድቅ ፀሀይ ትወጣላችሁለች ሚል 4፥1 ህዝ 44፥1፦4 ነብዩ ህዝቅየልም እመቤታችንን ያያት በምስራቅ ነው ስለዚህ ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር እመቤታችን ትዝዝዝ ትለናለች የፅድቅ ፀሀይ ክርስቶስ ስለተወለደልን በጨለማ አለመሆናችን ትዝ እያለን ከሀጥያት እንርቃለን።



፦ የአለም ድህነት የተገኘው በምስራቅ ነው ። ጌታ የተሰቀለው እና አለምን ያዳነው በምስራቅ ነው እየሩስ አሌም ምስራቃዊት ከተማናት እና በመሆኑን ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር የተሰቀለውን ክርስቶስን እና የተከፈለልንን ዋጋ እናስባለን።



፦ክርስትናና ቤተክርስቲያን የተመሰረቱት በምስራቅ ነው። የመጅመሪያው ቤተክርስቲያን የተመሰረተው በእየሩስ አሌም ሲሆን ወንጌል የተሰበከውም ከዚሁ በመነሳት ነው ።ስለዚህ ወደምስራቅ ስንዞር የቤተክርስቲያን ጉዞ የወንጌል መስፍፍት ና የህዝበ አለም መዳን ትዝ ይለናል።



፦ ምስራቅ የእግዚአብሄር ክብር መገለጫ ነው ። ኢሳ 28:13 እግዚአብሄርን በምስራቅ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሄርን ስም በባህር ደሴቶች አክብሩ ህዝ 43፦2 የእስራኤል አምላክ ክብር ከምስራቅ መንገድ መጣ።



~የጌታ ዳግም ምፅአትም ከምስራቅ ነው። ዘካ 14፥14 በዚያን ቀን እግሮቹ በእየሩስ አሌም ትይዩ በምስራቅ በኩል ይቆማሉ ሐዋ 1፦11 ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደሰማይ ሲርግ እዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል ።
• ፦ ቅዱሳን አበው ሲፀልዩ ወደ ምድራቅ ይዞሩ ነበር ዳን 6፥9 ወደ እየሩስ አሌም ያለውን መስኮት ከፍቶ ይፀልይ ነበረ ነብዩ ዳንኤል እግዚአብሄር ምሉዕ በኩልሄ (የሌለበት ቦታ የሌለ) መሆኑን ያውቃል። ነገርግን ወደ እየሩስ አሌም መዞሩ ነፍሱ የምታስባት እዲኖራት ነው ።



፦ ታቦቱ በምስራቅ በኩል ባለው ቤተ መቅደስ አስቀምጠን ስጋወ ደሙ የሚፈተተው ጌታ በምስራቅ ሀገር ጎለጎታ ለኛ ስጋውን መቁረሱ ደሙን ማፍሰሱበማሰብ ነው ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር
አሜን!